የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል

ፀሀፊ፡ ዶ/ር ቤንጃሚን ዲን

ተረጓሚ፡ ዶ/ር በቀለ ደቦጭ

ንባብ፡ ምሩቅ ዩሐንስ

ማውጫ

00:00
00:00
  • መቅድም 00:00
  • አምስት ማጣፈጫዎች 00:00
  • አምስቱ ቃላት 00:00
  • አምስቱ ገፆች 00:00

መጻህፍት

የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣምና (ማርቆስ 10፡45)

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሄር አንዲያ ልጁን እንኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና (ዮሃንስ ወንጌል 3፡16)

ደግሞም ኢየሱስ፡– እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የህይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው (ዮሃንስ ወንጌል 8፡12)፡፡

እንዲሁም ኢየሱስም፡- ትንሳዔና ህይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኮን ህያው ይሆናል (ዮሃንስ ወንጌል 11፡25)፡፡

ኃጢኣተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ወደ ዓለም መጣ (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡15)፡፡

ታላቅ ድምጽ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል፡- አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል ምንግስትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ (ራእይ 12፡10)፡፡

ታላቅ ሥራ ሰርቶአልና ለእግዚአብሄር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ አስታውቁ (ኢሳይያስ 12፡5)፡፡

በልዩ ልዩ ስነ መለኮት ሰዎች የቀረቡ ጽሁፎች

ቅዱስ ኦገስቲን የተባለ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን አባትና የስነ መለኮት ሊቅ እንዳለወ፡- ቅዱሳን መጻህፍት በትኩረት አጥበቀው የሚያስተምሩአቸው ሁለት ነገሮች አሉ፡፡ ከነዚያም አንዱ  አንድን ነገር ከማወቃችን በፊት ምን ዓይነት ነገሮችን ስለ ጉዳዩ በሚገባ መረዳት እንዳለብን መገንዘብ  ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ በሚገባ ያወቅነውንና የተገነዘብነውን ነገር ወደ ሌሎች ህይወት ውስጥ ሰርጾ እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ ጉዳዩን በሚገባ የመገንዘብን ጉዳይ እንወያይና፤ ቀጥሎ ደግሞ ጉዳዩን በተግባር ላይ የምናውልበትን መንገድ እንነጋገራለን፡፡ (Augustine).[1]

ማርቲን ሉተር የተባለው የተሃድሶ ጀማሪ እንዳለው እንዳለው፡- በክርስቲያኖች መሃል አንድን ነገር በትክክል አውቆና አረጋግጦ ከማወጅና ከማስተማር የበለጠ ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ ስለዚህ ስለ ክርስትናህ እርግጠኝነትህን ካጣህ ክርስትናህንም አጥተሃል ማለት ነው (Luther).[2]

ካልቪን የተባለው የስነ መለኮት ሊቅ ደግሞ በተመሳሳይ፡-

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም የመጣበት ዋና ዓላማው ሁሉንም ለማዳንና ለመታደግ ሲሆን የድነቱም ዜና የመጣው በስሙ ለሚምኑት ለታላላቆችና ለታናናሾች ሁሉ ነው፡፡ ይህም እውነት የሚረጋገጠው እኛ እግዚአብሄር አባታችን እርሱ አምላካችን መሆኑን አውቀንና በፍቅሩም ተነክተን በምናሳየው እውነተኛ የእምነታችን ፍሬ ነው፡፡ በዚህም እምነት አማካኝነት እኛ ሁላችን ወደ እግዚአብሄር የምንመጣበት መንገድ ተከፍቶልናል፡፡ እርሱም አዳኛችን ለመሆን የተስፋ ቃል በመስጠቱ ሁሌም ሊቀበለንና እንኳን ደህና መጣችሁልኝ ለማለት ፈቃደኛ መሆኑን  አሳቶናል ማለት ይቻላል (Calvin).[3]

እንዲሁም ፓስካል የተባለው የስነ መለኮት አጥኚ እንዳለው፡-

የክርስትና እምነት በዋናነት የሚያረጋግጣቸው ሁለት እውነቶች አሉ፡፡ እነዚያም እውነቶች የፍጥረትን ሁሉ በኃጢኣት ምክኒያት መርከስና መበላሸት እና በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የሚመጣውን ተሃድሶ ነው (Pascal).[4]

ጆርጅ ዊት ፍልድ ደግሞ እንዳለው፡- ዋና ዓላማዬ እና የህይወቴም እቅድ ድሃ ነፍሳትን ሁሉ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ማምጣት ነው (George Whitefield).[5]

ጆናታን ኤድ ዋርድም ስለ ወንጌል ትክክለኛ እውቀት ባገኘህና በተጎናጽፍክ መጠን የመንፈስንም እስትነፋስ በተቀበልከው መጠን የእግዚአብሄርን ታላቅ ክብር ለማየት የበለጠ እድልና የወንጌሉም እውነት ጣፋጭነቱ ይሰማሃል ብሎ ነበር (Jonathan Edwards)[6]

ብራይተን ኖክስ የተባለ የስነ መለኮት ሰው ደግሞ ከዘላለም ፍርድ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚያድነውን የእግዚአብሄርን ይቅርታ የሚሰብክ የስነ መለኮት ጥናት በማንም ዘንድ እንደተለመደ ጉዳይ ሊታይ ወይም ሊቆጠር አይገባም (Broughton Knox).[7]

ቢሊ ግርሃምም ስለ ጉዳዩ በአጭሩ ሲገልጹ የክርስቲያን መልእክት አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ያድናል ነው ብለው ነበር (Billy Graham).[8]

ጎዚ ኦኬኬ እና ማርክ ቶምፕሰን የተባሉ ሰዎችም፡- የክርስቶስ ወንጌል ነፍስን ከሃጢኣትና በሃጢኣት አማካኝነት ከሚመጣው ፍርድ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ አማካኝነት ሊያድንና ነጻ ሊያወጣ የሚችል፤ ህይወትንም የመለወጥ ሃይል ያለው መልእክት ነው፡፡ ይህ ወንጌል በክርስቶስ አማካኝነት የተደረገልንን ታላቅ ሥራ የምናውጅበትና ሌሎችን ሁሉ ወደዚህ እውነት የምንጠራበት አዋጅ ሲሆን በመጨረሻም ራሳችንንና ሌሎችንም ለጌትነቱ ሥልጣን በንስሃና በእምነት አማካኝነት አሳልፈን የምንሰጥበት ነገር ነው (Ngozi Okeke and Mark Thompson).[9]

[1] Augustine, Teaching Christianity, 1.1; trans. Edmund Hill, O.P. (New City Press, 2014), 99; emphasis supplied.

[2] Martin Luther, The Bondage of the Will, trans. J. I. Packer and O. R. Johnstone (James Clarke, 1957 [Orig. 1525]), 67.

[3] John Calvin, Sermons on 1 Timothy, trans. Robert White (Banner of Truth, 2018), 233; slightly amended.

[4] Blaise Pascal, Pensées, 3.194.

[5] A Letter from the Reverend Mr. Whitefield, to Some Church Members of the Presbyterian Persuasion, in Answer to Certain Scruples and Queries Relating to Some Passages in his Printed Sermons and Other Writings (S. Ireland and T. Green, 1740), 12; cited in Andrew Atherstone and David Ceri Jones eds., The Routledge Research Companion to the History of Evangelicalism (Routledge, 2022), 1.

[6] Jonathan Edwards, ‘The Importance and Advantage of a Thorough Knowledge of Divine Truth,’ in The Sermons of Jonathan Edwards: A Reader, ed. Wilson H. Kimmach, Kenneth P. Minkema, and Douglas A. Sweeney (Yale University Press, 1999), 45; slightly amended.

[7] D. Broughton Knox, Selected Works, Volume 1: The Doctrine of God (Matthias Media, 2000), 60.

[8] Billy Graham, Just as I Am: The Autobiography of Billy Graham (HarperCollins/Zondervan, 1997), 727.

[9] Ngozi Okeke and Mark Thompson, ‘What is the Gospel?’ in Charles Raven ed., The Truth Shall Set You Free: Global Anglicans in the 21st Century (The Latimer Trust, 2013), 17.

መቅድም

በአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ1968 የነበረ አር አር ቶኬን የተባለ ጻሃፊ የደረሰው ብቸኛ የተባለለት አስደናቂ የእንግሊዝኛ የልብ-ወለድ ምንባብ ነበረ፡፡ ቶኬን ልብ ወለዶች እንዴት ባሉ መንገዶችና ዘዴዎች ነገሮችን ግልጥልጥ አድረገው እንደሚያብራሩና የታወቁ ታላላቅ ሥራዎችንም እንደ ንኩለር ቦምብ እንደሚፈታቱት አስተያየት በመስጠት ተናግሮ ነበር፡፡ እንዲሁም ደግሞ አንድ አስተያየት ሰጭ የነበረ ሰው ስለ ልብ-ወለዱ ሲናገር፡- መልካም! ይህማ በጣም አስደሳች መጽሃፍ ነው፤ አይደለም እንዴ? በማለት አድናቆቱን በመግለጥ ጥያቄ ጠይቆ ነበር፡፡ እንዲሁም ደግሞ ትክክለኛ የሆኑ ልጆች ሁሉ ወደ ወላጆቻቸው ቤት ይመለሳሉ፤ እያንዳንዳቸውም ደስ ይላቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ እውነት አይደለም ይላል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ  የመጽሃፉን ታሪክ እንዳላነበበ ይናገራል፡፡

እንዲሁም ለሌላው ሰው ነገሩን ሲያብራራለት በእውነት የትኛውንም ትልቅ ታሪክ አንብበህ ቢሆን ኖሮ በሌሎች ሰዎች ውስጥ ትልቅ እምነት በፈጠረና ነገሩን የሚያሰላስሉበትን የልብና አእምሮ ስሜታቸውን ሁሉ ለረጅም ጊዜ ይገዛና ይቆጣጠረው ነበር ይላል፡፡ የሰዎችም ታሪክና ህይወት ሁል ጊዜ ስለ አንድ ነገር ሲሆን እርሱም ስለ ሞትና ስለ ሞት አይቀሬነት ነው፡፡ ነገር ግን ስለዚህ ጉዳይ አንተም ከኔ ጋር ትስማማ እንደሆነ አላውቅም ይላል፡፡

በመቀጠል ልናውቀው የሚገባን ትልቅ ነገር ቢኖር ሞት በጣም አስጨናቂ ነገር እንደሆነና በዚህች ምድር ምንም ዓይነት ነገር ዘላለማዊ እንዳልሆነ ነው፡፡  ይሁን እንጂ ማንም ሞትን ቢጠላና ቢቃወም እንኳን ከሞትና ሞት ከሚያስከትለው የጋራ ጉዳት ማምለጥ የሚችል አይኖርም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ከኃጢኣትና ከሰው ልጆች ክፋት የተነሳ ነው፡፡ ስለዚህ የሰው ዘር ሁሉ በሚያሳዝን ሁኔታ የመከራና የጭንቀት ሸክም የበዛበትና ጥልቅ የሆነ ምህረት የሚያስፈልገው ፍጥረት ሆኖ ሊቀር ችሎአል፡፡ ከነዚህ ከባባድ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች የተነሳ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መልካም ዜና ሆኖ በመቅረብ ከዘለዓለም ጥፋትና ሞት ሊያድነንና ሊታደገን ወርቃማ መጽናናትን፤ ንጹህ ተስፋንና ለሁሉም ዓይነት ችግር ልዩ መፍትሄ ሆኖ እንደቀረበልን እንረዳለን፡፡

ሄርማን ብቪንክ የተባለ ሰው እንዳለው፡- ያለ ምንም ጥርጥር፤ የሰውን ልጆች ሁሉ የሚያጠቃልል መከራና ጭንቀት ስላጋጠመው ህዝብ ሁሉ ከላይ ከእግዚአብሄር ዘንድ ብቻ የመዳን መፍትሄ የሚያስፈልገው እንደሆነ እንዲሰማው አደረገው (2011፡ 393)፡፡[1] ይሁን እንጂ የክርስቶስ ወንጌል በሚገባ ውስጣችንን ከመረመረው በኃላ በግልጽ የሚያሳየን ትክክለኛ ችግር ቢኖር በህይወታችን ደስታ የማጣታችን መሰረታዊው ችግር ውጫዊ ወይም ቁሳዊ (ለምሳሌ፤ ሱሰኝነት፤ የጅምላ እልቂት፤ ድርቅ፤ በሽታና ሞት ብቻ) አይደለም፡፡ እንዲሁም ችግራችን ስለ ልቦናዊ (ለምሳሌ የአእምሮ መታወክ፤ ዓላማ ቢስነት፤ ጭንቀት፤ በነገር ሁሉ ግራ መጋባት እና ወሲባዊ መቃወስ) ብቻም አይደለም፡፡ እጅግ በጣም የከፋ ችግራችንም ከሰዎች ሁሉ ከመለየትና ጎደኛ/ወዳጅ በማጣት ከቤተ ሰብ ሁሉ ከመለየት ጋር የተያያዘ ማህበረ ሰባዊም ብቻ ነው ማለት አይቻልም፡፡

እንዲሁም የመልካም አስተዳደር እጦት፤ የጦርነት፤ የአምባገነንነት እና የሰላም እጦትንም ጭምር ፖለቲካዊም ብቻ ነው ማለት አይቻልም፡፡ የምጣኔ ሃብታዊና የአካባቢ አየር መዛባትን ጭምር የተፈጥሮ ቀውስም ብቻ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ነገር ግን ትልቁና ከባዱ ችግራችን ከላይ ከተዘረዘሩት ችግሮች ሁሉ በላይ ከእግዚአብሄር ጋር ካለን መልካም ካልሆነ ግንኙነት ጋር የመነጨና የተያያዘ ነው፡፡

በሌላ አባባል ትልቁና ጥልቁ ችግራችን ከውስጣችን የሚመነጭ መንፈሳዊ ችግር ነው ማለት ነው፡፡ ይህም ዓይነት ችግር የሚመነጨው ኃጢኣታችንና ከእግዚአብሄር በላይ የምንመለከታቸውን የኃጢኣታችን ውጤት የሆኑ ልዩ ልዩ ነገሮችን ተከትሎ ነው፡፡ ሁላችንም ልናውቀው እንደሚገባው ሁሉ እግዚአብሄር በቅድስናውና በፍቅሩ ወሰን የሌለው አምላክ እና የሁሉም ነገር ምንጩና ትርጉም የሚያገኝበት አምላክ ሲሆን መልካምነትም የሚመነጨው ከራሱ ነው፡፡  ስለዚህ በእግዚአብሄር ላይ በማመጻችን ምክኒያት እርሱንም አለማክበራችን ወይም መናቃችንን ብቻ ሳይሆን እኛ ራሳችን በእውነት መልካም ከሆነው ነገር ሁሉ እየራቅን ወደ ክፋትና ጥፋት እንዲሁም ወደ ዘላለም ጨለማና ወደ ልብ እውርነት እየተጠጋን እንደሆነ ነው፡፡

በስተመጨረሻም የክርስቶስ ወንጌል ከሁሉ የተሸለና ተወዳዳሪ የሌለው መልካም ዜና ሆኖ ተገልጦአል፡፡ ምክኒያቱም ሁሌም እያጋጠመን ስለሚያስጨንቀንና ስለሚያሰጋን ኃጢኣት ስለተባለው ትልቅ ችግር ስለሚናገር ነው፡፡  ይህም ችግር ሞትን የሚያስከትለው የመጨረሻው ፍርድ ነው፡፡ ምክኒያቱም እርሱ እግዚአብሄር ቅዱስ እና ጻድቅ አምላክ ስለሆነ አመጻችንና ክፉ ሥራችንን ችላ ብሎ አያልፍም፡፡

የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በውስጡ የያዘው የሰው ልጆች ከሞቱ በኃላ የሚኖራቸውን ህይወት ወይም ስለሚያገኙትን መልካም ነገር ብቻ ሳይሆን በወንጌሉ ካላመኑበት ስለሚከተላቸው ቅጣትም ጭምር ከባባድ ማስጠንቀቂያዎችን ጭምር ነው፡፡  በማቴዎስ ወንጌል 5፡29፤ ማርቆስ 9፡45 እና 47 በመጨረሻው የፍርድ ቀን ኃጢኣተኛ ሁሉ ወደ ስኦል እንደሚጣል እናነባለን፡፡ እኛ የክርስቶስ ተከታዮች ግን ከዚህ ክፉ ቅጣትና የዘላለም ፍርድ እንድናመልጥበት እግዚአብሄ ያዘጋጀልን ትልቅና አስገራሚ መንገድ አለን፡፡ ይህም መንገድ መልካም ዜና ወይም መልካም አዋጅ ተብሎ የሚታወቀው ወንጌል ነው፡፡ በዚህ ታላቅ ወንጌል የሚያምኑት ሁሉ ቢሞቱም እንኳን ከሞት በኃላ የሚቀጥል የዘላለም ህይወት ስለሚኖራቸው የመጨረሻውን ፍርድ ተከትሎ ከሚመጣው የዘላለም ሞት የመውጫ መንገድ አዘጋጅቶላቸዋል ማለት ነው፡፡

ወደንና ፈቅደን በእግዚአብሄር እውነት ላይ በማመጻችን ምክኒያት ከዲብሎስና ከሌሎችም ርኩሳን መናፍስት ጋር ከእግዚአብሄር ፊት ብቻ ሳይሆን ከመልካም ነገር ሁሉ ተለይተን እንደምንቀጣ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ይህም ጉዳይ የአዲስ ኪዳን መልእክቶችን ስናነብ በጣም ግልጽ ሆኖ ይታያል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- የዮሃንስን ወንጌል 3፡17-18 እና ቁጥር 36ን ብናነበው በማያሻማ ሁኔታ ሊገባን  ይችላል፡፡

ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሄር ወደ ዓለም አልላከውምና፡፡ በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሄር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል፡፡ በልጁ የሚያምን የዘላለም ህይወት አለው፤ በልጁ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአእግዚአብሄር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል፡፡

ስለዚህ ሁላችን ልናውቀው የሚገባን በክርስቶስ የምናገኘው ድነት ከኃጢኣት፤ ከሰይጣን፤ ከቁጣ፤ ከእርግማንና መዓት ነጻ የምንወጣበት እና ወደ እግዚአብሄር በመቅረብ በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘንበት ነገር እንደሆነ ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ ወንጌል ወደ እርሱ በመቅረብ ሰላምና እርቅን በማግኘት ከእርሱ ጋር ልዩ ግንኙነት የፈጠርንበት በልዩ ክብር የተሞላ እውነት ነው፡፡  ይህ የጸጋ ወንጌል እጅግ በጣም ታላቅና አስደናቂ ዜና ነው፡፡ ምክኒያቱም ከእግዚአብሄር ዘንድ የሆነ የተስፋን ቃል እና የኃጢኣትን ይቅርታ በማግኘት ከእግዚአብሄር ጋር ልዩ ግንኙነት እንዳለን የሚያረጋግጥ እውነት ነው፡፡ እንዲሁም ገደብ የሌለውን የእግዚአብሄርን ፍርድ ሊያስወግድልንና አዲስና አስደናቂ የሆነ መንፈሳዊ ህብረትና ግንኙነት ከእግዚአብሄር አብ ከእግዚአብሄር ወልድና ከእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ጋር ፈጥረን ወደ ተሃድሶ እንድንገባ የሚያደርግ ወንጌል ነው፡፡

በተጨማሪም ከእግዚአብሄር ጋር ብቻ ሳይሆን ህብረታችን ከሌሎች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እና ከሌሎችም ፍጥረታት ጋር የጠበቀና ጤናማ ህብረት ሊኖረን ይገባል፡፡ ይህ ወንጌል ከእግዚአብሄር ዘንድ የሚገለጠውን ቁጣና ፍርድ በሚቃረን መልኩ በኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠውን መልካም ዜናና የዳግመኛ መወለድን ተስፋ ይዞ የተገለጠ አዋጅ ስለሆነ በግል ህይወታችንም ልዩ ተሃድሶ በማግኘት ወደ ዘላለም ጽድቅና ፍጹምነት ገብተን ለዘላለም ከጌታችን ከኢየሱስ ጋር እንድንነግስ የጸና ተስፋ የሚሰጠን ወንጌል ነው (የዮሃንስ ራእይ 2፡7፤ ሉቃስ ወንጌል 23፡43 እና 2ኛ ቆሮንቶስ 12፡3)፡፡ ይህ በክርስቶስ አማካኝነት የመጣው ሰማያዊ እርቅ የማይደርስበት ሥፍራ ስለማይኖር ወደ እኛ ህይወት ብቻ ሳይሆን ወደ ሌሎችም ብዙ ሰዎች እንዲሁም ወደ ፍጥረታትም ሁሉ ህይወት ውስጥ ዘልቆ የመግባት ኃይልና አቅም ያለው እርቅ ነው፡፡

እኛም ከሚወደን ፈጣሪያችን ጋር ያለንን ግንኙነትና እርቅ የሚያረጋግጥልን እውነት ነው፡፡ እንዲህ ያለ የእርቅና የጸጋ ወንጌል የህወትን መፍትሄና የተስፋን ቃል እያወጀ የመጣ፤ የተስፋውም ቃል እጅግ የጸናና የማይለዋወጥ ታሪክዊ ሃቅ  ነው፡፡ በርግጥ የወንጌሉ ባህሪይ በጥልቀት ሲጠና በቀላሉ ልንገነዘበው የምንችለው ትምህርትና መልእክት ብቻ ሳይሆን በማይነቃነቅ መሰረት ላይ የቆመ በክርስቶስም ማንነት ላይ የተመሰረተ እውነት ነው፡፡ ይህ ወንጌል በዋናነት አረጋግጦ የሚነግረን ሃቅ ምንድር ነው ቢባል በሃዋሪያት ሥራ 23፡ 11 ላይ ስለተገለጸው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ሲሆን የመልእክቱም ጭብጥ ሃሳብ የኢየሱስን ማንነትና የእግዚአብሄር ሥራ አጉልቶ ማሳየት ነው፡፡ እነዚህም ምስክርነቶች በጣም አስፈላጊና ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን የያዙ ሲሆኑ እነርሱም ስለ ጌታችንና መድኃኒታች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፤ ስለ ህይወቱና ስለ ሞቱ እንዲሁም ሞትን አሻንፎ ስለመነሳቱ የሚናገሩ ናቸው፡፡ እንዲሁም ይሀው ወንጌል ስለ ኢየሱስ እና በእርሱም አማካኝነት ምን እንደተፈጸመ ይናገራል፡፡ ከእርሱም ድንቅ ሥራ የተነሳ የእግዚአብሄር የማዳን ኃይሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለሁሉም ህዝብ በሚሆን መልኩ በወሳኝ ሁኔታና መንገድ እንደ ተገለጠ የሚናገር  ዜና ነው፡፡ ጌታችን አየሱስ ክርስቶስ ባይሰበክ ኖሮ ወንጌል አይሰበክም ነበር፡፡ የኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በማእከላዊነት ባይሰበክ ኖሮ ትክክለኛው ኢየሱስም ባለተሰበከ ነበር፡፡ ስለዚህ ሃዋሪያው ጳውሎስ እንደተናገረው የወንጌል ስብከታችን ዋናው ማእከል ክርስቶስ ስለኃጢኣታችን ሞተ፤ ስለ ጽድቃችንም ከሙታን ተነሳ የሚል መሆን አለበት፡፡[2]  ከሁሉ በላይ ልናስተውለው የሚገባን ነገር ቢኖር በክርስቶስ ሞትና ከተቀበረበት በኃይል በመነሳቱ ምክኒያት በኃጢኣቱ ምክኒያት የዘላለም ፍርድ የሚጠብቀው የሰው ዘር ሁሉ በተለይም በክርስቶስ የሚያምኑት ሁሉ ነጻ እንደወጡ እንገነዘባለን፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄር መንግስት የመንግስቱ ንጉሥ በሆነው በክርስቶስ  አማካኝነት እንደተመሰረተና የዘላለም ህይወትም እንደነገሰ በሚገባ ልንረዳ እንችላለን፡፡

ይህ መጽሃፍ ቅዱሳዊ የምስራች ዜና ሁልጊዜ ትኩስና ለዘላለም የሚኖር አዲስ ሰበር ዜና ነው፡፡ በዚሁ ወንጌል የምስራች አዋጅ አማካኝነት በኃጢኣትና ክፋት ሁሉ ላይ ስለ ተገለጠው የእግዚአብሄር ታላቅ ድል እንማራለን፡፡ በርግጥ የወንጌል ስብከት ኢየሱስ ጌታ ነው የሚል አዋጅ ነው፡፡ ይህም አዋጅ ኢየሱስ ከሙታን ተነስቶ ወደ ላይ አረገ የሚል ነው፡፡ ይህም የሚያሳየን የኢየሱስ ታሪክ እና ሥራዎቹ በእርሱ አካላዊ ትንሳኤው ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን አሁንም ለዘላለም እየነገሰ ያለና መኖሩን የሚቀጥል ንጉሥ እንደሆነ ነው፡፡ [3]

በብዙዎች ዘንድ በአሁኑ ዓለማችን ከሁለት መቶ ቢሊን እስከ ሁለት ትሪሊየን የሚገመቱ ጋላክሲዎች እንደሚገኙ ይታሰባል፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ሰማይንና ምድርን ባጠቃለለው ሥልጣኑ ሲታሰብ ፍጥረታትን ያጠቃለለ እንጂ ስልጣኑና አገዛዙ በተወሰኑ ነገሮችና አካባቦዎች ብቻ ያልተወሰነ እንደሆነ ልንገነዘብ ይገባናል፡፡ ከሁሉም በላይ ልንረዳው የሚገባን ነገር ደግሞ ሁሉን ያጠቃለለውን የእግዚአብሄርን መንግስትና የክርስቶስን አገዛዝ የሚያውጀው የኢየሱስ ወንጌል መሆኑ ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ስለኛ ሃጢኣት መስዋእት ለመሆን መወሰኑና መሞቱ እንደ ሌሎች ሰዎች ሞት የድካምና የመሸነፍ ምልክት ሳይሆን ወደ ከፍታ ሥፍራና ሁሉን ወደሚገዛበት ዙፋኑ የሚወጣበት፤ እንዲሁም በሚታዩና በማይታዩ ኃይላትና ሥልጣናት ሁሉ ላይ የተቀዳጀውን ድል አረጋግጦ በግልጽ የሚያሳይበት መንገድ ነበር፡፡  ከዚያም አንጻር ስንመለከተው ፍጹም በሆነ አገዛዙ ከሁሉ በላይ ከፍ ብሎ በመንግስታት እና በፍጥረታት ሁሉ ላይ የነገሠ ንጉሥና የሁሉ ተቆጣጣሪ እንደሆነ እንረዳለን፡፡

እርሱ ጌታችንና ንጉሣችን ኢየሱስ የሁሉም ነገር ራስ፤ በአዲስ ፍጥረትም ሁሉ ላይ ልዕልናው ከፍ ያለ፤ ከመንግሥታትም ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉሥ ነው፡፡ 

ጌታችን ኢየሱስ ጌታና አዳኝ ከመሆኑ የተነሳ አሁንም በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ አስደናቂ የሆኑ ስራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ እነዚያም ሥራዎች 1ኛ.  በየዘመናቱ የሚነሱትን ነገሥታትና አገዛዛቸውን ሁሉ መቆጣጠርና መግዛት፡፡ 2ኛ የርሱን ተከታዮችና ወዳጆቹን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ መርዳትና መደገፍ፡፡ 3ኛ መንፈሱን ወደ ተከታዮቹ እየላከ ኃልን ማስታጠቅ፡፡ 4ኛ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለህዝቦች ሁሉ በሚዳረስ መልኩ የኃጢኣት ይቅርታና ምህረትን ሁሉም ህዝብ እንዲያገኝበት የንስሃን እድል መስጠት ነው (ሉቃስ 24፡47)፡፡ በስተመጨረሻም የዓለም ታሪክ ሁሉ ሲጠቃለል እርሱም በታላቅ ክብር ድልን ተጎናጽፎ ሲገለጥ ወንጌላዊ ማቴዎስ እንዳለው፡- ይህ የመንግስት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል…..(ማቴዎስ 24፡14)፡፡

[1] Herman Bavinck, Reformed Dogmatics: Abridged in One Volume, ed. John Bolt (Baker Academic, 2011), 393.

[2] The Gospel Coalition Confessional Statement, paragraph 6, in D. A. Carson and Timothy Keller eds., The Gospel as Center: Renewing our Faith and Reforming Our Ministry Practices (Crossway, 2012), 276.

[3] ‘The ascension is the counterpart to the incarnation as we see in passages like Philippians 2:5-11.’ Robert C. Doyle, ‘The Ascension of Jesus Christ and Present Heavenly Session,’ Unpublished Lecture Notes, 1.

አምስት ማጣፈጫዎች

ልዩ ቋንቋ

በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ “ወንጌል” የሚለው ቃል ለየት ያለ ቃል ነው፡፡ ቃሉ አጭርና ውስን ቢመስልም በብዙ መንገዶች ሊገለጹ የሚችሉ ልዩ ልዩ ሃሳቦችንና መልእክቶችን የያዘ ቃል ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- በመጀመሪያ ደረጃ በብሉይ ኪዳን ዋና እምብርት ላይ የተጠቀሱትን የድነትን ተስፋዎች ሁሉ አቅፎ በመያዝ ጉዳዩን በሚገባ ያብራራል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ በስሙ ለሚያምኑ ሁሉ ያዘጋጀውን መልካም ዜና ግልጽ አድርጎ ይነግረናል፡፡ እንዲሁም  ሰዎች ስለ ክርስቶስ የተነገረውን እውነት እና የእግዚአብሄርን የማዳን ሥራውን በሚገባ እንዲረዱ ለአድማጮች ሁሉ ግልጽ ያደርገዋል፡፡ በመጨረሻም፡- ይህ “ወንጌል” የሚለው ስም ራሱ በቀደመቺው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልዩ ሥፍራ ተሰጥቶት የኢየሱስን ታሪክና ድንቅ ሥራዎቹን መናገር ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥለውም ትውልድ ሊተላለፍ በሚችልበት ሁኔታ በአዲስ ኪዳናችን ውስጥ ተጽፎ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ “ወንጌል” የሚለው ቃል በተለየ ሁኔታና መልክ የምንረዳው ቃል ቢሆንም ለሁሉም ሰው ሊሆን በሚችል መልኩ በቀላሉ ሊገለጽ የሚችል የእግዚአብሄር መልእክት ነው፡፡

ወደ ስነ ጽሁፋዊ ትርጉም ሲመጣ “ወንጌል” የሚለው ቃል በቀጥታ ሲተረጎም “ቃል” የሚል ሲሆን በግሮክ ቋንቋ ደግሞ a logos (ሎጎስ) ይሉታል (ለምሳሌ ማርቆስ 16፡20፤ ሃዋሪያት ሥራ 13፡36፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 2፡4፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፡15 እና 17፤ እብራውያን 4፡2፤ 1ኛ ዮሃንስ 1፡5 እና 3፡11)፡፡ ይህ ሁሉ የሚያሳየን የወንጌል መልእክት በዋናነት የሚናገረው እግዚአብሄር አባቱ መለኮታዊ ቃል የሆነው ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ በሰው ልጆች መልክ በመገለጡ  የዘላለም እቅዱንና የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም የሠራውን ታላቅ ሥራ ነው (ዮሃንስ 1፡1-18)፡፡ በአጭሩ ሲጠቀለል ወንጌል በኢየሱስ ሞትና ትንሳዔ አማካኝነት የተገለጠውን የኢየሱስን የሉዓላዊ አገዛዙን ከሁሉ የበላይነት የሚገልጥ መልእክት ነው፡፡

እንደገና ደግሞ በእርግጠኝነት ልናውቀው የሚገባን እውነት ቢኖር ይህ የወንጌል እውነት ሁላችንም ከኃጢኣት የዳንንበት ታላቅና ልዩ መልእክት ነው (ሃዋሪያት ሥራ 11፡14)፡፡ ምክኒያቱም ሁላችንም ከእግዚአብሄር ጋር የታረቅንበትና የኃጥኣትን ይቅርታ ያገኘንበት ታላቅ ዜና ስለሆነ ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19)፡፡ አዲስ ኪዳን መጀመሪያ በተጻፈበት በግሪክ ቋንቋ “ወንጌል” የሚለው ቃል Euangellion (ኢቫንጀሊዮን) ተብሎ ነው የሚታወቀው፡፡ ትርጎሜውም የእግዚአብሄርን መልእክት ማወጅ ወይም ለሌሎች በስብከት መልክ ማስተላለፍ ማለት ነው፡፡ በአጭሩ ሲገለጽ በብሉይና በአዲስ ኪዳን ቋንቋ ወንጌል ማለት ዜና ወይም መልእክት ማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቃሉ ትርጉም መልካም ወይም ክፉ ዜና ተብሎ ስለሚታወቅ የቃሉን ትርጉም ለመገንዘብ አውዱ በሚገባ ግልጽ ሊሆን ያገባል፡፡ ለምሳሌ 1ኛ ነገስት 1፡42፤ ኢሳይያስ 52፡7፤ 2ኛ ሳሙለ 4፡9-10፤ ትንቢተ ኤርሚያስ 20፡15ን ስናጠናው ዜና ሁሉ መልካም ሊሆን አይችልም፡፡ ምክኒያቱም አንዳንድ ዚናዎች መልካም ሌሎች ደግሞ መጥፎም ዜናዎች ሊሆኑ ስለሚችሉ ልዩነቱን በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

መጽሃፍ ቅዱሳችን “ወንጌል” የሚለውን ቃል ሲገለጸው አዳኝ የሆነ የእግዚአበብሄር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በኃጢኣት የተበላሸችውን ዓለም ለማዳንና የፍጥረቱንም ክብር ወደ ቀደመው ሥፍራው ለመመለስ በማቀድ ዓለሙን በጽድቅና በርህራሄ ለመግዛት የገባውን ኪዳንና የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም እንደሆነ ለማሳየት ነው (ብራየን ቸፕል 2012፡116):: ስለዚህ መጽሃፍ ቅዱስ “ወንጌል” የሚለውን ቃል የሚገልጽው በብዛት መልካም ዜና ከሚል ትርጉም ጋር አያይዞ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስም በ2ኛ ቆሮንቶስ 2፡14-16 ይህንኑ ሃሳብ ሲገልጸው እኛ የምንሰብከው ወንጌል ለሚድኑት የህይወትና ለሚጠፉት ደግሞ የሞት ሽታ እንደሆነ በግልጽ ይነግረናል፡፡ ምክኒያቱም ወንጌል ለአንዳንዶች መልካም ዜና እንደሆነ ሁሉ ለሌሎች ደግሞ መጥፎ ዜና መሆኑን አንባቢ ሁሉ ሊገነዘብ ይገባል፡፡ በሌላ አጠቃቀሙ ደግሞ የአራቱ የአዲስ ኪዳናችን ወንጌሎች መጀመሪያ ላይ የማቴዎስ፤ የማርቆስ፤ የሉቃስና የዮሃንስ ወንጌል ተብለው እንደተጻፉ ደግሞ እንመለከታለን፡፡

