መላእክት

ፀሀፊ፡ ዶ/ር ቤንጃሚን ዲን

ተረጓሚ፡ ዶ/ር በቀለ ደቦጭ

ንባብ፡ ምሩቅ ዩሐንስ

ማውጫ

መግቢያ

ሰማይና ምድር ሠራዊታቸውም ሁሉ ተፈጸሙ (ዘፍጥረት 2፡1)፡፡

ኦገስቲን የተባሉ የጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን አባት እንዳሉት፡- ቤተ ከርስቲያን ሲባል እኛ መረዳት ያለብን ቤተ ክርስቲያንን እንደ አጠቃላይ የክርስቶስ አካል እንጂ ከጸሃይ መውጫ እስከ መግቢያ ድረስ እንደምትታይ እና የጌታን ስም እያመሰገነችና ስለማዳኑም ኃይል አዳዲስ ዝማሬዎችን እየዘመራች እንደሚተጎዝ እንደ አንዲት ቁራጭ የህብረተስብ ክፍል አይደለም፡፡ ይህም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚከናወነው በቅዱሳን መላእክቱ አማካኝነት ሲሆን ይህም ዓይነቱ የመላእክቱ ሚና የተባረከ ሆኖ የሚዘልቅ ይሆናል[1]፡፡ እንዲሁም ዊሊየም ሼክስፒር ደግሞ በሰማይና በምድር የሚገኙት ብዙ ነገሮች ስለ ፍልስፍናችን ከምናልመው ህልም በላይ የሆኑ ነገሮች ናቸው ብሎ ነበር፡፡[2]

ፍራንስስ ሰካፈር የተባለ ክርስቲያን ፈላስፋ ደግሞ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ንግግር ሲደርግ በነበረበት ወቅት ተማሪዎቹ ሲጠይቁት የመጀመሪያ ንግግሩ ስለ እግዚአብሄር እና ስለ ኃጢኣት ስለነበረ ሰዎቹ እርሱ ስለ ግብረገብ እንደሚናገር ነበር የተረዱት፡፡ ነገር ግን እርሱ ስለ መላእክት ሲናገር እነዚያው ሰዎች ስለ መንፈሳዊ እውነት እንደሚናገር አድርገው ተረዱት፡፡ ይህም መንፈሳዊ እውነት ትልቅና ከላይ የወረደ ሁሉንም ሊያጠቃልል የሚችል ዓይነት እውነት አድርገው የተረዱት፡፡ ይህም ሁሉ የሚያስተምረን ይህ ትልቅ እውነት የሚባለው በእግዚአብሄር አብ፤ በኢየሱስ ከርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ እውቀትና እውነት ላይ የተመሰረተ ሃቅ ሲሆን በእግዚአብሄር ትእዛዝ የሰማያዊውን ሠራዊት የመላእክቱንም ሚና የሚያጠቃልል ነገር ነው[3]፡፡

[1] Augustine, Enchiridion, 15.56; ed. and trans. Albert C. Outler (The Westminster Press, 1955/2006), 372.

[2] Hamlet, Act 1, Scene 5; in William Shakespeare, Complete Works, RSC Edition, eds. Jonathan Bate and Eric Rasmussen (Palgrave Macmillan, 2008), 159–167.

[3] Rory Shiner and Peter Orr, The World Next Door: A Short Guide to the Christian Faith (Matthias Media, 2022), 22-23.

1. መንፈሳዊው ዓለምና የመላእክት መገኛ ሥፍራ

የማይታየው ዓለም ሙሉ በሙሉ እውነት ነው 

በመጽሃፍ ቅዱሳችን የመጀመሪያው ዐ. ነገር የሚነግረን በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይንና ምድርን እንደ ፈጠረ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየን እኛ የምንኖርበት ዓለም ሁለት ዓይነት እንደሆነ እና የእግዚአብሄር ዓለም በሁለት ክፍል የተከፈለ እንደሆነ ነው፡፡ ከነዚህም ከሁለቱ ዓለማት አንዱ የሚታየው ምድር የሚሉት ሲሆን ሌላው ደግሞ በቀላሉ የማይታየው ሰማይ የሚሉት እንደሆነ ነው፡፡ እንዲሁም የተፈጥሮን ሁለት ዓይነት ልኬቶችን እንመለከታለን፡፡ እነዚህም ሁለቱ የተፈጥሮ ልኬቶች በአንዳንድ መንገዶች በቀጥታ ከሌሎች እውነታዎች ጋር የሚገኛኙ ናቸው፡፡

