ቤንጃሚን ዲን
ከካምብሪጅ ዩንቨርስቲ ፒ.ኤች.ዲ
ቄስ ዶ/ር ቤንጃሚን ዲን በ ባልካን የስነ መለኮት ሲሚናሪ ተጋባዥ አስተማሪ በመሆን እያገለገሉ ሲሆን ከዛ በፊት የለንደን ሴሚናሪን በፕሮግራም መሪነት እና በኬፕ ታውን ጆርድ ዋይትፊልድ ኮሌጅ መሪ በመሆን አገልግለዋል።
ቤን (ቤንጃሚን) ወደ ጌታ የመጡት በ1987 በቅዱስ ኒኮላስ ቤ/ክ ሰቨንኦክስ ሲሆን በትምህርት ጥናት ዝግጅት በለንደን እና ካምብሪጅ ካሳለፉ በኋላ በእንግሊዝ ቤ/ክ (Church of England) የእረኝነት አገልግሎትን ተቀብለው በሰሜን ዴቮን አገልግለዋል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2008 ዓ.ም ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት የጆርጅ ዋይትፊልድ ኮሌጅ የድህረ ምረቃ ትምህርትን በመምራት እና ስነመለኮት በማስተማር ለአመታትም አገልግለዋል።
ናኦሚ ከተባለች ሚስታቸው ጋር ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በትዳር ያሉ ሲሆን በነዝህ ቆይታቸው አራት ልጆችን አፍርተዋል።