እንዲሁም እነዚህ የወንጌሎቹ ዘገባዎች ሁሉ የሚያሳዩን ዋናው መልእክታቸው የተመሰረተውና የሚያጠነጥነው በኢየሱስ ክርስቶስ ማንነትና ሥራዎቹ ላይ እንደሆነ ነው፡፡ በርግጥ የአራቱም ወንጌሎች ዘገባዎች የሚያስረዱን ወንጌል የእግዚአብሄር ወንጌል ወይም የመንግስቱ ወንጌል እንደሆነ ሲሆን ይህ ወንጌል በኢየሱስ በራሱ የተሰበከ መልእክት እንደሆነም ነው (ማርቆስ 1፡14፤ ማቴዎስ 9፡35)፡፡ ስለዚህ በመጀመሪያ ደረጃ ልናውቀው የሚገባን ነገር፤ አንደኛ፡- የወንጌል መልእክት በኢየሱስ በራሱ ተነሳሽነት የተሰበከ እንደሆነ ነው፡፡ በኃላ ደግሞ በሃዋሪያው ጳውሎስና በሌሎችም የክርስቶስ ተከታዮች ስለ ኢየሱስ ሞት፤ ስለ መቀበሩ እና ስለ ትንሳዔው የተሰበከ እውነት ነው (ሮሜ 1፡3-4፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡1-5፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡8)፡፡ ሁለተኛ፡- ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰበከ መልእክት ነው፡፡

በጣም ጠቃሚ የሆኑ አያሌ ርእሰ-ጉዳዮች

በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ “ወንጌል” የሚለው ቃል አያሌ ጉዳዮችን የሚያጠቃልልና የብዙ ሰዎችን ስብከት ወይም አዋጅ እንድናስታውስ የሚያደርግ ቃል ነው፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ወንጌል  ሲባል ብዙ ጻሃፊዎች ብዙ ዓይነት የስነ ጽሁፍ ዘዴዎችን በመጠቀም በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የጻፉትን እውነት የሚያስታውሰን ቃል ነው፡፡ ይህንን ስንል ግን ወንጌል የሚለው ቃል በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ወይም በአዲስ ኪዳን ውስጥ ወይም በክርስትና እምነታችን ውስጥ የተጻፉትንና የተጠቀሱትን ጉዳዮች በሙሉ አጠቃልሎ ያብራራል ማለት አይደለም፡፡

ወደ ቀደመችው ቤተ ክርስቲያን የእምነት መግለጫ ስንመጣ በአጭሩ ጉዳዩ ጠቅለል ብሎ በዚህ መልክ ተቀምጦ እናያለን፡፡

          እኔ ሁሉን በሚችል፣ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ አምናለሁ፡፡

          ደግሞም በአንድ ልጁ፣

          በመንፈስ ቅዱስ በተፀነሰ፣

          ከድንግል ማርያም በተወለደ፣

          በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራን በተቀበለ፣

          በተሰቀለ፣ በሞተ እና በተቀበረ፤

          ወደ ሲዖልም በወረደ፡፡

          በሦስተኛውም ቀን ከሙታን በተነሣ፡፡

          ወደ ሰማይም በወጣ

          ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር አብ ቀኝ በተቀመጠ፣

          ከዚያም በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ በሚመለስ፣

          በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፡፡

          ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ፣

          በአንዲት ቅድስት የሐዋርያት ቤተክርስቲያን፣

          በኀጢአት ስርየት፣

          በሥጋ ትንሣኤ፣

          በዘላለም ሕይወት አምናለሁ፡፡ አሜን፡፡

የቀደመቺው ቤተ ክርስቲያን የእምነት መግለጫ በቀደሙት የክርስቶስ ሃዋሪያት ስለ መጻፉ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ ነገር ግን የእምነት/የሃይማኖት መግለጫው የእግዚአብሄርን መንፈስ ሥራና የአዲስ ኪዳንን ትምህርት አጠቃልሎ የያዘ ስለሆነ እንዲህ ተብሎ ይገለጻል፡-

መሰረታዊ የሆኑ የክርስትና እምነት ጽሁፎች ሁሉም በቀላል መጽሃፍዊ ቋንቋ ለድነታችን በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህና ሌሎችም የሃዋሪያት የሃይማኖት መግለጫዎች ስለ ሁሉም ጉዳዮች ይነግሩናል ወይም ጥያቄዎቻችንን ሁሉ ይመልሳሉ ማለት አይቻልም፡፡ ለምሳሌ በ325 ዓ.ም የተካሄደው የኒቂያው ጉባኤ የክርስቶስን መለኮታዊ ባህሪ ለመግለጽ በቂና መሰረታዊ ነገር ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የኒቂያና ኮኒስታንትኖፖል የእምነት መግለጫዎችም ስለ መንፈስ ቅዱስ ሙሉ መለኮታዊ ባህሪዩ በሚገባ አብራርቶታል ማለት ይቻላል፡፡

በ451 የተካሄደው የቻልሴዶን ጉባኤ በክርስቶስ መለኮታዊ እና ሰብዐዊ ባህሪያቱ መሃል ያለውን ግንኙነት ሲያብራራ በ8ኛ ክፍለ ዘመን የተካሄደው የአትናቴዎስ ጉባኤ ደግሞ ስለ እግዚአብሄር ሥላሴ ባህሪይ ጠንካራ አመለካከትን አቆይቶልናል፡፡[1]  በኋላ ደግሞ በተሃድሶ ወቅት የተካሄደው የእምነት መግለጫ ስለ መጽሃፍ ቅዱስ  ሥልጣን እና ስለ ኃጢኣት፤ ስለ ጸጋ፤ እና በእምነት ብቻ ስለሚገኘው ጽድቅ ጭምር በግልጽ ያስረዳናል፡፡[2] ስለ ወንጌል የሚያወሩና ዋና ዋና ሃሳቦቹንም ሊያብራሩ የሚችሉ በብዙ የሚቆጠሩ አስተያየቶችና መልእክቶች ይገኙበታል፡፡ ስካፍ የተባለ ሰው በጽሁፉ ውስጥ ያስቀመጠው ጥያቄ እንደሚያስረዳን፡- በህይወትህና በሞትህ ብቸኛው መጽናኛህ ምንድነው ለሚለው ጥያቄ መልሱ፡- በህወቴም ሆነ በሞቴ ሥጋዬም ሆነ ነፍሴ የራሴ ሳይሆን የታመነው አዳኜ  የክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡ በክቡር ደሙ የዋጀኝና የታደገኝ፤ ስለ ኃጢኣቴም መስዋእት በመሆን እዳዬን ከፍሎ ነፍሴን ከክፉ የዲያብሎስ ወጥመድና የጥፋት መንገድ የታደጋት እርሱ ነውና፡፡ ስለዚህም በመንፈስ ቅዱስ ሥራ አማካኝነት የዘላለምን ህይወት አረጋግጦልኝ፤ እኔንም ለዘላለሙ ሙሉ በሙሉ ዋስትናዬን አረጋግጦ የራሱ አድርጎኛልና’[3]

ጆን ካለቪን የተባለ የስነ መለኮት ሊቅ በሚገርም ሁኔታ፡- ማንም ሰው በንግግር አማካኝነት የወንጌልን ዜና ማቅረብ ካስፈለገው እንዲህ ባለ መንገድ ማቅረብ ይችላል አለ፡- ኢየሱስ መቶ በመቶ አምላክ ነው፡፡ እንዲሁም መቶ በመቶ ሰው ነው፡፡ በእርሱ ካላመኑ በስተቀር የሰው ልጆች ሁሉም በጣም መራራ የሆነ የዘላለም የሞት ፍርድ ይከተላቸዋል[4]

ነገር ግን ኢየሱስ ስለሚወደንና የኖረውም የሞተውም ስለኛ ኃጢኣት ሲል ነው፡፡ ከሙታን የተነሳውም ስለኛ ጽድቅ ነው፡፡ ብዙ መከራም ተቀብሎ የኃጢኣትን ይቅርታም ያረጋገጠልን እኛ ለዘላለም ጸድቀን ከእግዚአብሄር አባቱ ጋር ለዘላለም ትክክለኛ ግንኙነት እንዲኖረን ነው፡፡ እርሱ ኢየሱስ ህያው ነው፡፡ በአባቱም ቀኝ ተቀምጦ በሁሉም ዘንድ ታውቆና ታምኖ ለዘላለም በመኖር ሁሉን ይገዛልና፡፡ ከእርሱም የተነሳ ከእግዚአብሄር ጋር ልዩና አዲስ ግንኙነት ተፈጥሮልን ልዩ ደስታ እየተደሰትን  በኃይል ተሞልተን መኖሩን እንቀጥላለን፡፡

ይሁን እንጂ ህይወት በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም በጣም መልካም ነው ማለት ደግሞ ይቻላል ምክኒያቱም ሁሉን ነገር የምናደርገው እኛ ብቻችንን ሳይሆን አባታችን እግዚአብሄር በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን አማካኝነት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስላደረገልን ነው፡፡ በክርስቶስ ስንሆን ከሞት ወዲያ ሌላ አዲስ ህይወትና አዲስ ዘመን አለንና ወደዚያ ፍጹምና ብሩህ የዘላለም ህይወት አትኩረን እንለመከታለን፡፡ ሌሎችም ከኃጢኣት መንገድ ተመልሰው ወደ እግዚአብሄር እንዲቀርቡ በወንጌልም እንዲያምኑ ከዚያም አልፎ እግዚአብሄርንና መንግስቱን እንዲያገለግሉ እናሳስባለን፡፡

 ዋናው ነገር ወይም ዋናው ጉዳይ

“ወንጌል” የሚለው ቃል ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ በተመረጡና ጠንካራ ቃላት እንዲሁም ደግሞ ቀለል ባሉ እለት እለት በምንጠቀማቸው አባባሎችም ጭምር ሊገለጽ የሚችል ቃል ነው፡፡ በሌላ አባባል ይህ ቃል ሁላችን ልንረዳው በምንችልበት መንገድና ሁኔታ ሊነገርና ሊገለጽ የሚችል ቃል ነው፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ይህ ወንጌል የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም ሊሰጥ በሚችል መልኩ ብዙ ዓይነት ሃሳቦችን የሚያቅፍና በሁሉም ሰው ላይ ጠንካራ ተጽእኖ ማሳደር በሚችልበት ሁኔታ የሚገለጽ ቁም ነገሮችን ያዘለ ቃል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ መጽሃፍ ቅዱሳዊው መልካም ዜና ወይም የምሥራቹ ቃል በጣም ብዙ ምስጢሮችን ሁሉ በአንዱ ኢየሱስ በተባለው በእግዚእብሄር ልጅ ላይ በአንድነት የሚገልጽ መልእክት ነው፡፡ የክርስቲና ወንጌላችን ዋናው መልእክት የታወጀውና የተበሰረው በጌታችን በኢየሱስ በራሱ ነው፡፡ እንዲሁም እርሱ ባዘጋጃቸውና ለዓላማው መርጦ በመረጣቸው በመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች አማካኝነት ተሰብኮአል፡፡ ይህም በቀጥታ ሲጠቃለል እንዲህ ሊባል ይችላል፡- በቀላሉ ስንገልጸው ወንጌል ክርስቶስን ያውጀዋል ወይም ያስተዋውቀዋል ማለት ይቻላል (ሃዋሪያት ሥራ 8፡5)፡፡ እንዲሁም ደግሞ ወንጌል ስለ ኢየሱስ የሚነገር አዲስ አዋጅ ወይም ስብከት ነው (ሃዋሪያት ሥራ 8፡35)፡፡ ይህም አዋጅ ወይም ስብከት የእግዚብሄርን መንግስት አዋጅና ያንኑ እውነት ማስተማርን ደግሞ ያጠቃልላል (ሃዋሪያት ሥራ 28፡31)፡፡ ይህ ቃል በጥቂት ቃላት ሲገለጽ፡- ኢየሱስ ጌታ ነው (ሮሜ 10፡9፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡3)፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡3-5፤ ፊልጵስዩስ 2፡11)፤ ኢየሱስ ክርስቶስ የኛ ጌታ ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታችን (ሮሜ 1፡4) በሚሉት ቃላት ማብራራት ይቻላል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ የክርስቶስን የበላይነትና ጌትነቱን በተመለከተ መሰረታዊው ጉዳይ ቢኖር መጻህፍት እንደሚሉት እርሱ ስለ ኃጢኣታችን ሞተ ስለ ጽድቃችንም ከሙታን ተነሳ የሚል ይሆናል (1ኛ ቆሮንቶስ 5፡3-4)፡፡ ስለዚህም እግዚአብሄር በሁሉም ላይ ከፍ ያለ የእግዚአብሄር ልጅ አድርጎ አስቀመጠው (ሮሜ 1፡4)፡፡ እንዲሁም ፍጥረት ሁሉ የሚገዛለት፤ ስሙም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ካሉትና ከነበሩት ስሞች ሁሉ የበላይ እንደሆነ ተረጋግጦ ታወጀ (ፊሊጵስዩስ 2፡ 9-10)፡፡

ስለዚህ በክርስትና መልእክታችን ውስጥ በጣም ጠቃሚና የመልእክቶች ሁሉ ማጣፈጫው አጭር መልእክት ምንድነው ቢባል ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢኣት በሽታ ሁሉ መፍትሄ ለመሆን ተሰቀለ፤ ለኃጢኣታችንና ለበደላችንም መፍትሄ በመሆን ይቅርታን አወጀልን፤ በመንፈስ ቅዱስ ሥራም አማካኝነት አዲስን ልደትና የዘላለምን ህይወት ሰጠን የሚል መልእክት ነው፡፡[5]  ይህ የወንጌል መልእክት አዋጅ የሚጠይቃቸው መሰረታዊ መጠይቆች አሉ፡፡ እነርሱም በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንና በእርሱም መተማመን ንስሃም ገብቶ ለእርሱ ራስን አሳልፎ መስጠት ነው፡፡

[1] A brief introduction is Justin S. Holcombe, Know the Creeds and Councils (Zondervan, 2014).

[2] See Philip Schaff, The Creeds of Christendom, Volume 3: The Evangelical Protestant Creeds. Sixth edition (Baker, 1931/1985).

[3] Schaff, Creeds, 3:307-8.

[4] John Calvin, Institutes of the Christian Religion, 3.2.1, trans. Ford Lewis Battles (The Westminster Press, 1960), 542.

[5] J. I. Packer, Evangelism and the Sovereignty of God (IVP, 2010 [Orig. 1961]), 66.

አምስቱ ሥርዓተ-ንጥለት 

ውንጌል በመጀመሪያ ደረጃ የሚያመለክተን ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ነው፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የማዳኑ ሥራዎች ወይም ተግባሮቹ ነው፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ከአስደናቂ ሥራዎቹና ተግባሮቹ የተነሳ እንደ ጌታና ንጉሥ እርሱ ወደ ፈጸማቸው እና አሁንም እየፈጸማቸው ወደሚገኙ ሥራዎቹ ነው፡፡  አራተኛ፡- ከነዚያ ተግባራት የተነሳ ወደ ተገኙት እና እርሱም የኃጢኣተኞችን ነፍስ ከማዳኑ ጭምር ወዳሳካቸው ጥቅሞች ነው፡፡ በመጨረሻም ሰዎች ሁሉ አምነው እንዲድኑበት መንገድ ወደሚሆነው አዲስና ልዩ ወደሆነው የወንጌል መልእክት ነው፡፡

ከሁሉ በላይ “ወንጌል” የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳናችን ውስጥ በልዩ ልዩ መንገዶችና የአጻጻፍ ዘዴዎች ተተቅሶ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ በትረካና በስብከት መልክ ተቀምጦ እንመለከታለን፡፡ እንዲሁም ደግሞ የወንጌል ዘገባዎች በጸሃፊዎቹ ግለሰቦችም ሆነ በሌሎች ግለሰቦች እንደተጻፉ የህይወት ታሪኮችም በሚመስሉ ሁኔታዎች ተጽፈው እናነባለን፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ “ወንጌል” በሚለው ሃሳብ ዙሪያ የሚያጠናጥኑ አንዳንድ አስተያየቶችንና ነጥቦችን እያነሳን በአምስት ከፍለን እንመለከታለን፡፡ እነዚህ አምስቱ አስደናቂ እውነቶች በልዩ ልዩ መንገዶችና ዘዴዎች በተደጋጋሚ ተገልጸዋል፡፡ እነዚህም እውነቶች በተገቢ ሁኔታ የተጣሩ፤ የተገለጹና ይዘታቸውና ዋናው መልእክታቸውም እንደ ንጹህ የክርስቲያን መልእክት ተጠብቀው ብዙ ህዝብ ሊረዳው በሚችልበት መንገድ የተገለጹ ናቸው፡፡

ይህንን ጉዳይ በግልጽነት ለማስረዳት ሲባል መልእክቱን ውስብስብ ከሆነ አስተሳሰብ ጀምሮ ወደ ቀላል አገላለጽ ከመሄድ ይልቅ በቀላል ጀምሮ ቀስ በቀስ ወደ ከባዱ መግባት እጅግ ይጠቅማል፡፡ ስለዚህ ይህንን የመጽሃፍ ቅዱሳዊውን የወንጌል ባህሪይና ትርጉሙ በተቻለ መጠን በአጭሩ በአምስት ክፍል በመክፈል ለማብራራት መሞከር ይጠቅማል፡፡ እነዚህም ደረጃ በደረጃ ወይም ቁራጭ በቁራጭ፤ በአምስት ሃረጎች፤ በአምስት አረፍተ ነገሮች፤ በአምስት ገጾች እና በአምስት ረጃጅም ክፍሎች መግለጽ ይቻላል፡፡