እግዚአብሄርም በአባታዊ መልካምነቱ ስንረዳው የሁለቱም ዓለማት ጌታ/አምላክና ፈጣሪ ነው፡፡ ሁለቱንም ለራሱ ክብርና ለህዘቡም ጥቅም ሲል ይገዛል፤ ያስተዳድራልም፡፡ በኒቂያ ጉባኤም እንደተገለጸው፡- ሁሉን በሚችል በእግዚአብሄር አብ፤ ሰማይንና ምድርን በፈጠረ፤ በውስጣቸውም ያሉትን የሚታዩትንና የማይታዩትን ሁሉ በፈጠረው አምላክ እናምላለን፡፡ ………፡፡

As expressed in the Nicene Creed, ‘We believe in God, the Father Almighty, maker of heaven and earth and of all things visible and invisible.’ As well as the observable, visible, material world, the cosmos includes a transcendent realm, a spiritual sphere, exterior and superior to us, that is for the time being usually invisible to us, but which is actually continuous and coexistent with us. According to Scripture, ‘the heavens’ (literally ‘atmosphere, sky’) is the world of angels, spirits, demons, cherubim, seraphim, authorities, principalities, powers, rulers, thrones, and dominions (Rom 8:38-39; Eph 1:21; 3:10; 6:12; Col 1:16; 2:10).[1] Herman Bavinck’s summary is astute: ‘Belief in a spiritual world is rooted in and profoundly expresses the truth of revelation; only God can make it known to us, and he has done so in Scripture.’[2]

እነዚህ ሁለቱ ቤቪንክስ የተባለው ሰው ያስቀመጣቸው ዐ. ነገሮች ሁላችንም ስለ መላእክት እውነተኛውን እውቀት እንድንጨብጥ የሚረዱን ሃሳቦች ናቸው፡፡

እኛ የሰው ልጆች ሁላችን ማንም ሊያየንና ሊረዳን በሚችልበት ሁኔታ የተፈጠርን በቁሳዊ ዓለም የምንገኝ ፍጥረታት ነን፡፡ መላእክት ግን ሙሉ በሙሉ ከኛ በላይ ሆነው በሰማያዊ ሥፍራዎች የሚገኙ መንፈሳዊ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ስለዚህ ስለ መላእክት ትክክለኛውን ግንዛቤ ሊሰጠን የሚችለው እግዚአብሄር ብቻ ነው፡፡ ይህንንም እግዚአብሄር የሚያደርገው በሰማይና በምድር ባለው በጌትነቱ ሥልጣን የቃሉን (የመጽሃፍ ቅዱስን) እውነት በመጠቀም ነው፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ ብቸኛው የዚህ እውቀት ምንጩ ሊሆን ይገባል፡፡ ስለዚህ ሁላችንም በመጽሃፍ ቅዱሳችን እውቀትና እውነት ላይ ብቻ መሰረታችንን አጠንክረን ሌላውን ሁሉ መንገድ ልንቃወምና ከአስተሳሰባችን ውስጥ ልናስወግደው ይገባል፡፡ ስለዚህ ጉዳይና ስለ ጉዳዩ ባህሪይ እና ስለ መንፈሳዊውም ዓለም የምንገምተውና የምናስበው ትልቅ ነገር ቢኖር የእግዚአብሄር አባታዊ ጌትነቱና ራሱን በክርስቶስ የገለጠበት መንገድ የወንጌሉ እውነት ብቻ እንደሆነ በማረጋገጥ ነው፡፡

ስለዚሁ ጉዳይ ሲናገር ካልቪን እንዳለው፡- ሁላችንም በሁሉም ሃይማኖታዊ ትምህርቶች ውስጥ በሚገባ አጥብቀን ልንይዘው የሚገባን እውነት ቢኖር ስለ ጉዳዩ እውቀትን በቀጥታ ከእግዚአብሄር ቃል መቀበላችንን ነው፡፡ በዚህም ጉዳይ የስነ መለኮት ሰዎች ዋናው ሥራቸው/ተግባራቸው ሊሆን የሚገባው የአድማጮቻቸውን ጆሮ በብዙ ወሬ መሙላት ሳይሆን ከእግዚአብሄር ቃል እውነተኛ፤ እርግጠኛና ትልቅ ትርፍ ያለውን ነገር አጠንክሮ ማስተማር ነው[3]፡፡

[1] ‘We live in a world of unseen spirits. Everywhere we go, we live in the presence of God, the infinite, eternal, and unchangeable Spirit. A human spirit animates the body of every man, woman, or child that we encounter. Furthermore, angelic and demonic spirits move invisibly about us as they strive to advance or defeat Christ’s kingdom’ (Joel R. Beeke and Paul M. Smalley, Reformed Systematic Theology, Volume 1, Revelation and God (Crossway, 2019), 1:1109). Since the time of writing, a very fine study came to my attention: Graham A. Cole, Against the Darkness: The Doctrine of Angels, Satan, and Demons (Crossway, 2019). For those whose interest immediately (and understandably) turns to matters of ‘spiritual warfare,’ the best recent single thing available is Keith Ferdinando, The Message of Spiritual Warfare (IVP, 2016). See also, Cole, Against the Darkness, 163-202.

[2] Herman Bavinck, Reformed Dogmatics: Abridged in One Volume, ed. John Bolt (Baker Academic, 2011), 276. In the face of atheistic disinclination to recognize the reality of the spirit world, Bavinck remarks, ‘[N]o science or philosophy can advance any argument against the possibility of such spiritual beings. Humans are psychic beings and cannot explain the life of the soul from material metabolism but have to predicate some spiritual substance for that life. This continues even after death and, therefore, the reality of the spiritual world is not inconsistent with any argument of reason or fact of experience’ (276).

[3] John Calvin, Institutes of the Christian Religion, trans. Ford Lewis Battles (The Westminster Press, 1960), 1.14.4; 164. Thanks to Robert Doyle for helping clarify this matter.

መላእክት መንፈሳዊ ፍጥረታት ናቸው

ምንም እንኮን የመላእክት መኖር በመጽሃፍ ቅዱሳችን በግልጽ የተቀመጠ ቢሆን እንኮን ጉዳዩ በጥልቀት ሲጠና ከየት እንደመገጡና ምንጫቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በሌላ አባባል መላእክት የመኖራቸው ጉዳይ ጥርጥር የሌለው ሃቅ ቢሆንም በእግዚአብሄር የተፈጠሩ ፍጥረታት እንጂ መለኮታዊ ማንነት ያላቸው እንዳልሆኑ መጽሃፍ ቅዱሳችን በግልጽ ያስተምረናል (መዝሙረ ዳዊት 148፡1-6)፡፡ ስለዚህ መላእክት በፍጹም ከእግዚአብሄር የተለዩ ናቸው ማለት ነው፡፡ በተጨማሪ እንደ ሌሎቹ ፍጥረታት ሁሉ መላእክትም እግዚአብሄር ዓለማትን በፈጠረበትና በሚገዛበት በውድ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን የተፈጠሩ ናቸው (ቆላሳይስ 1፡3-16)፡፡ እግዚአብሄር ዓለምንና ፍጥረታትን ሁሉ ሲፈጥር መላእክት እንደ ተወካዮችም እንደ መሃከለኛ አማካሪዎችም አልተጠቀመባቸውም፡፡ ምንም ዓይነት ተሳትፎና ድርሻም አልነበራቸውም፡፡ እነርሱም ልክ እንደ ማንኛውም የሰው ልጆች የሥላሴው የሥራ ውጤቶች እና እግዚአብሄር ሲጠራቸው ብቻ ካለመኖር ወደ መኖር የመጡ ፍጥረታት ነበሩ፡፡

ባለ ራእዩ ዮህንስ በራእይ 5፡11 እንደሚነግረን መላእክት ከቁጥር በላይ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ፍጥረታት ናቸው (ዳንኤል 7፡10፤ ኢዮብ 25፡3)፡፡ ስለዚህ የመላእክትን ትክክለኛውን ቁጥር ማናችንም በፍጹም አናውቅም፡፡