አምስቱ ቃላት

የወንጌል ቅርጹና አቀማመጡ ወይም አጻጻፉ ከታች እንደተጻፈው ቀለል ባለ ሁኔታና መንገድ በማያሻማም መንገድ ተቀምጦአል ማለት ይቻላል፡፡

ለምሳሌ፡- 1. እግዚአብሄር

  1. ኃጢኣት
  2. ክርስቶስ
  3. የኃጢኣት ይቅርታ
  4. እምነት ናቸው፡፡

እነዚህን አምስቱንም ቃላት በአንድ ላይ በመውሰድ መጽሃፍ ቅዱሳዊውን የወንጌል ይዘት በግልጽና በማያሻማ መንገድ ቅርጽ አስይዞ ማስረዳት ይቻላል፡፡

አምስቱ ሃረጎች

የወንጌልን እውነት በማስፋፋቱ ረገድ ወንጌል ራሱ ስለ ምን እንደሚናገር በግልጽ ማወቅ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ወንጌል የሚናገረው፡

(1). ስለ እግዚአብሄር ባህሪያትና ከኛም ጋር ስላለው ግንኙነት ነው፡፡

(2). ስለ ኃጢኣትና ስለ ኃጢኣት ውጤቶች ነው፡፡

(3). ስለ ክርስቶስ ማንነትና ሥራዎቹ ወይም ተግባራቱ ነው፡፡

(4). በይቅርታ ላይ ስለተመሰረተው ስለ ዘላለም ድነት ነው፡፡

(5). በእምነትና ከኃጢኣት ወደ ክርስቶስ በመመለስ በእግዚአብሄርም በመተማመን ስለሚገኘው የህይወት ለውጥ ነው፡፡

አምስቱ አረፍተ ነገሮች

የወንጌል ቅርጹና ዋናው ቁም ነገሩ በሚከተሉት አምስት አረፍተ ነገሮች ሊገለጽ ይችላል፡፡

  1. ወንጌል ሙሉ በሙሉ በአዎንታዊ መንገዶች ህይወትን የመለወጥ ሃይል ያለው እውነት ሲሆን ለመፍጠር፤ ለመግዛት፤ ለመፍረድና ለማዳንም የሚችልበት ሥልጣን ያለው ከእግዚአብሄር የወጣ ቃል ነው፡፡
  2. ወንጌል ወደ ኃጢኣተኛው የሰው ልጆች ሲመጣ ድነትን ብቻ ሳይሆን የሰውን ልጅ ሁሉ በኃጢኣትቱ ምክኒያት ስለሚከተለው ፍርድም ጭምር ማስጠንቀቂያን የያዘ እውነት ነው፡፡
  3. ወንጌል በማእከላዊነት አትኩሮ የሚናገረው በኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት፤ በህይወቱ፤ በሞቱ፤ በትንሳዔው፤ በእርገቱና ዳግመኛ በመመለሱ ላይ ነው፡፡
  4. የድነት ወንጌል የሰውን ልጆች ሁሉ በኃጢኣት ይቅርታ አማካኝነት ክእዚአብሄር ጋር በመጣመር አዲስ ፍጥረት ወደ መሆን የሚያመጣና ህይወትን የማደስ አቅም ያለው እውነት ነው፡፡
  5. የሰውን ልጅ ሁሉ ወንጌል ከሚጣይቃቸው ግልጽ መጠይቆች ትቂቶቹ፤ ለእግዚአብሄር ጸጋና ምህረት ምላሽ በሚሆኑትን እምነትና ንስሃን ነው፡፡

አምስቱ አንቀጾች

  1. ስለ እግዚአብሄር

በመጀመሪያ ደረጃ ወንጌል በጥቅሉ የሚነግረን ስለ ፈጣሪያችን፤ በመልካምነቱም ብዛት ስለሚያኖረን፤ በእጆቹም መዳፍ ይዞን ስለሚጠነቀቅልን ስለ እግዚአብሄር ነው፡፡

ፈጣሪያችን እግዚአብሄር ፈጣሪ ብቻ ሳይሆን ከፍጥረቱ ጋር ግልጽ የሆነ ግንኙነት ማድረግ የሚችል አምላክም ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል መልካሙ የምስራች ዜና ራሱ ቃሉ ከሚገለጥባቸው መንገዶች አንዱ የሆነ የግንኙነት መንገድ ነው፡፡ ወንጌል ወይም የምስርቹ ቃል መሰረታዊውና ዋናው መልእክቱ እግዚአብሄር ራሱ ከኛና ከሌሎችም ፍጥረታት ጋር ለግንኙነት አቅዶ ያወጣው መንገድ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ወይም የእግዚአብሄር ንግግር በራሱ መንገድና ዘዴ እንደ ራሱ ድንቅ ሥራና የግንኙነት መሳሪያ የሚጠቀምበት ነገር ነው፡፡

በርግጥ ስለ እግዚአብሄር ማንነትና ባህሪያቱ ማወቅ ካስፈለገ በቃል መነጋገር በጣም ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ በዮሃንስ ወንጌል ውስጥ እንደምናነበው በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃሉም በእግዚአብሄር ዘንድ ነበረ ቃሉም እግዚአብሄር ነበረ ይላል (ዮሃንስ ወንጌል 1፡1)፡፡ እንዲሁም ገና መጽሃፍ ቅዱሳችን የሚጀምረው እግዚአብሄር ዓለምን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣው በመናገር ወይም በቃሉ ነበረ (ዘፍጥረት 1፡1)፡፡ ገና ከመጀመሪያው “በመጀመሪያ” (ዘፍጥረት 1፡1) እና “እግዚአብሄር ፈጠረ” በማለት ሲናገር እግዚአብሄር የመፍጠር ሥራውን ሲጀምር የእርሱ ንግግር ወይም ቃል በጣም አስፈላጊ ነገር እንደነበረ ያሳያል፡፡ እንዲሁም፤ ንግግሩ ግልጽ፤ የማያሻማ፤ ሊረዱትም የማይከብድ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ስለዚህም በጽሁፍ መልክ ተዘግቦ እንደ መጽሃፍ ቅዱስም ተጠርዞ ሊቀርብልን ቻለ ማለት ነው፡፡ በዚያም ዓይነት መልክ በልዩ ልዩ ታሪኮች ውስጥ በማለፍ እግዚአብሄር መናገሩን ቀጥሎአል ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህም ነው የብሉያና የአዲስ ኪዳን መጻህፍት ተብለው በመለኮታዊ ኃይልና ሥልጣን የተሞሉ ወንጌሎችን የያዙት፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄር ወንጌል መጽሃፍ ቅዱሳዊ ወንጌል ነው ማለት ነው፡፡ ይህም ወንጌል አስቀድሞ በነቢያት ትንቢቶች የተተነበየ (ሮሜ 1፡2) እና መጻህፍት እንደሚሉት በኢየሱስና በሃዋሪያቱም አገልግሎት ወደ ሌሎች ሁሉ የተላለፈና አዲስ ኪዳንና ብሉይ ኪዳን ተብሎ የተጠበቀ ነገር ሆነ (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡1-11)፡፡

በመጽሃፍ ቅዱሳችን እግዚአብሄር ብዙ ነገሮችን ተናግሮአል፡፡ ዓለሙንም የኛ መኖሪያ አድርጎታል፡፡ እኛንም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወዶናል፡፡ ከእርሱና ከሌሎችም ሰዎች እንዲሁም ፍጥረታት ሁሉ ጋር በስምምነት እንድንኖር አድርጎናል፡፡ ይህንንም ሁሉ ያደረገበት ምክኒያት እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንድንጠቀምና እንድንደሰትበተ ብሎም እርሱን እንድናገለግልበት እንድናመልክበትም ጭምር ነው፡፡ ምክኒያቱም እርሱ ፈጣሪያችንና በፍጹም መልካምነቱ የራሱ ያደረገን ራሱ ነውና፡፡ እኛ የእርሱ ነን፡፡ የያዝነውና የጨበጥነውም ነገር ሁሉ የራሳችን ሳይሆን የእርሱ ነው፡፡ ስለዚህ የሰው ልጆች ሁሉም በዚህ ምድር ላይ የሚኖሩት የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግና መልካሙን ነገር ሁሉ በማድረግ ፈቃዱን ለመፈጸም ነው፡፡

የእያንዳንዱ የሰው ልጅ ህይወት የተለያ ዓላማና ትርጉም ያለው ነው፡፡ ምክኒያቱም በመጀመሪያ ደረጃ እግዚአብሄር የፈጠረን ለራሱ ዓላማ ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ እርስ በርሳችን እንድንጠቃቀም ወይም እንድንደጋገፍ ነው፡፡ ስለዚህ ለእግዚአብሄር ዓላማ ካልኖርን ህይወታችን ሁሉ ባዶና ከጥቅም ውጪ የሆነ ትርጉመ-ቢስ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ከዚያም አልፎ በሚያስደንቅ ሁኔታ በአደጋ ላይ እንዳለን ልናውቅ ይገባናል፡፡ እግዚአብሄር ሲፈጥረን ወደ ራሱ የሳበን እረፍት የለሽ የሆነ ልባችንን በራሱ ለማሳረፍም ነበር፡፡ እንደ ፈራጃና አዳኝ እግዚአብሄር ፍጥረትን ሁሉ ጠቅልሎ ይገዛል፡፡ ወንጌላችንም እንደሚነግረን እግዚአብሄር ኃጢኣተኛውን የሰውን ልጅ በሰዎች ቃላት ድምጹን ከፍ አድርጎ ይጠራዋል፤ በጸጋውም ኃይል ወደ ራሱ ይጋብዘዋል፡፡ ይህንንም ሥራ የሚሰራው የሰውን ልጆች እንደ አምባሳደር በመጠቀም መልእክቱን በመጽሃፍ ቅዱስ ቃላት ግልጽ አድርጎ በመናገር ነው፡፡ ለምሳሌ አስተማሪዎችን፤ ሰባኪዎችን፤ መጋቢዎችንና ወንጌላውያንንም በመጠቀም የእግዚአብሄርን መልእክት ግልጽ በሆነ ቋንቋ እንዲያስተላልፉ ያደርጋል፡፡

  1. ስለ ኃጢኣት

በሁለተኛ ደረጃ ወንጌል ስለ ኃጢኣትና በኃጢኣት ምክኒያት ስለሚከተሉት የኃጢኣት ውጤቶች በግልጽ ይነግረናል፡፡ ኃጢኣት በመሰረቱ የተጀመረው በሰው ልጆች ውስጥ ሳይሆን በዲያብሎስ አእምሮ እና ልብ ውስጥ ነው፡፡ በርግጥ ኃጢኣት ወደ ዓለም የገባው በአዳምና ሄዋን ለእግዚአብሄር ባለመታዘዝ ምክኒት እንደነበረ ግልጽ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጥፋቱ የአዳምና የሄዋን ብቻ ነው ማለት አያስደፍርም፡፡ ምክኒያቱም እነዚህ ባልና ሚስት የእግዚአብሄርን ህግ በመጣስ ህጉንም ባለመጠበቃቸው ወድቀዋልና፡፡  ከዚያም የተነሳ ከፈጣሪያቸው ከእግዚአብሄር ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሁሉ ፈርሶ እርስ በርሳቸውም ግንኙነታቸው ሊሻክር ችሎአል፡፡ ስለዚህ ላጠፉት ጥፋት ራሳቸው እንጂ አንዱ ስለ ሌላው ሊጠየቁ አይገባም፡፡ ሁሉም ለየራሱ ኃጢኣት ሊጠየቅና ሃላፊነቱን ሊወስድ ይገባዋል፡፡ ምክኒያቱም እያንዳንዱ ሰው በኃጢኣት ምክኒያት ተበላሽቶ ፍጹም ከሆነው ከእግዚአብሄር ፍርድ በታች ወድቆአልና፡፡ ከኃጢኣቱም የተነሳ ምንም ዓይነት መልካምና ትክክለኛ ሥራ መስራት የሚችልበት አቅሙ ከድቶታልና፡፡[1]. እንዲህ ያለ ሰው ከእግዚአብሄርም ተለይቶና በጠላትነት ተፈርጆ ያለ ምንም ረዳት በመቅረት ተስፋቢሰ ሆኖ ከመለኮታዊ ፍርድ የማያመልጥ ሆኖ ይቀራል፡፡ ምክኒያቱም በእግዚአብሄር ፊት የሠራነው ኃጢኣት  ፍርድንና ኩነኔን ማስከተሉ አይቀሬ ነውና፡፡ ያ ብቻም አይደለም፡፡ ከክርስቶስ ተለይቶ ለሚኖር ሰው ኃጢኣት በቀጥታ ሰይጣናዊ ተግባርና በክፉ ኃይል አስሮ የሚያስቀር ኃይለኛ ወጥመድ ነውና፡፡ በሌላ አባባል ኃጢኣት፤ ክፋት ሁሉ የሚወጣበት የክፋት ሁሉ ምንጭ ነውና፡፡ ይሁን እንጂ የሰውን ህይወት ጭምር ሁሉንም ነገር የመረዘውንና ያበላሸውን የኃጢኣትን ክፋት ሊያዳምና ሊያስወግድ የሚችለው የእግዚአብሄር ምህረት ብቻ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ቅድስና፤ ፍቅሩ እና የጽድቅ ሥራው ካለፈው፤ አሁንም ካለውና ከሚመጣው የእግዚአብሄር ፍርድና ቁጣ ሊታደገን የሚችል ሲሆን፤ የእግዚአብሄር ባህሪዩና ሥራውም ፍቅርና ጽድቅ ነው፡፡ ፍጹም የሆነው የእግዚአብሄር መልካምነት የሚገለጠው ክፋትን በመቃወሙና በመጥላቱ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡  

ታሪክ ሁሉ ወደ መጨረሻው በሚደርስበት እና እግዚአብሄርም ሁሉን ነገር ያላማዳላት በትክክለኛው ቦታ በሚያስቀምጥበት ቀን በራሱ እውቀት የተመሰረተ ፍርድ ይከናወናል፡፡ የፍጥረታቱም ሁሉ የሰዎችና የመላእክቱን ጭምር ግላዊ፤ ማህበራዊና መንፈሳዊ ህይወቱም እድሉ በእግዚአብሄር እውነተኛ ፍርድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ ሁል ጊዜ የእግዚአብሄር ፍርድ የሚመሰረተው ሰዎች ከእግዚአብሄር ጋር በሚኖራቸው መልካም ግንኙነትና ለወንጌል እውነት በሚኖራቸው ፍጹም መታዘዝ ላይ ነው፡፡ በሌላ አባባል ከእግዚአብሄር ቁጣና ከመጨረሻው ፍርድ ለማምለጥ የሚፈልግ ሰው ሁሉ ለወንጌል እውነት በመታዘዝ በክርስቶስ ማመንና መተማመን አለበት ማለት ነው፡፡ የመጨረሻውም የእግዚአብሄር ፍርድና ውሳኔው በግለሰቦች ላይ ሲተላለፍ ወደ መንግስተ ሰማይ ወይም ወደ ሥኦል እንዲገቡ የሚያደርገው ውሳኔው የሚተላለፈው የወንጌሉን እውነት ተቀብለን በክርስቶስ በማመናችንና ባለማመናችን ላይ ተመስርቶ ነው ማለት ነው፡፡ ክፋት ሁሉ ይገረሰሳል፤ ኃጢኣትም ይወገዳል፤ የስህተት ሥራም ሁሉ ቅጣቱን ያገኛል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ጽድቅ ይገለጣል፤ በእግዚአብሄር ምህረትም ልዩ የህይወት ተሃድሶ ይመጣል፡፡ የእግዚአብሄርም መንግስት ወደ ዘላለማዊው ፍጹምነት ወደ ፊት ይገሰግሳል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሄር ፍርድ በጥብቅ የሚያሳየን ስለኃጢኣታችንና ስለ በደላችን ሃላፊነቱና ተጠያቂነቱ የራሳችን እንጂ የማንም እንዳልሆነ ነው፡፡ ምክኒያቱም እውነተኛው የእግዚአብሄር ፍርድ በኃጢኣትና በደል ሁሉ ላይ መገለጡ አይቀሬ ነውና፡፡ ፍጹም በሆነው በእግዚአብሄር ጥበብና እውቀት ላይ የተመሰረተ እግዚአብሄር ፍርድ በመጨረሻው ቀን ሁሉን ትክክል በሆነ መልኩ ቦታ ቦታ ያስይዛል ማለት ነው፡፡

እስራኤልን ከግብጻውያን ባርነት ከማዳኑና ከመታደጉ የተነሳ እግዚአብሄር እውርነትና የጭካኔን አገዛዝ ለማስወገድ ብቻ ሳይሆን ህዝቡ ከራሱ ጋር የነበረውን መልካም ግንኙነት ለማደስም የሚጠቅም ፍርድ አምጥቶ እንደነበረ እንመለከታለን (ዘጸኣት 2፡23-25፤ 5፡1-2፤ 6፡1-13፤ 7፡5፤ 12፡29-32፤ 14፡1-4)፡፡ የእግዚአብሄር የፍርዱ ሁኔታ ሲታይ አሁናዊ በሆነ ታሪክ ውስጥ እና ወሳኝ በሆነው በመጨረሻውም የፍርድ ቀን እንደሆነ እንመለከታለን (ሃዋሪያት ሥራ 17፡31)፡፡ ይህም የፍርዱ ሁኔታ የሚከናወነው በታላቁና በነጩ ዙፋን ላይ በሚቀመጠው በእግዚአብሄር በራሱ አማካኝነው ነው (የዮሃንስ ራእይ 20፡11-15)[2] ስለዚህ ግልጽ የሆነው የወንጌል እውነት እንዴት ይታወጃል ቢባል ንስሃ ለሚገቡት ሁሉ የኃጢኣት ይቅርታ በመስጠት ሲሆን በንስሃ በማይመለሱት ላይ ደግሞ ኩነኔን በማወጅ ነው ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል፡ የእግዚአብሄር ፍርድ ሲታወጅ ሁለት ነገሮችን ያጠቃልላል፡፡ እነርሱም፡- አንደኛ፤ በእርሱ ለሚያምኑት በኃጢኣት ይቅርታ አማካኝነት ወደ ገነት እና ወደ ዘላለሙ የእግዚአብሄር መንግስት መምራት ሲሆን፤ ሁለተኛ ደግሞ፤ በክርስቶስ ለማያምኑት የእግዚአብሄር መንግስት ተዘግቶባቸው ከመልካም ነገር ሁሉ ተለይተው የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሄርም ፊት ርቀው ይፈረድባቸዋል (2ኛ ተሰሎንቄ 1፡9)፡፡   