የኦሪት ዘፍጥረት መጽሃፍም ስለ መላእክት የአፈጣጠር ሁኔታ በቀጥታ አይነግረንም፡፡ ይሁን እንጂ ገና ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ እግዚአብሄር ብቻ መላእክትን ካለመኖር ወደ መኖር እንዳመጣቸው መገንዘብ ይቻላል[1]፡፡ እንዲሁም በዘፍጥረት 2፡1 እና ኢዮብ 38፡4-7 መላእክት በቁሳዊው ዓለምና በሰውን ልጆች ሁሉ መሃል የእግዚአብሄር ሥራ መስካሪዎች እንደሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ ስለዚህ በሌላ አባባል መላእክት ከቁሳዊ ዓለምና ከሰውም ልጆች ሁሉ በፊት እንደነበሩ ማሰብ ይቻላል ማለት ነው፡፡ በአጭሩ ሲገለጽ መላእክት ሰማያዊ ፍጥረታት ይሁኑ እንጂ በሚታየው ዓለም በመገኘታቸው በእግዚአብሄር የተፈጠሩ ፍጥረታትም ናቸው እንጂ ከፍጥረታት ውጪ አይደሉም፡፡ በሌላ አባባል መላእክት ሰማያዊ ፍጥረታት ናቸው ማለት ከፍጥረተ-ዓለሙ የተለየ ማንነት ያላቸው ሌላ ፍጥረታት ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ምክኒያቱም እንደ ሌሎች ፍጥረታት በእግዚአብሄር ቢፈጠሩም እንኮነ እንደ ሰው ልጆች በወንድና በሴት ጾታ ተለያይተው የሚታወቁና ሌሎችን መላእክት በመውለድ የሚባዙ ፍትረታት አይደሉም (ማቴዎስ 22፡30)፡፡ ስለ ሰማይና ምድር መፈጠር አስቀድሞ የታወቀ ነገር ባይኖርም ሰማይና ምድር በውስጣቸውም የነበሩ ብዙ ሰራዊት ሁሉ ተፈጥረው ካለቁ በኃላ መላእክት ደግሞ ከሰባተኘው ቀን በፊት መፈጠራቸውን ነው፡፡ ከዚያች ቀን በኃላ እግዚአብሄርም ከሥራው ሁሉ እንዳረፈ እናነባለን[2]፡፡

 ቦታ እና ጊዜ የሚባሉ ነገሮች እንደ ተፈጠሩና መንፈሳዊው ዓለም ደግሞ ወደ መኖር እንደመጣ እናነባለን፡፡ በሌላ አባባል ይህ መንፈሳዊው ዓለም የተፈጠረው ከቁሳዊው ዓለም መፈጠር በኃላ ነው፡፡ የወሰኑ ልክ እንዲህ ነው ተብሎ በግልጽ ባይታወቅም እንደ መንፈሳዊ ፍጥረታት መላእክትም ከጊዜና ከቦታ ጋር ያላቸው ግንኙነት የተወሰነ ብቻ ነው፡፡ ከሁሉ በላይ መላእክት ከሰው ልጆች ጋር ያላቸው ግንኙነት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ከሌላው ቁሳዊ ነገሮች ጋር ካላቸው ግንኙነት ይለያል፡፡ ምክኒያቱም መናፍስት እንደመሆናቸው መጠን ቢያንስ ቁሳዊ ነገሮች አይደሉምና፡፡

[1] Noting again Calvin’s measured advice referred to above: ‘[L]et us remember here … The theologian’s task is not to divert the ears with chatter, but strengthen consciences, by teaching things true, sure, and profitable’ (Institutes, 1.14.4; 164).

[2] Bavinck, Reformed Dogmatics. Abridged, 279.

ሁለት ገጽታዎች እርስ በርሳቸው እንዴት ይገናኛሉ?

ሁለት የፍጥረታት ገጽታዎች ማለትም መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ገጽታዎች ቢያንስ የሚገናኙበት ቦታ ይኖራል፡፡ በሌላ አባባል የሚታየውና የማይታየው ዓለም የየራሱ የሆነ መገናኛ ሥፍራ አላቸው፡፡ ይሁን አንጂ እግዚአብሄር የሁለቱም፤ የመንፈሳዊውና ቁሳዊው ወይም የሰማያዊውና ምድራዊው ዓለማት  ሁሉ ጌታና ገዢ ነው፡፡ ነገር ግን የሁለቱም ዓለማት ባህሪይ የአንዱ ከሌላው የተለያየ ነው፡፡ለምሳሌ ያህል በነጠላው ሰማይ የሚለው ቃል እግዚአብሄርን ሊይዘው አይችልምና ምክኒያቱም ሰማይ የእግዚአብሄር ፍጥረት ስለሆነ፡፡ በተጨማሪ፤ ሰማያት የእግዚአብሄር ሰማያት ናቸው ይላልና (መዝሙረ ዳዊት 115፡16)፡፡ ሰማይ እግዚአብሄር የሚያድርበት ወይም የእርሱ አገዛዝ የሚገለጥበት የእርሱ መኖሪያና መገኛ ሥፍራ ነው፡፡ ከዚያው ሆኖ እግዚአብሄር ሥራውን በመሥራት ፍጥረትን ሁሉ ይገዛል፤ ያስተዳድራልና፡፡ ስለዚህ ሰማይ እግዚአብሄር ፍጥረትን ሁሉ የሚቆጣጠርበትና የሚገዛበት ከሰው ልጆችም ሁሉ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ሥፍራ ነው ማለት ይቻላል፡፡ እግዚአብሄርም ከዚያው ስፍራ ሆኖ ማንም ሳቆጣጠረውና ሳይገዳደረው የፈለገውን ሁሉ በሥልጣኑ የሚሠራበት ሥፍራ ነው (ዘዳግም 26፡15፤ ማቴዎስ 6፡9-10፤ ሃዋሪት ሥራ 1፡11፤ ራእይ 4፡11)፡፡