  1. ስለ ክርስቶስ

በሶስተኛ ደረጃ ወንጌል ስለ ክርስቶስ ማንነትና ድንቅ ስለሆኑት ሥራዎቹ ይነግረናል፡፡ በሌላ አባባል ወንጌል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ማንነቱ ብቻ ሳይሆን ስለ ሰራቸው እና ወደፊትም ስለሚሰራቸው ታላላቅ ሥራዎቹ በግልጽ ይናገራል፡፡ እንዲሁም ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሉ አምላክና የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነ እና ሙሉ በሙሉ ከሰማይ የወረደ የእግዚአብሄርንም ፍጹም ፍቅር ተላብሶ የተገለጠ በህወቱና በአገልግሎቱ፤ በሞቱና በትንሳዔውም አማካኝነት ሰብኣዊ የሰው ልጅም ሆኖ የተገለጠ እንደሆነ በግልጽ ይናገራል፡፡ ስለዚህም ፍጹም የሆነ የእግዚአብሄርን ባህሪይ ለሰው ልጅ ሁሉ የገለጠ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ለኛ የተገባውንም ፍርድ በስቃዩና በሞቱ አማካኝነት በራሱ ላይ በመውሰድ ስለ በደላችንም ደቅቆ እዳችንን በመክፈል ከሞት እንደታደገን እንረዳለን፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በብዙ ስቃይ ውስጥ አልፎ በኛ ፈንታ እንደ ሞተ፤ እንደ ተነሳበትና አሁንም በአባቱ ዙፋን ላይ በቀኙ ከፍ ብሎ እንደ ተመቀመጠ፤ አንደ ነገስታት ንጉሥና እንደ ጌቶቹ ጌታ ከሁሉም በላይ ከፍ ብሎ በመንገስ ላይ እንዳለ እናምናለን፡፡ ይሀው ጌታ ደግሞ  አንድ ቀን በታላቅ ክብርና በሚያስደንቅ ሁኔታ ዳግመኛ ተመልሶ ሊፈርድና ሊያድን እንደሚችልም እርግጠኞች ነን፡፡ ስለዚህ ይህ የምስራቹ ዜና ይህንኑ እውነትና የተደረጉ ነገሮችን በአንድ ላይ በመጠቅላል እና ልዩ ትርጉምም በመስጠት የኢየሱስን የሞቱን፤ የትንሳዔውንና የንግስናውን ታሪክ ሁሉ ጠቅልሎ ያስረዳናል ማለት ነው፡፡

እነዚህ ነገሮች ሁሉ በግልጽ የሚነግሩን እኛ ሁላችን የሰዎችን ህይወት፤ በምድር ላይ የመኖራቸውንም ዓላማ ከክርስቶስ መለኮታዊ ሥራዎቹ አንጻር እንድንረዳውና ክርስቶስም በሥራዎቹ ምን እንዳደረገልን በሚገባ እንድንገነዘብ ነው፡፡ ግልጹን ለመናገር ያህል የወንጌል መልእክት ማለት ስለ ክርስቶስ መለኮታዊ ማንነቱና ሰብዊ ማንነቱ ከሚያስተምረው ትምህርት በተጨማሪ ስለ ሥራዎቹም የሚያሳስብ መልእክት ነው፡፡ በሌላ አባባል ደግሞ ወንጌል የኢየሱስን መለኮታዊና ሰብአዊ ማንነቱን በአንድ ላይ በማጣመር የማስታረቅ ተግባሩንም በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ እውነት ነው፡፡ ወንጌል የክርስቶስን ማንነትና ባህሪያቱን ከመቤዠትና ከማዳን ሥራው ለይቶ አይገልጸውም፡፡ ወንጌል ሦስት ዓይነት በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሃሳቦችን ለይቶ እና ግልጽ አድርጎ ያስተምረናል፡፡ እነዚያም፡ 1ኛ፡ የክርስቶስ ሥጋ መሆን ወይም ሥጋ መልበስ (ትስብእት) ሲሆን የእግዚአብሄር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ለብሶ በመገለጥ ወደ ሰዎች ህይወትም በመግባት ሰው እንደሆነና የዓለምን ኃጢኣተኞችም እንደታደገ ያሳየናል (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡15)፡፡ 2ኛ ደግሞ የመዋጀት ሥራው ነው፡፡ ይህም የሚያሳየን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የምድር ላይ አገልግሎቱ ራሱን ስለ ኃጢኣተኞች ሲል በመስዋት መሞቱንና ትንሳኤውን እንደሚያጠቃልል ይነግረናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በስቅላት ቅጣት መሞቱ የዓለምን ኃጢኣት ለማስወገድ መስዋእት መሆኑን የሚያሳይ ሥራው ነው፡፡ ሦሥተኛው ትንሳኤው ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መነሳቱና በሰማያት ባለው በአባቱ ቀኝ በክብር መቀመጡ አዳኝነቱንና ፈራጅነቱን የሚያሳይ ታላቅ ተግባሩ ነው፡፡ ኃጢኣታችንና በደላችንን በሚያስወግደው እና ቅጣታችንንም ተቀጥቶ ነጻ በሚያወጣን በክርስቶስ ሞትና ትንሳዔ አማካኝነት ህያው ጌታና ንሥስ መሆኑ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጌትነቱ ለሁሉም ታውጆአል ማለት ነው፡፡

ይህ ሁሉ ከተባለ በኃላ ስለዚሁ ጉዳይ ሲናገሩ ጄ. አይ ፓከር የተባሉ ሰው እንዳሉት፡ የክርስቶስ የመዋጀት አገልግሎቱ መተኪያ የማይገኝለት እርግጠኛ የሆነ የማዳን ተግባሩ ነው፡፡ የሚያድነውም ህያው የሆነ ክርስቶስ ነው እንጂ ስለ እርሱ የሚነገረው ተረት አይደለም፡፡ የናዝሬቱ ኢየሱስን እንደ ዘላለም አምላክ እና ህያው ጌታ አድርገን በግልጽ ካላወቅነው ፈጽሞም አላወቅነውም ማለት ነው፡፡ የህማማቱንም ታሪክ የሰውን ልጆች ሁሉ ኃጢኣት የሚያሰወግድበት መንገድ እንደሆነ ካላወቅነው ምንም አላወቅንም ማለት ነው፡፡ ስለዚህም እግዚአብሄርን በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ከፍ ያለ ንጉስ እንደሆነ በሚገባ ተረድተን ልንቀርበው አንችልም ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ጉዳይ በሚገባ እስከምናውቅ ድረስ ክርስቶስ ስለኛ ምን እንዳደረገልን ትርጉሙም አልገባንም ማለት ስለሚሆን እውነቱን በሚገባ ተረድተን ትርጉም በሚሰጥ መንገድ ልናመልከው ይገባናል፡፡

4ኛ፡ ስለ ድነት

በአራተኛ ደረጃ ወንጌል ስለ ኃጢኣት ይቅርታ እና ስለ ዘላለም ህይወት ይናገራል፡፡ እንደ ኃጢኣተኛ ፍጥረታት  ሁላችንም በእግዚአብሄር ፊት በደለኞች ስለሆንን የእግዚአብሄር ቁጣ ሊመጣብን የተገባ ሰዎች ነን፡፡ ምክኒቱም እርሱ ቅዱስ፤ ቀናተኛና ጻድቅ ሲሆን እኛ ደግሞ በኃጢኣት ብዛት የተበላሸን ፍጥረታት ነንና፡፡ እርሱ እግዚአብሄር ግን የኃጢኣት ይቅርታን በማወጅ ኃጢኣተኞችን ወደ መንግስቱ የሚያመጣበት መንገድ አለው፡፡ የኃጢኣትም ይቅርታ ለሁላችን ሊታወጅ የቻለው  በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥቃይ፤ ሞቱና ከሙታን በመነሳቱ ነው (ሉቃስ 24፡46-47፤ ሃዊሪያት ሥራ 10፡38-43)፡፡ ስለዚህ ከእውነተኛ የኃጢኣት ይቅርታ አማካኝነት መልካም የሆነ የድነት እውቀት ይገኛል ማለት ነው፡፡ ምክኒያቱም እግዚአብሄር አምላካችን ሩህሩህና መሃሪ አምላክ ነውና (ሉቃስ 1፡77-78)፡፡ የኃጢኣት ይቅርታም ያስፈለገበት ምክኒያት ሁላችንም መሰረታዊ የሆነ ስህተት በማድረግ ወይም በመፈጸም ከእግዚአብሄር መንግስት ርቀን ጠላቶቹ ስለሆንን ወደ ተሃድሶ በመምጣት ከእግዚአብሄር ጋር ወደ እርቅ መምጣት ስለነበረብን ነው፡፡ እግዚአብሄርም ይቅር ሲለን ሙሉ በሙሉ አዲስ የሆነ የህይወት ጅማሮ ይሆንልናል፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እና በክርስቶስም በሞቱና የትንሳዔው ኃይል አዲስ ወይም እንደገና መወለድ ይሆንልናል፡፡ ይህም በአዲስ ኪዳናችን ውስጥ አዲስ መወለድ ወይም ልደት የሚባለው ከተፈጥሮአዊ ወይም በሥጋ ከመወለድ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ የአዲስ ልደት ጽንሰ-ሃሳቡ የሚመጣው ዮሃንስ በወንጌሉ እንደሚነግረን በእግዚአብሄር መለኮታዊ አሰራሩ ላይ ብቻ ተመስርቶ ነው (የዮሃንስ ወንጌል 1፡13)፡፡ ይህም ዓይነቱ ልደት ትልቅ የውስጣዊ ሰውነትን መለወጥና መታደስን የሚጠይቅ ከእግዚአብሄር ልብ ውስጥ የሚመነጭ ነገር ነው፡፡

እግዚአብሄር አዲስን ህይወት በሰዎች ውስጥ ይፈጥራል፡፡ አዲስ ባህሪይንም ከአዲስ እምነትና አዲስ ምኞች ጋር ይሰጣል፡፡ እንደ አዲስ ማንነትና አዲስ ቤተ ሰብም  ፈጥሮ ከራሱ ጋር አዲስ ግንኙነት እንዲፈጥሩ በማድረግ ለአዲስ ዓላማና ግብም ይጠቀማል፡፡ ይህንን ዓላማ እግዚአብሄር ሲያከናውን መጀመሪያ እንዴት እንደሆነ ቶሎ ላይገባን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ልዑል እግዚአብሄር ለራሱ አዲስ ዓላማና አዲስ ግብ በአዲስ ተስፋ ልዩ ትርጉም በሚሰጥ ሁኔታ ሁሉን ገደብ በሌለው ሁኔታ ያድሰዋል፡፡ በዮሃንስ ወንጌል 1፡13 ላይ የምንመለከተው የእግዚአብሄርን አስደናቂና አስገራሚ መለኮታዊ እርምጃ ስለሆነ እኛንም እንደገና ልጆቹ አድርጎ ወለደን ማለት ነው፡፡ በወንጌሉ ውስጥ እንደምንመለከተው እኛን እንደገና በመውለዱና የራሱ የዘላለም ልጆቹ በማድረግ ወደ ፍቅሩና ወደ ጸጋው ዙፋን ፊት በማምጣት ለዘላለሙ አባታችን ለመሆን ፈቃደኛ ሆነ ማለት ነው፡፡

ይሀው የዳግመኛ መወለድ እውነት በሃዋሪያው ጳውሎስ ንግግር ከድነታችን ጋር ሰለተፈጠረው ለውጥ አዲስ ፍጥረት በማለት ይነግረናል፡፡ ምክኒቱም በዘፍጥረት 3፡1-19 እንደምናነበው በአዳምና ሄዋን የአመጽ ሥራ የተነሳ ተበላሽቶ የነበረው ግንኙነታችን  በአዲሱ አዳም በክርስቶስ ሥራ አማካኝነት ወደ ልዩ ተሃድሶ ተለውጦአልና፡፡ በአዳምና በሄዋነን አመጽ ምክኒያት የተፈጠሩትን ሦሥት ዓይነት ትላልቅ ችግሮችን እንመለከታለን፡፡ እነዚያም 1ኛ፡- በኛና በእግዚአብሄር አምላካችን መሃል የነበረው ግንኙነታችን ሙሉ በሙሉ መበላሸቱና እኛም ከፊቱ መወገዳችን፡፡ 2ኛ፡- እንደ ሰው ልጆች እርስ በርሳችን የነበረን ግንኙነትም ተበላሽቶ እርስ በርሳችን አንዳችን ከሌላች ለመብለጥና ዋናውን የክብር ሥፍራ ለመያዝ የምንጨነቅና ሌላውን ሁሉ ጥለን በማለፍ የራሳችንን ልዕልና ለማስመስከር መሽቀዳደማችን፡፡ በሦሥተኛ ደረጃ ላይ ደግሞ አሁን በዚህ ዘመን የምንደሰተው ደስታ ቁሳዊና በብዙ መከራና ትግል የተሞላ ደስታ ሲሆን በመረሻም በሞት የሚጠቀለል ነው፡፡   ነገር ግን በ2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17 እንደምናነበው በክርስቶስ ፍጥረት ሁሉ አዲስ ይሆናል፡፡ ይህም የፍጥረት ሁሉ የመታደሱ ጉዳይ ወደፊት የሚሆን ቢሆንም እንኳን ያው ተሃድሶ በክርስቶስ በሆኑት አሁንም ጀምሮአል ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህ እኛም በክርስቶስ ሆነን እግዚአብሄርን አባታችን ብለን እንጠራዋለን፡፡ እንዲሁም እርስ በርሳችን ወንድሞችና እህቶች ተባብለን እንጠራራለን (ገላቲ 6፡1-16፤ ኤፌሶን 2፡11,22)፡፡ ስለዚህም በክርስቶስ አዲስ ፍጥረታት የሆንን ሁላችንም ቁሳዊው ዓለም ከከንቱነትና ከመበስበስ ነጻ የሚሆንበትን ቀን በናፍቆት እንጠባበቃለን (ሮሜ 8-18-25)፡፡ በመጨረሻም ቀን የፍጥረትን ሁሉ ሙሉ በሙሉ መታደስና መገለጥ እናያለን፡፡ በሉቃስ 1፡31-33 እንደምናነበው ማሪያምም እንደተነገራት ኢየሱስ የልዑል አምላክ ልጅ የተባለው ይህንኑ የእግዚአብሄርን መንግስት ስለሚያመጣው ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ሰዎች በሚገባ ማየት ባይችሉም በአባቱ ፈንታ ሁሉን እየገዛ ያለው እርሱ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ክርስቶስ ከመላእክቱ ጋር በሙሉ ክብሩ በሚመለስበት ቀን ህዝቦችም ሁሉ በፊቱ ሲሰበሰቡ (ማቴዎስ 25፡31-32) የሚሆነውን ሁለት ነገሮች እንመለከታለን፡፡ ከነዚም ነገሮች አንዱ ሁሉም ኃጢኣትን እንደሰሩ ሁሉ ክርስቶስን ባይቀበሉና ንስሃም ባይገቡ በሰሩት ኃጢኣት ልክ እንዲሁም በእግዚአብሄርም ቅድስናው ልክ እርሱ ይፈርድባቸዋል፤ ይቀታቸአውማል፡፡ ዲብሎስና ተከታዮቹም ሁሉ ከነሥራቸው በእሳት ባህር ይጣላሉ (ማቴዎስ 25፡31-46)፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በኃጢኣት ምክኒያት የተበላሹት ሰማይና ምድር ደግሞ ያልፋሉ፡፡ በዚያም ጊዜ እግዚአብሄር በቀጥታ መጥቶ በኛ በህዝቡ መሃል ያድራል፡፡ ሁሉንም ነገር አዲስ ደርጋል፡፡ ከእያንዳንዱም የህዝቡ ዓይኖች እንባን ያብሳል፡፡ ኃጢኣትና ሞትን የህዝቡንም ሥቃይና ልቅሶም ሁሉ ያስወግዳል፡፡ የቀደሙት ወይም አሮጌ ነገሮች ሁሉ አልፈዋልና (ራእይ 21፡4)፡፡ ሃዋሪው ጳውሎስም እንደተናገረው ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ሲመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ፡፡ የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሄርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና… (ሮሜ 8፡18-25)፡፡ ከኛ ጋር በመሆኑ በምድር ላይ የሚኖረውም ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሄርን ክብር፤ ደስታን  እና ከመከራ ሁሉ ነጻ መሆንን ይናፍቃል፡፡

5ኛ ስለ መለወጥ

በአምስተኛ ደረጃ ወንጌል የሚነግረን ከኢየሱስ ክርስቶስ የእውነት ቃል የተነሳ በሙሉ ልባችን፤ በእምነትና በንስሃ ጌታን ለመከተል እና ለማገልገል ቆርጠን ወደእርሱ ዓላማ ለመለወጥ መወሰናችንን የሚያሳይ ነገር ነው፡፡ በአጭር ቃል ወንጌል ስለ እውነቱ አምነን መቀበላችንን ብቻ ሳይሆን ያንኑ የወንጌልን እውነት ለሌሎች መስበክንና አዋጅ እየነገርን ወደ ክርስቶስ መጥራትንም ያጠቃልላል (የዮሃንስ ወንጌል 3፡16)፡፡ ስለዚህ እንደ ልዩ ጌታና አዳኝ ራሳችንን ለክርስቶስ እና ለዓላማው ሙሉ በሙሉ በማስረከብ በእርሱም ልንተማመንና ፈቃዱን ለማድረግ መስማማታችንን በግልጽ ማወጅ አለብን ማለት ነው፡፡ ይህም ዓላማ  የሚጠይቀንን ምንም ዓይነት ዋጋ ለመክፈል በሙሉ ልባችንና በሙሉ ቆራጥነት ልንዘጋጅ ይገባናል፡፡ እንዲሁም ጄ አይ ፓከር እንዳሉት፡-

የወንጌል መልእክት እንደሚነግረን እምነት ማለት ክርስቶስ በገባልን የተስፋ ቃሎቹ መሰረት ራሳችንን ሙሉ በሙሉ በእርሱ ላይ መጣል ማለት ነው፡፡ ንስሃም ማለት ልባችንና አስተሳሰባችን ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስቶስ አዲስ ህይወት ለመወጥና ለራሳችን ምኞትና ፈቃድ ሞተን ለእርሱና ለፈቃዱ በመገዛት ለአዳኙ ክርስቶስ እንደ ንጉሳችን ለመገዛት መወሰን ማለት ነው፡፡ ደቀ መዝሙርነትም ማለት ራሳችንን ከከበረው ጌታና ንጉስ ከክርስቶስ ጋር በማጣመር እርሱንም በሚገባ በመከተል ትምህርቶቹን ሁሉ ለመማር መወሰንና ለእርሱም ሙሉ በሙሉ መታዘዝ ማለት ነው፡፡

አምስቱ ገጾች

መቅድም ወይም ዋዜማ

የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አዲስና አዲስ መልካም ዜና ነው፡፡ ይህ የእርሱ ዜና ከሁሉም ዜናዎች የተለየ፤ የተሸለ እና የሰው ዘር ሁሉ ሰምቶት የማያውቀው ስለሆነ በተለየ ሁኔታ አዲስ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እንዲሁም እግዚአብሄርን ለማወቅ ከእርሱም ጋር በሰላም፤ በፍቅርና በደስታ ለመኖር፤ በክርስቶስ ሞትና ትንሳዔ አማካኝነት የዘላለምን ህይወት አግኝትን በተስፋ ለመኖር የሚያስችለን ብቸኛው መንገድ ምን እንደሆነ ይህ አዲስ ዜና በግልጽ ያስረዳናል፡፡ ወንጌል የቅዱሳት መጻህፍት ሁሉ ማእከላዊው መልእክት ሲሆን ቅዱሳት መጻህፍትንም እንድንረዳ የሚረዳን ቁልፍ መልእክት ነው ማለት ያቻላል፡፡ ይህ ወንጌል ግልጽ አድርጎ የሚነግረን ምንድነው ቢባል፤ የእስራኤል መሲህና የእግዚአብሄር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥላሤ መሃል ሁለተኛው፤ ሥጋ ለብሶ የተገለጠ፤ በሞቱ በትንሳዔውና በእርገቱ የአባቱን የማዳን ሥራውን ያከናወነ አገልጋይ እንደሆነ ነው፡፡ ስለ ኃጢኣታችን መሞቱና ከሙታንም በድል መነሳቱ በነቢያት ትንቢት የተነገረና በአይን ምስክሮችም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ በእግዚአብሄር በራሱ ጊዜና በራሱ መንገድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ፈራጅና እንደ ጌታ በክብር ይመለሳል (1ኛ ተሰሎንቄ 4፡13-18፤ ማቴዎስ 25፡31-32)፡፡ በአሁኑ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ መንፈሱን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ሶስቱም የሥላሴ አካላት በአንድ ላይ በመሆን ኃጢኣተኞችን የማዳን ሥራ በመሥራት ላይ የገኛሉ ማለት ነው፡፡

ይህ ወንጌል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አንደ ህያው አዳኝ፤ ጌታ፤ ህይወት እና እምነታቸውን በእርሱ ላይ የሚጥሉ አማኞቹ ሁሉ ተስፋ አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ እንዲሁም፤ ይህ ወንጌል ሌላ ወንጌል ከጎኑ የሌለው ብቸኛ ወንጌል ነው፡፡ እርሱን ለመለወጥ መሞከር ማለት እርሱን ለማጥፋት ወይም ለመደምሰስ መሞከር ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ወንጌል ህጻናትም እንኳን ጭምር ማንም በቀላሉ ሊረዳው በሚችለው መንገድ የተጻፈ እውነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ መሰረቱ እጅግ ጠንካራና በልዩ የስነ መለኮት ጥበብ የተሞላም መልእክት ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሁሉም በዚሁ ወንጌል ወደ ፍቅር አንድነት ተጠርተዋል፡፡ ስለዚህ እንደ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አማኞች ሁላችን ይህንን የወንጌልን እውነት በማወቃችንና አውቀን በወንጌሉ በማመናችን እጅግ ደስ ሊለንና እግዚአብሄርን ልናመልከው ይገባናል፡፡ ምክኒቱም በዚህ ወንጌል እውነት በማመናችን የእግዚአብሄርን የማዳን ሥራውን ተካፍለናልና፡፡ መጽሃፍ ቅዱሳችንም በግልጽ እንደሚነግረን በክርስቶስ ወንጌል የሚያምኑ ሁሉ በጸጋው አማካኝነት የእግዚአብሄር ሴትና ወንድ ልጆቹ የመሆንን፤ እንዲሁም እህትማማችና ወንድማማች የመሆንንም እድል አግኝተዋልና፡፡ በክርስቶስ ጽድቅን ያገኙት ሁሉም ከአባቱ ጋር ታርቀዋልና፤ ሙሉ የኃጢኣትን ስርየት አግንተዋል ማለት ነው፡፡ ከጨለማውም የዲያብሎስ መንግስት ወደ አስደናቂው የእግዚአብሄር ልጅ መንግስት ተሸጋግረዋል ማለት ነው፡፡ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የመሆን እውነታ እና የመንፈስ ቅዱስም ህብረትና አንድነት ሆኖላቸዋል ማለት ይቻላል፡፡

የወንጌል አማኞች ሁላችንን እግዚአብሄርን እንድናመልከው፤ በማያቋርጥ ሁኔታም እንድናመሰግነውና በቃሉ አማካኝነት ራሳችንን ሙሉ በሙሉ አሳልፈን ለጌታ እንድንሰጠው ተጠይቀናል፡፡ እንዲሁም በጸሎት አማካኝነት በእርሱ መደገፋችንን እንድንቀጥል ያሳስበናል፡፡ ምክኒያቱም ክርስቶስ ካመጣልን አስደናቂ የህይወት ለውጥ የተነሳ ሃዋሪያው ጳውሎስም በተለወጠና በታደሰ አእምሮና ልብ እርሱን ማምለክ ተገቢና አስፈላጊ ነገር እንደሆነ ይገልጸዋልና (ሮሜ 12፡1-2)፡፡

ስለዚህ የዚህን ወንጌል ተስፋ እና ደስታ መካፈል እጅግ በጣም የላቀ እድል ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ ይህ የወንጌል አዋጅ ለተወሰነ ጊዜ እየተሰበከ ቆይቶ የሚቆም ነገር ሳይሆን ከጌታ እንደ ተቀበልነው አደራ በየትኛውም ጊዜና የዓለም ክፍል ሁሉ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ሌሎችንም በትጋት በማስተማር፤ በማጥመቅ እና ደቀ መዛሙርትም በማድረጉ ሥራ ላይ ልንሰማራ የሚገባን ታላቁ ተልእኮ ነው (ማቴዎስ 28፡16-28)፡፡ ይህ ወንጌል ስለ ታላቁ ተልእኮ ያለንን ሙሉ እውቀትና መሰጠት በግልጽ የሚያስረደንና በዙሪያችንም ላሉት እውነቱ ምን እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን እኛም ሆንን ሌሎች በዙሪያችን ያሉት ሁሉ ለክርስቶስ ሊኖረን ስለሚገባው ልዩ አክብሮት በግልጽ የሚያስረዳ ነገር ነው፡፡

የወንጌል እምብርት

ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እግዚአብሄር አምላክ በማይሻረው ቃሉ ውስጥ ስለ መንግስቱና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ታላላቅ ሥራዎቹ እውነቱን በግልጽ ያስቀመጠበት እውነት ነው፡፡ ሃዋሪያትም ስለ ክርስቶስ ማንነትና ለኃጢኣተኞች ሁሉ ስለ ሠራላቸው የጽድቅ ሥራዎቹ በሚገባ አብራራርተው የተናገሩት ታላቅ ዘገባ ነው፡፡ የእምነት አባቶችም የእምነት ደንቦችን፤ ታሪካዊ የሃማኖት መግለጫዎችን፤ የተሃድሶ እና መሰረታዊ ትምህርቶች ሁሉ የሚመሰክሩበት ጠንካራ መሰረት ላይ የቆመ የወንጌልን መልእክት ነው፡፡ ይህም በአጭር ቃላት ሲገለጽ የወንጌል እምብርት ሊባል ይገባል፡፡

በሌላ አባባል የወንጌል ዋናው ልቡ ወይም እምብርቱ ምንድነው ቢባል በፍቅር የተሞላው ቅዱሱ ፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ምክኒቱም ኢየሱስ ከሰዎች ሁሉ አመጽና ክፋት ጋር ፊት ለፊት በመጋጠም እና በማሸነፍ ህዝቡንም በመታደግ ነጻነትን ለመስጠት በመቻሉ ታማኝነቱን አስመስክሮ አዳኛችንና ታዳጊያችን ሊሆን ችሎአልና፡፡ ዮሃንስም በመልእክቱ እንደሚነግረን እግዚአብሄር አብ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ኃጢኣታችንን በማስወገድ እንዲያድነን ልኮታልና (1ዮሃንስ 4፡14)፡፡ ስለዚህ በአንድያ ልጁ በኢየሱስ ታላቅ የማዳን ሥራው ምክኒያት የእግዚአብሄር የማዳን እቅዱ ተሳክቶ በተግባር ላይ ውሎአልና፡፡ እንዲሁም ጴጥሮስ በሃዋሪያት ሥራ 4፡12 ላይ መዳን በሌላ በማንም እንደሌለና በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወይም ሥልጣን ብቻ እንደሆነ አረጋግጦ ይናገራል፡፡ በዋናነት ደግሞ በዮሃንስ ወንጌል 14፡6 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እርሱ መንገድ፤ እውነትና ህይወት እንደሆነ፤ እንዲሁም በእርሱ በኩል ካልሆነ ምንም ወደ አባቱ ሊመጣ ወይም ሊቀርብ እንደማችል በግልጽ ሲያስተምር እንመለከታለን፡፡

ሰብዐዊነት (1)

በዚህ በወንጌል ቃል አማካኝነት እኛ የሰው ልጆች ሁላችን ከእግዚአብሄር ጋር ለመልካም ግንኙነት የተፈጠርን ቢሆንም በአዳም በኩል በገባው ኃጢኣት ምክኒያት ግን ከፈጣሪችን ተለይተን ሙታን መሆናችንን እንመለከታለን በ1ኛ ቆሮንቶስ 15፡22፡፡ ከዚያም የተነሳ የእግዚእበሄርን እውነት የምንጠመዝዝና ህጎቹንም በመጣስ በእርኩሰታችን ምክኒያት ስሙን እንደምናጎድፍ ልናስተውል ይገባናል፡፡ እግዚአብሄር ግን በራሱ ተነሳሽነት ከራሱ ጋር ሊያስታርቀን ወዶ ኃጢኣት ባልነካው እና ቅዱስ በሆነው ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና የድል ትንሳኤው አማካኝነት ሊያድንና ጸጋውንም ሊያበዛልን እንደወደደ እናውቃለን (ኤፌሶን 2፡4-10፤ ሮሜ 3፡21-24)፡፡

ስርየት (1)

ይህ የኃጢኣት ስርየት ሥራ ተብሎ የሚታወቀው ጽንሰ-ሃሳብ ብዙ ዓይነት ጉዳዮችን የያዘ ትልቅ ሃሳብ ነው፡፡ በክርስቲያናዊ ስነለመኮት አንጻርም ሲታይ የሰው ልጆች ከእግዚአብሄር ጋር የነበራቸው ግንኙነት በኃጥኣት ምክኒያት ሲበላሽ በክርስቶስ ኢየሱስ የመስዋእትነት ሥራው አማካኝነት እንደ ገና የመታረቅን መልእክት የያዘ ነው[3]፡፡ እግዚአብሄር አባት ከኃጢኣት እስራት እና ከሰይጣን ግዞት ውስጥ ነጻ እንዲያወጣን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮልን ልጆቹና ወዳጆቹ አድርጎናል፡፡ ጌታችን ኢየሱስም በኛ ፈንታ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በመቀጣት ክቡር ደሙንም በማፍሰስ በኃጢኣታችን ምክኒያት የተቆጣውን የእግዚአብሄርን ቁጣ አብርዶልናል፡፡ ስለዚህም በእርሱ ለሚናምን ለሁላችን የጽድቅ አዋጅ ታውጆልን ከኃጢኣትችን ነጻ ልንወጣ ችለናል (ሮሜ 3፡25-26)፡፡ መጽሃፍ ቅዱሳችን ስለዚህ ጉዳይ ሲያስተምረን ሰጥቶ በመቀበል ላይ እንደ ተመሰረተ ጉዳይ ሲብራራ ከኃጢኣት ስርየት እና ከአብ ጋር ከማስታረቅ ጋር ያያይዘዋል (ማቴዎስ 20፡28፤ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡18-21፤ ሮሜ 3፡23-25፤ ዮህንስ ወንጌል 12፡31፤ ቆላሳይስ 2፡15)፡፡ ይህም ሁሉ የሚያስረዳን በክርስቶስ ሥራ ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር የነበረንና በኃላም የተበላሸው ግንኙነታችን እንደገና እንደ ታደሰና እኛም በእግዚአብሄር ዘንድ የሃጢኣትን ስርየትና ሰላምን  አግኝተን እንደገና ቤተሰቡ እንደሆንን ነው (ቆላሳይስ 1፡20፤ 2፡13-14፤ ሮሜ 5፡1-2፤ ገላቲያ 4፡4-7፤ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡18)፡፡ ስለዚህ ይህ በወንጌል ጥሪ ምክኒያት በእግዚአብሄር አባታችንና በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ ያመንንበት እምነታችን እውነተኛና ጽኑ ተስፋ ያለው ሲሆን ከልባችን ውስጥ እየፈለቀ ወደ ሌሎችም የሚፈስ ነው፡፡

በተጨማሪ ደግሞ ይህ ወንጌል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በአካል ከሙታን መነሳቱን፤ ወደ ላይ ማረጉን እና በአባቱ ቀኝ በዙፋኑ ላይ መቀመጡንም ይነግረናል፡፡ በዚህም ምክኒያት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መስዋእት ሆኖልን ከቅጣታችን ሁሉ ነጻ እንዳወጣን ያረጋግጥልናል፡፡ ይህም የሚያሳየን ወደ ፊት ደግሞ በታላቅ ክብር ዳግመኛ የመመለሱ ጉዳይ እርግጠኛ እንደሆነ ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡ እብራውያን 1፡1-4፤ 2፡1-18፤ 4፡14-16፤ 7፡1-10፡25)፡፡ ወንጌል እንደሚነግረን በእምነት አማካኝነት አማኞች ሁሉም ከትንሳኤው ጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድ ይሆናሉ፤ ልዩ ህብረትና አንድነትም ይፈጥራሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል እየተሞሉ ከኃጢኣት ተለይተው ወደ ቅድስናና እግዚአብሄርን ወደ መምሰልና ማገልገል ያድጋሉ ማለት ነው፡፡

ጽድቅ (1)

ወንጌል እንደሚስተምረን በእግዚአብሄር የሚተማመኑትና የሚያምኑ ሰዎች መጽደቅ በኃጢኣታቸው ምክኒያት ከሚመጣው ፍርድና ከእግዚአብሄር ቁጣ ለማምለጥና በክርስቶስ የጽድቅ ሥራ አማካኝነት በአሁኑ ዘመን እንኳን በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት እና ዋስትና እንዲኖራቸው ዋናው ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ እግዚአብሄር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ክፉና ኃጢኣተኛ የሆኑትን ሰዎች ያጸድቃል (ሮሜ 4፡5)፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በሠራላቸውም ታላቅ ሥራ አማካኝነት የእርሱን ጽድቅ ወደ እነርሱ በማዛወር ከፍርዱ ነጻ ያወያቸዋል (ሮሜ 4፡1-8)፡፡ ኃጢኣተኞችም በክርስቶስ ብቻ ካላቸው እምነት የተነሳ የጽድቅን ሥጦታ ያገኛሉ (ሮሜ 1፡17፤5፡17፤ ፊሊጵስዩስ 3፡9)፡፡ ስለ ኃጢኣታችን ኃጢኣት ከሆነው ከክርስቶስ የተነሳ እኛ ልንጸድቅ ችለናል (2ቆሮንቶስ 5፡21)፡፡ በአጭሩ ሲገለጽ በኃጢኣታችን ምክኒያት ክርስቶስ ኃጢኣተኛ ሆኖ እንደተቆጠረ ሁሉ እኛም በእርሱ የጽድቅ ሥራ ምክኒያት ጸደቃን ሆነናል ማለት ነው፡፡

እምነት 1. Faith (1)

እምነትን በኛ ላይ ያፈሰሰው የእግዚአብሄር አብ፤ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ እና የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ሁሉም የእግዚአብሄር የጸጋው ፍሬዎች ወይም ውጤቶች ናቸው፡፡ ይሀው እምነታችን እኛን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በማገናኘት ወደ አስደናቂው ድነት አመጣን፡፡ ወንጌል አረጋግጦ እንደሚነግረን ህይወታቸውን ለኢየሱስ ክርስቶስ አሳልፈው የሰጡ ሰዎች ዳግመኛ የተወለዱና የእግዚአብሄር ልጆች ናቸው (ዮሃንስ ወንጌል 1፡12)፡፡ በመንፍስ ቅዱስም የተሞሉና ዋስትናቸው የተረጋገጠላቸው እንደሆኑም ይናገራል (ሮሜ 7፡6፤ 8፡9-17)፡፡ በእውነት በክርስቶስ ባመንንበት ቅጽበት እግዚአብሄር አባታችን በእርሱ እንደ ጸደቅንና ወደ እርሱ መልክ እንደ ተለወጥን፤ መለኮታዊ ትእዛዙንም ለመጠበቅና እርሱን ለመታዘዝ እንደ ወሰንን ያረጋግጥልናል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ለእግዚአብሄርና ለትእዛዛቱ የመታዘዝ ጉዳይ በጣም ጠቃሚ ቢሆንም የጽድቁ ሥራችን ዋናው መሰረት ሊሆን አይችልም (የያእቆብ መልእክት 2፡14-26፤ እብራውያን 6፡1-12)፡፡

ቅድስና (1)

 ህይወታችንን በሚቀድሰው ጸጋው አማካኝነት ክርስቶስ የወደቀ ማንነታችንን የማደስ ሥራ በእምነት ይሰራል፡፡ ወደ እውነተኛው መንፈሳዊ ብስለትና ወደ ክርስቶስ ሙላት በምናድግበት አቅጣጫ ይመራናል ማለት ነው (ኤፌሶን 4፡13)፡፡  ወንጌላችን እንደ ክርስቶስ ታዛዥ አገልጋዮች እና በዓለምም እንደ እርሱ አምባሳደሮች የጽድቅን፤ የፍቅርንና የምህረትን አገልጎሎቶች በመስጠት ህያው ምስክሮቹ ሆነን በክርስቶስ መንግስት ውስጥ እንድናገለግለ ይጠራናል፡፡ በመስቀል ላይ በመሞቱ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ከሚገመተው በላይ ወደ ሆነው ደስታና ማቆሚያ ወደሌለው አምልኮ አምጥቶናል (ፊሊጵስዩስ 1፡21፤ ራእይ 22፡1-5)፡፡

ድነት  (1)

ድነት የሚለው ቃል መሰረተ ሃሳቡ ባለፈው ዘመን ከተሰራው የኃጢኣት ክስ፤ በአሁኑም ዘመን በመሰራት ላይ ካለው የኃጢኣት ኃይል እንዲሁም በሚመጣው ዘመን ሊሰራ ካለው ኃጢኣት ሁሉ ነጻ የመውጣትን ጽንሰ-ሃሳብ የያዘ ቃል ነው፡፡ስለዚህ አማኞች የወደፊቱን ድነት እያሰቡ ደስ እያላቸው አሁንም ሙሉው ድነት እስከሚገለጥ ድረስ ይጠባበቃሉ ማለት ይቻላል (ማርቆስ 14፡61-62፤ እብራውያን 9፡28)፡፡ ድነት በእግዚአብሄር አብ አነሳሽነት የተጀመረ፤ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ የተተገበረና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ደግሞ የተፈጸመ ነገር ነው፡፡ ድነት በእግዚአብሄር እቅድ ውስጥ ዓለም አቀፋዊ የሆነ ይዘት ያለው ስለሆነ ሰዎችን ከልዩ ልዩ ብሄሮች፤ ጎሳዎች እና ቋንቋዎች ያጠቃለለና በአንዲት ቤተ ክርስቲያን በመሰብሰብ አዲስንም ማንነት በመስጠት በአንዱ የእግዚአብሄር ህዝብነት እንዲታወቁና የክርስቶስ ሙሽሪትና አካል የሚያደርግ እውነት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ ጉዳይ በአጭሩ ሲገለጽ የዳኑ ሰዎች ሁሉ የመንፈስ ቅዱስ ማህበረሰብ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ ምክኒያት የዚህ የድነቱ ተካፋዮች ሁሉም እግዚአብሄርንና እርስ በርሳቸው አንዳቸው ሌላቸውን በፍቅርና በአንደነታቸው በመተሳሰር ሊያገለግሉ የተመረጡና የተጠሩ ናቸው ማለት ነው፡፡

አዲስ ፍጥረታት[4]

ጌታችን ኢየሱስ የልዑል እግዚአብሄር ልጅ እንደሆነና ንግስናውና መንግስቱም መጨረሻ የሌለው እንደሆነ ማሪያም እንደተነገራች እናስታውሳለን (ሉቃስ ወንጌል 1፡31-33)፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስም በክርስቶስ የሚገኘውን ድነት ከአዲስ ፍጥረት ጋር አያይዞ ይገልጸዋል፡፡ ይህም የሚያሳየን በአዳምና ሄዋን በኩል የገባውንና የሰውን ሁሉ ህይወት ያዘበራረቀውን አመጽና የኃጢኣትን ክፋት እንዲሁም በክርስቶስ በኩል የተገለጠውን የህይወት ተሃድሶ ነው (ዘፍጥረት 3፡1-19፤ ሮሜ 5፡12-21)፡፡ እኛ ራሳችንን እንደ ጣኦት እንድንቆጥር በሚገፋፋን የኃጢኣት አዘቅት ውስጥ አዳምና ሄዋንም ተጠላልፈው የወደቁበትና ከኤድን ገነት የተባረሩበት ወጥመድ ነበር፡፡ በዚህም ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር የነበራቸው መልካም ግንኙነት ሲበላሽ ሦስት ነገሮችን ያስታውሰናል፡፡ 1ኛ፤- ከእግዚአብሄር ጋር የነበረን የሁላችን ግንኙነት እንደተበላሸና ሁላችንም ከእግዚአብሄር ፊትና መገኛ ሥፍራ እንደተወገድን፡፡  2ኛ፤- እንደ ሰው ልጆች እኛም የነበረን የእርስ በርሳችን ግንኙነት በአስቀያሚ ሁኔታ እንደተበላሸና አንዳችን ለሌላችን እንደጠላት እንድንተያይ እንዳደረገን፡፡ ይህም የሚመነጨው እኛ አንዳችን በሌላችን ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላውም ፍጥረት ላይ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ ከምናደርገው ጥረት እንደሆነ ልናስተውል ይገባል፡፡ 3ኛ፡- አሁን ሁላችንም ደስ እያለን የምንገኘው ቁሳዊውን ፍጥረት እያየን በብዙ ሥቃይ ውስጥ እየታገልን ነው፡፡ ይህም ሥቃችን በመጨረሻው ቀን በሞት የሚያከትም እንደሆነ እናውቃለን፡፡

ይሁን እንጂ በክርስቶስ ሁሉም ነገር አዲስ እንደሆነ ደግሞ እናውቃለን (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡17)፡፡ ይህ አዲስ ፍጥረት የመጨረሸው ግቡ ወደፊት የሚፈጸም ቢሆንም በእውነተኛ ክርስቲኖች ህይወት ውስጥ አሁንም መፈጸሙን የጀመረ እንደሆን  ፍልፕ ታወር ተባለ የአዲስ ኪዳን ሊቅ አረጋግጦ ያብራራልናል[5]፡፡

ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች አሁንም እግዚአብሄርን አባታችን ብለን ልንጠራው እርስ በርሳችንም ወንድሞችና እህቶች ተባብለን ልንጠራራ እንችላለን ማለት ነው (ገላቲያ 6፡1-16፤ ኤፌሶን 2፡11-22)፡፡ ከዚያም ቀትሎ ደግሞ ወደ ፊት ቁሳዊው ፍጥረት ሁሉ ከከንቱነትና ከኃጢኣት እስራት  ነጻ ሆኖ የምናይበትን ቀን ለማየት እንናፍቃለን (ሮሜ 8፡18-25)፡፡

አዲሱ የፍጥርት ሙሉ መገለጥና የመጨረሻው ፍርድ[6]

በመጨረሻው ቀን የአዲሱን ፍጥረታት ሙሉ መገለጥ እናያለን፡፡ ምንም ብዙዎች ስለዚህ ጉዳይ እውሮች ቢሆኑም በአሁኑ ዘመን እንኳን ክርስቶስ በአባቱ ፈንታ ሁሉን በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡ እርሱ ራሱ በታላቅ ክብር በመላእክቱ ታጅቦ ዳግም በሚመለስበት ጊዜ ከነገድ ከቋንቋና ከብሄሮችም ሁሉ ሰዎች በፊቱ ይሰበሰባሉ (ማቴዎስ ወንጌል 25፡31-32)፡፡ ስለዚህም ጉዳይ ወንጌላችን ሁለት ነገሮች እንደሚሆኑ ይነግረናል፡፡ እነዚያም 1ኛ፤- ሁሉም ኃጢኣትን እንደሰሩ ሁሉ ክርስቶስን ያልተቀበሉትም ሁሉም በሰሩት ኃጢኣት መጠን ከክርስቶስ እጅ ፍርድን ይቀበላሉ፤ ይቀጣሉም፡፡ ዲያብሎስና ክፉ ሥራዎቹም ሁሉ በፍርዱ እሳት ይቃጠላሉ (ማቴዎስ 25፡31-46)፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ አሮጌው ሰማይና ምድር በኃጢኣት ምክኒያት ሲያልፉና ሲወገዱ እግዚአብሄር በታላቅ ክብር ተገልጦ በህዝቡ መሃል በማደር ሁሉን አዲስ ያደርጋል፡፡ ከአይኖቻቸውም አንባዎችን ያብሳል፡፡ ሞትንም ለዘላለም ያስወግደዋል፡፡ ልቅሶና ጩሀትም አይኖሩም፤ ሥቃይና መከራም ይወገዳሉ፤ አሮጌው ሁሉ አልፎ ሁሉም አዲስ ይሆናልና (ራእይ 21፡4)፡፡ እንደዚያም ሲሆን የፍጥረት ናፍቆት ሁሉ ይፈጸማል፡፡ እኛም እንደ እግዚአብሄር ሴት ልጆችና ወንድ ልጆች ሙሉ ድነታችን ተፈጽሞ ወደ ሙሉ ክብራችን እንገባለን፡፡ ቁሳዊው ማንነታችንም ከኃጢኣት እስራት ነጻ ሆኖ በዘላለሙ ክብር ውስጥ በመሆን በእግዚአብሄር ደስ ይለዋል (ሮሜ 8፡18-25)፡፡

በወንጌል የሚገኝ አንድነት

በዘር፤ በጾታ፤ በማህበራዊ፤ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮቻችን ከመለያየታችን ባለፈ እኛ ክርስቲኖች ሁላችንም በፍቅርና በአንድነት እንድንኖረና ለሌሎችም መልካም ምሳሌዎች እንድንሆን ታዘናል (የዮሃንስ ወንጌል 13፡34-3፤ ገላቲያ 3፡28-29)፡፡ እንዲሁም ደግሞ በተቻለ መጠን ሁሉ በአእምሮኣችን አስተሳሰብና በመሳሰሉት ነገሮቻችን ሁሉ አንድ እንድንሆን ተጠርተናል (ዮሃንስ 17፡20-21፤ ፊልጵስዩስ 2፡2፤ ሮሜ 14፡1-15፡13)፡፡ በክርስቲኖች መሃል ክፍፍል ሲፈጠር ለዓለም የምንመሰክረውን ምስክርነታችንን እንደደሚያደናቅፍብን ልናውቅ ገባናል፡፡ በክርስቲናዊ አስተምህሮችም መሃል በተለያዩ ዓይነት ክርክሮች አማካኝነት የሃሳብ ልዩነቶች ሲፈጠሩ የጋራ እምነቶቻችን እተሸረሸሩና  ልዩነቶቻችን እየሰፉ ሲሄዱ የህይወታችን ዋናው ዓላማ የሆነው አንድነታችን እየተዳከመ በመሄድ ለሁለተኛና ለሦሥተኛ ጉዳዮቻችን ሥፍራችንን እየለቀቅን እንሄዳለን ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት ምንባቦች ውስጥ በወንጌል አማኞች ዘንድ ቅድሚያ ልሰጠውና በመጀመሪያ ደረጃ ሊታወቅ የሚገባው ጉዳይ ምን እንደሆነ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይሁን እንጂ መልካም ንግግርና በጎ አድራጎትን ለማከናወን የምናደርገው ጥሩ አመለካከት ብቻ ሳይሆን ግልጽ በሆኑ ቃላት ሃሳባችንን በመግለጽ ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ መሆንንም ይጠይቃል፡፡ በክርስቶስ በማመናችን ብቻ መጽደቃችንን የምናስተምረው እውነት በጣም አስፈላጊ ነገር ቢሆንም ይህንኑ እውነት አረጋግጠን ለሌሎችም ግልጽ በሆኑ መንገዶች ለማስተላለፍ እንደ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በፍቅራችንና በአንድነታችን ደግሞ ልናረጋግጥ ይገባናል፡፡

ወንጌል ተገለጠ ነው

ማረጋገጫዎችና ተቃውሞዎች 1ኛ፡- በመጀመሪያ ደረጃ በእርግጠኝነት ልናውቀው የሚገባን ነገር ቢኖር የወንጌል ደራሲው ወይም ባለቤቱ እግዚአብሄር ራሱ እንደሆነ ነው (ማርቆስ 1፡14፤ ሮሜ 1፡1)፡፡ በሌላ አባባል የወንጌሉ ባለቤተ ብቻ ሳይሆን በተጻፈው ቃሉ አማካኝነት የወንጌልን እውነት የሚገልጥልንም እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡ ይህም ወንጌል ከእግዚአብሄር ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን በአደራነት የተሰጠ እውነት ነው፡፡ ስለዚህ የወንጌል እውነቱና ሥልጣኑ ሁሉ የሚያርፈው በእግዚአብሄር በራሱ ብቻ ላይ ነው፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስም በእርግጠኝነት የሚነግረን ወንጌል በሰዎች ፈቃድ ወይም ተነሳሽነት ለሰዎችም ዓላማ ታስቦ የመጣ ነገር ሳይሆን ቀጥታ ከእግዚአብሄር ልብ ውስጥ ፈልቆ ወደ ሰዎች ህይወት በመፍሰስ የማዳንና የማጽደቅ ሥራውን የሚሰራ ነገር እንሆነ ነው (ገላቲያ 1፡1-11)፡፡ እንደ ግለሰብ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም የቤተ ክርስቲያን ወይም በግል ተቆማት ሥልጣንና እውቅና ላይ ተመስርቶና ህጋዊነቱም ተረጋግጦለት የሚስፋፋ ነገርም ሊሆን በጭራሽ አይገባም፡፡ ምክኒቱም የወንጌል ባለቤቱ እግዚአብሄር ብቻ ነውና፡፡

የወንጌል ኃይል

ማረጋገጫዎችና ተቃውሞዎች 2፡ ሌላው በእርግጠኝነት መናገር የምንፈልገው ነገር ቢኖር ወንጌል ያለ ምንም ልዩነት ለሚያምኑበት ሁሉ ድነትን መስጠት የሚችል የእግዚአብሄር የማዳን ኃይሉ እንደሆነ ነው (ሮሜ 1፡16)፡፡ ይህም የወንጌ፤ል እውነት እርግጠኝነቱ የሚገለጠው በእግዚአብሄር በራሱ ኃይልና ሥልጣን ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 1፡18)፡፡ ስለዚህ አንዳንዶች እንደሚያስቡት የወንጌል ኃይል በሰባኪዎች የንግግር ችሎታ፤ አንደበተ ርቱእነት እና በወንጌላውኑ ሥልታዊ ዘዴዎች ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የሚታሰብ ከሆነ ፈጽሞ ልንቃወመው ይገባናል (1ቆሮንቶስ 1፡21፤ 2፡1-5)፡፡

ሰብኣዊነት (2)

ማረጋገጫዎችና ተቃውሞዎች  3. ወንጌል በአጠቃላይ የሰውን ህይወት በሙሉ በእግዚአብሄር ላይ በማመጽ የተበላሸ እንደሆነ መርምሮ እና አረጋግጦ ያሳያል፡፡ ከዚያም የተነሳ እያንዳንዱ ሰው ወደ ዘላለም ጥፋትና ፍርድ እየተጓዘ እንደሆነ በግልጽ ያረጋግጥልናል፡፡ ስለዚህ ማንኛውንም ዓይነት የሰዎችን ውድቀት እና አመጽ በራሳቸው መልካምነት ላይ በተመሰረተ የድነት ተስፋ ወይም በዘርና በሃማኖት አማካኝነት የመጽደቅን አስተሳሰብ ፈጽሞ ልንቃወመው ይገባናል፡፡

ድነት (2)

ማረጋገቻዎችና ተቃውሞዎች 4. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቸኛው የድነት መንገድ እና በእግዚአብሄርና በሰዎች መሃል ብቸኛው አማላጅ እንደሆነ አስረግጠን እናምናለን (ዮሃንስ ወንጌል 14፡6፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡5)፡፡ እንደዚሁም ከኢሱስ ክርስቶስና ከወንጌሉ ሌላ በምንም ዓይነት መንገድ ድነት ይመጣል ብሎ ማሰብን ፈጽሞ እንቃወማለን፡፡ ምክኒያቱም በሌሎች ሃይማኖቶች ውስጥ ምንም ዓይነት ነገር የሚያመልኩ ሰዎች ያለ ኢየሱስ ሊድኑ ይችላሉ የሚል ተስፋ የለምና፡፡

ወንጌል ለዓለም ሁሉ

ማረጋገጫዎችና ተቃውሞዎች 5. ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ለመስበክና ለማወጅ በእግዚአብሄር እንደተመረጠችና እንደታዘዘች እንዲሁም ለእንዳንዱ የሰው ልጅ ወንጌልን ለማድረስ ጥሪ እንዳላት በእርግጠኝነት እናምናለን (ሉቃስ ወንጌል 24፡47፤ ማቴዎስ ወንጌል 28፡18-19)፡፡ በተቃራኒ ደግሞ ሰዎች ከየትኛውም ኑሮ ደረጃ፤ ብሄር፤ ጎሳ ወይም ባህልና የሃማኖት ቡድን ቢሆኑ በወንጌሉ ካላመኑ በስተቀር ሊድኑ እንደማይችሉ አረጋግጠን እናውቃለን (1ኛ ቆሮንቶስ 9፡19-22)፡፡ ምክኒቱም እግዚአብሄር ከዓላም ሁሉ ዙሪያ ከእያንዳንዱ ጎሳ፤ ቋንቋ እና ብሄር ለራሱ የሚሆን አንድን ህዝብ ለመፍጠር ወስኖአልና (ራእይ 7፡9)፡፡

የኢየሱስ ክርስቶስ መለኮት

ማረጋገጫዎችና ተቃውሞዎች 6. እንደ መለኮታዊ ቃል (ዮሃንስ ወንጌል 1፡1)፤ ከስላሴም አካላት መሃል እንደ ሁለተኛ አካል፤ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ለዘላለም እንደሚኖር አምላክ (እብራውያን 1፡3) በኢየሱስ የሚኖረን እምነት በወንጌል የመዳናችን ዋናው መሰረት እንደሆነ እናምናለን፡፡ በተቃራኒ ደግሞ የጌታችንን የኢየሱስን ሙሉ መለኮት የማይቀበለውን ወይም የሚክደውን ትምህርትና አስተሳሰብ ፈጽሞ እንቃወማለን፡፡

አምላክ ሥጋ መሆን ወይም ሥጋን መልበስ

ማረጋገጫዎችና ተቃውሞዎች 7. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሊሆን የቻለ አምላክ እንደሆነ እናምናለን (ዮሃንስ ወንጌል 1፡14)፡፡ ሃዋሪው ጳውሎስም እንደሚነግረን ከዳዊት ዘር የመጣና ከድንግል የተወለደ እንደሆነም እናምናለን (ሮሜ 1፡3)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ የሆነ የሰውን ባህሪ የለበሰ፤ ለእግዚአብሄርም ህግ የሚገዛ እንደሆነ እናምናለን (ገላቲያ 4፡5)፡፡ በእንዳንዱም ነገር በትክክል እንደ እኛ ሲሆን ኃጢኣት ግን ያልነካው  ቅዱስ እንደሆነ እናምናለን (ዕብራውን 2፡17፤ 7፡26-28)፡፡ ስለዚህ በኢየሱስ እውነተኛ የሰው ልጅነት ማመን ማለት በእውነት በወንጌል ማመን እንደሆነ እናረጋግጣለን፡፡

በተቃራኒው ደግሞ የክርስቶስን የሰው ልጅነት ወይም በሥጋ መገለጡን የሚቃወመውን እንደሁም እርሱ ከኃጢኣት ሁሉ ነጻ እና ቅዱስ መሆኑን የማያምነውን ወይም እነዚህን እውነቶች የማይቀበለውን ትምህርት ሁሉ አጥብቀን እንቃወማለን (1ኛ ዮሃንስ 4፡2-3)፡፡

ሥርየት 2.

ማረጋገጫ እና ተቃውሞ 8. በክርስቶስ ፍጹም ታዛዥነትና መስዋእትነት ላይ የተመሰረተውን የኃጢኣትን ሥርየት ትምህርት እንቀበላለን፡፡ ስለ ኃጢኣታችን አስፈላጊ የሆነውን መስዋእትነት ሁሉ በመክፈል ጌታችን ኢየሱስ እዳችንን ሁሉ በመክፈል ቅዱስ አባቱንም በማርካት የኃጢኣትን ሥርየት አድርጎልናልና፡፡ ይህ ዓይነት ሥራው በእግዚአብሄር የዘላለም እቅዱ ውስጥ የነበረና በወንጌሉም እውነት የተረጋገጠ ነበርና፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በኃጢኣተኞች ፈንታ መስዋእት በመሆን ራሱን ለሞት አሳልፎ በመስጠት የእግዚአብሄርን ቁጣም በማብረድ የሰራውን የክርስቶሰን የኃጢኣት ስርየት ተግባር የሚቃወመውን ትምህርት ሁሉ አጥብቀን እንቃወማለን፡፡ ምክኒቱም ይህ ዓይነቱ ትምህርት የወንጌልን ዋና እምብርት የሚቃወም ክፉ ትምህርት ነውና፡፡

በህወቱና በሞቱ ያሳየው የኢየሱስ ክርስቶስ መታዘዝ

ማረጋገጫና ተቃውሞ 9. የክርስቶስ የማዳን ሥራው በኛ ፈንታ ሞቶና ከሙታን ተነስቶ ያሳየውን ታላቅ ሥራም የሚያጠቃልል እንደሆነ እናምናለን (ገላቲያ 3፡13)፡፡ እንዲሁም ደግሞ የእግዚአብሄር ህግ የሚጠይቀውን መጠይቅ ሁሉ ፈጽሞ በማሟላት እኛን ነጻ ባወጣን በክርስቶስ በማመን መዳናችንን በሚገልጸው ወንጌል እናምናለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ድነታችን ግቡን የሚመታው ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም የጽድቅ ሥራ ነው ብሎ  የሚያስተምሩትን ምንም ዓይነት ትምህርት እንቃወማለን፡፡ ምክኒቱም የድነታችን ዋናው መሰረቱ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ተግባሩ ነውና፡፡  

የኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤው

 ማረጋገጫና ተቃውሞው 10. የኢየሱሰ ክርስቶስ ከሙታን በአካል የመነሳቱ ጉዳይ በጣም እውነተኛና ሁሉም ሊያምነው የተገባ ሲሆን ወንጌላችንም ይህንኑ እውነት እንደሚያረጋግጥልን እናምናለን (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡14)፡፡ በተቃራኒው ደግሞ የክርስቶስን ከሙታን በአካል መነሳት የማያምነውን ምንም ዓይነት ወንጌል-ተብዬ የሚመስሉ ነገሮችን ፈጽሞ እናቃወማለን፡፡

ጽድቅ (2)

ማረጋገጫና ተቃውሞ 11. እውነተኛ ጽድቅ የሚገኘው በክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሆነ ከሚያስተምረው መጽሃፍ ቅዱሳዊ ትምህርት በስተቀር ሌላው ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ አረጋግጠን እናምናለን (ሮሜ 3፡28፤ ገላቲያ 2፡16)፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ማንም ሰው በመጽሃፍ ቅዱሳዊው ወንጌል ቢያምንም ነገር ግን ጽድቅ የሚገኘው በክርስቶስ በማመን ብቻ ነው የሚለውን የሃዋሪያቱን ትምህርት የሚክድ ከሆነ ፈጽሞ እንቃወማለን፡፡ እንዲሁም ከአንዱ ወንጌል በስተቀር ሌላ ወንጌል እንዳለ የሚያስተምሩትን ትምሀርት ፈጽሞ እንቃወማለን (ገላቲያ 1፡ 6-)፡፡

ማረጋገጫና ተቃውሞ 12. ክርስቶስ ስለኛ በመሞት መስዋእት በመሆኑ የኛ ኃጢኣት ወደ እርሱ የእርሱም ጽድቅ ደግሞ ወደኛ እንደተዘዋወረ እናምናለን፡፡ በእርሱ የምናምን ሁላችንም ሙሉ የሆነ የኃጢኣትን ይቅርታ እንዳገኘንና በእግዚአብሄርም ዘንድ ተቀባይነትን እንዳገኘን በእርግጠኝነት እናምናለን (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡19-21)፡፡ ይህም መጽሃፍ ቅዱሳዊው ወንጌል የሚያስተምረን እውነት ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እኛ በክርስቶስ የጸደቅነው በውስጣችን ባደረው ልዩ ጽድቅ እንደሆነ የሚያስተምሩትን ልዩ ትምህርት እንቃወማለን፡፡

ማረጋገጫና ተቃውሞ  13. እኛ የጸደቅንበት ጽድቅ የራሳችን ጽድቅ ሳይሆን ከኛ ሥራ ውጪ ኢየሱስ ብቻ ለአባቱ ፈጽሞ በመታዘዝ ያመጣው ጽድቅ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ጽድቅ በህጋዊ መንገድ ከክርስቶስ ሥራ የተነሳ ወደኛ የተላለፈና የኛ ሆኖ እንዲቆጠር በእግዚአብሄር የታወጀ ጽድቅ ስለሆነ የዚህ ጽድቅ ብቸኛው መሰረቱ እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፤ በተቃራኒው ደግሞ በምንም ዓይነት መንገድና በየትኛውም ዓይነት ደረጃ ላይ ቢንሆን እኛ የሰራነው ሥራ ለጽድቃችን ምንም ዓይነት አስተዋጽኦ ያደርጋል ወይም የጽድቃችን መሰረት ይሆናል ብሎ ማስብ  ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው (ገላቲያ 2፡16፤ ኤፌሶን 2፡8-9፤ ቲቶ 3፡5)፡፡

የመንፈሱ በኛ ውስጥ ማደር

ማረጋገጫና ተቃውሞ. 14. መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሁሉ ውስጥ ስለሚያድር ወይም ስለሚኖር አማኞቹ ወደ ቅድስናና ክርስቶስን ወደ መምሰል በማደግ ሂደት ላይ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በዚያ ህደት ላይ መሆናቸው የጽድቃቸው ወይም የመጽደቃቸው መሰረት ነው ማለት ግን አይቻልም፡፡ እግዚአብሄር መጽደቃችንን አውጆታል፤ ኃጢኣታችንንም ይቅር ብሎታል፡፡ በጸጋውም ብዛት በእምነት ብቻ ልጆቹ አድርጎ ተቀብሎናል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አማኞች በውርስ ባገኙት እና በውስጣቸው ካደረው ቅድስና ተነሳ ጽድቃሉ የሚለውን ፍልስፍና እንቃወማለን፡፡ ምክኒያቱም እኛ ገና ኃጢኣተኞች ሳለን ወዶን አጽድቆናልና፡፡

ቅድስና ወይም መቀደስ (2)

ማረጋገጫና ተቃውሞዎ 15.   

የሚያድን እምነት ወደ ቅድስናና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልተን ክርስቶስን ወደ መምሰልና  ወደ እውነተኛ የህይወት ለውጥ ይመራናል የሚለውን እውነት በርግጠኝነት እንቀበላለን፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ በገላቲያ 5፡22-25 እና ሮሜ 8፣4 እና 13-14 እንደሚነግረን ቅድስና ማለት በንስሃና ከክፉ መንገድ ሁሉ ወደ ክርስቶስ ሃሳብ ፈጽሞ በመመለስ በእርሱም ሙሉ በሙሉ በመደገፍ እርሱንና ህዝቡን ለማገልገል መዘጋጀት ማለት ነው፡፡  በተቃራኒው ደግሞ የጽድቅና የቅድስናን አስተሳሰቦች ለያይቶ ለማየት የሚደረገውን ጥረትና ልዩ ትምህርት ፈጽሞ እንቃወማለን፡፡ ምክኒያቱም የጸደቅን ሁላችንም በጸሎት፤ በንስሃ፤ መስቀልንም በመሸከምና በመንፈስ በመመራት ወደ ክርስቶስ በማደግ ቅድስናችን በህይወታችን ዘመን ሁሉ ሊቀጥል ይገባልና፡፡

እምነት (2)

ማረጋገጫና ተቃውሞ 16. ለድነት የሚሆን እምነት ስለ ወንጌል ያለንን እውቀት በልባችንና በእምሮአችን ጭምር በሚገባ መረዳትን ይጠይቃል፡፡ ኃጢኣተኛ መሆናችንንም በሚገባ ተረድተን ከዚህ ችግር ለመውጣት በግላችን ክርስቶስን አውቀን በእርሱ ሥራ ላይ ብቻ  መደገፍን ያስፈልጋል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ይህ ዓይነቱ እምነት በጭንቅላት እውቀት ላይ ብቻ የተመሰረተ እንደሆነ የሚያስተምር ከሆነ ፈጽሞ ልናወግዘው ይገባል፡፡ ምክኒቱያም ጽድቅ የሚገኘው በውጫዊ አስተሳሰብ ላይ በተመሰረተ እምነት ሊሆን አይገባምና፡፡

የወንጌል ትምህርት     

ማረጋገጫዎችና ተቃውሞዎች 17. እውነተኛ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ትምህርት በጣም አስፈላጊና ለመንፈሳዊ ህይወታችንም ጤንነት ጠቃሚ ቢሆንም እኛ የዳንነው ትምህርቶችን በሚገባ በመማራችንና በማወቃችን እንዳልሆነ ልንረዳ ይገባናል፡፡መጽሃፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዎች በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ ናቸው፡፡ ምክኒያቱም ሊያድኑን ባይችሉም እንኳን እንዴትና በምን ዓይነት መንገድ ወይም በማን በማመን ልንድን እንደምንችል መንገድ ያሳዩናል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ስለ ወንጌል የሚናገረውን መጽሃፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶችን አለመቀበል መንፈሳዊ ውድቀትን በማስከተል ለእግዚአብሄር ፍርድ ያጋልጠናል፡፡

የወንጌል ሥርጭት

ማረጋገጫና ተቃውሞ 18. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተከታዮቹን ሁሉ የወንጌልን መልእክት ህይወት ላለው ነፍስ ሁሉ በየትም ስፍራና በምንም ዓይነት ላይ ሆነው እንዲሰብኩ ወይም እንዲያውጁ ትእዛዝ አስተላልፎአል፡፡ እንዲሁም ወንጌልን በማሰራጨትና ደቀ መዛሙርት በማድረግም በትጋት እንዲሰሩ አስተምሮ አሰማርቶአል፡፡ ሙሉ በሙሉ በታማኝነት የክርስቶስን ትእዛዝ መፈጸምም በጥሩ መንፈሳዊ ህይወት ለሌሎች መልካም ምስክር መሆንን እንዲሁም ለጎረቤቶቻችንም መልካም ሥራ በመሥራት የህይወት ምሳሌነትን ማካፈልንም ይጠይቃል፡፡ እንደዚያ ካልሆነ ግን የወንጌል ሥርጭትና የህይወት ምሳሌነት ተለያይተው ከተደረጉ ምንም ዓይነት ውጤት ሊያመጣ ስለማይችል ከንቱና ግልጽ ያልሆነ ወሬ ብቻ ሆኖ ይቀራል ማለት ነው፡፡

ማጠቃለይ

በወንጌል ሥራ ምክኒያት እንደተጣመሩና አንድ እንደሆኑ ክርስቲያኖች እኛም አንዳችን ለሌላችን ለመጠንቀቅና እርስ በርሳችንም ለመጠባበቅ ቃል ልንጋባ ይገባናል፡፡ እንዲሁም ደግሞ አንዳችን ለሌላችን ልንጸልይ፤ በመሃከላችንም ችግር ቢኖር ይቅር ልንባባል፤ የእርዳታ እጃችንንም ልንዘረጋጋ ይገባናል፡፡ ይህም ሊሆን የሚገባው በመልካዓ ምድራዊ ሁኔታ በቅርብ ወይም በሩቅ ስለምንኖር ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ህብረት የተጣመርነው እና በክርስቶስ ደም አንድ የሆንን ሁላችንም በያለንበት ስፍራ ሁሉ የአንዱ እግዚአብሄር ቤተሰብ ስለሆንን ነው፡፡

አንድ ሰው እንዳለው፡ “አስፈላጊና በጣም ጠቃሚ ለሆኑ ነገሮች አንድነት ያስፈልጋል፡፤ ከአስፈላጊ ነገር ለሚያነስ ነገር ደግሞ ነጻ መውጣት ያስፈልጋል፡፡ ለሁሉም ነገር ደግሞ በአንድ ላይ በጎ ለማድረግ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ምክኒቱም ለወንጌል እውነት እነዚህ ነገሮች ሁሉ በጣም አስፈላጊ ናቸውና”፡፡

በመጨረሻም ለወንጌሉ እውነትና ለጸጋው ባለቤት ለእግዚአብሄር አምላካችን በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ከዘላለም እስከ ዘላለም ምስጋናና ክብር ይሁን፡፡ አሜን!!

[1] Packer, Collected Shorter Writings, 2:250.

[2] These concluding sentences are drawn from ‘Great Truths: Sin and Death,’ 4.1 https://www.greattruthsglobal.com/sin-and-death/.

[3] Oxford English Dictionary, Dictionary app version 2.3.0 (294), Apple Inc. This paragraph is additional to the original 1999 statement.

[4] This section – ‘New Creation’ – is additional to the original 1999 statement.

[5] Philip H. Towner, “New Creation” in Walter A. Elwell (ed) Evangelical Dictionary of Biblical Theology (Baker, 1996), 563.

[6] This section – ‘The Full Unveiling of the New Creation and Final Judgment’ – is an amplification of the original section on ‘Final Judgment’ contained in the 1999 statement.

Copyright © 2022 by Benjamin T. F. Dean

ይመዝገቡ

ሙሉ ስም
Consent
I give permission for Great Truths to store my email address for the purposes of sending me regular updates. I understand that I can unsubscribe at any time using the link in any email.