ሰማይ ለምድርም እንደ ድንበር ወይም እንደ ኩታ ገጠም ሆኖ እያለ የእግዚአብሄር አገዛዝ የሚገለጥበት ሥፍራ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሰማያት የምንለው ደግሞ ለኛ በሥጋ አይናችን የማይታይና ልንደርስበትም የማይቻል ሥፍራ ነው፡፡ መላእክት ለሰው ዓይን የማይታዩ እና ከሰው ባህሪይ ውጪ የሆኑ ኃይላት ሲሆኑ ከእኛም ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ናቸው፡፡ ልንደርስባቸውም ከቶ የማይቻሉ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ በየእለት ተግባራቸው በዓይን በሚታዩ ተፈጥሮኣዊ ነገሮች ላይ ያላቸው ተጽእኖ ቀላል አይደለም፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስ በኤፌሶን 3፡10 እና 6፡12 እንደሚነግረን መላእክት በሰማያዊ ሥፍራዎችም የሚሰሩት ሥራ ታላቅ ነው፡፡ ስለዚህ በዓይኖቻችን የማይታዩ ነገሮች በቀላሉም የማንደርስባቸውና ልናውቃቸው የማንችል ይሁኑ እንጂ መላእክት ሙሉ በሙሉ ያሉና በትክክለኛ ተግባራቸው የሚታወቁ ነገሮች ናቸው፡፡

 በአጠቃላይ የመጽሃፍ ቅዱሳችንን ህግና ደንብ ትክክለኛ አሠራሩንም ተከትለን ስንሄድ እውነተኛው እና ውስጣዊው የእግዚአብሄር ሰማያዊ አገዛዙ ግልጽ ሆኖ ይታየናል ወይም ይታወቀናል፡፡ እኛም በዚያ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነን ነገሮችን ለማየትና ለመረዳት አለመቻላለችንን በሚገባ እንረዳለን፡፡ የኛም የተፈጥሮ አላዋቂነታችን ወይም ድንቁርናችን የግድ ከፍርሃት ወይም ከጭንቀት እንዲሁም ከጥንቆላ ስሜት የሚነጭ ነው ማለት አይቻልም፡፡ ምክኒያቱም መጽሃፍ ቅዱሳችን በግልጽ እንደሚነግረን ሰማይ እግዚአብሄር የሚኖርበትና ከዚያው ሆኖ ሁሉን የሚገዛበት፤ በቃሉም ኃይል ሁሉን የሚያዝበት ሥፍራ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየን በማቴዎስ 6፡10 ላይ ጌታችን ኢየሱስ አባቱን ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድርም ትሁን ብሎ የጸለየበትን ትልቁን ጸሎቱን መሰረት የሚያሳይ ሃሳብ ነው፡፡ ስለዚህ በመዝሙረ ዳዊት 103፡20 እንደምናነበው መላእክት የእግዚአብሄርን ቃል የሚታዘዙና የሚፈጽሙ ናቸው ማለት ነው፡፡ እግዘዚአብሄር የመንግስቱን ሉዓላዊ አገዛዙን ወደ ማጠቃለያው ሲያመጣው የክፋትን ኃይል ደምስሶ መንግስቱንም በምድር ላይ ሲያስፋፋው ምን እንደሚደረግ በዮሃንስ ራእይ ሃዋሪያው 60 ጊዜ በመጥቀስ እውነቱን ምን እንደሆነ ይናገራል፡፡ ያም የእግዚአብሄር መንግስት ማጠቃለያ የሚባለው የአዲሱ ሰማይና የአዲሱ ምድር የመጨረሻው ሥርዓት የሚፈጸምበት ሥፍራ ሲሆን ሰይጣንም ከአመጸኛ ሰዎቹና ሴቶቹ ጋር ወደ እሳት ባህር የሚጣልበትና የክርስቶስ ሙሽሪት የሆነቺው ቤተ ክርስቲንም ከመከራና ስደት ነጻ የሚትወጣበት ጊዜ ነው (ራእይ 20፡22)፡፡

በዚህ ዓይነቱም በእግዚአብሄር ክብር በተሞላው መለኮታዊ እንቅስቃሴ መላእክት እግዚአብሄርን በመታዘዝ እኛን በማገልገል ታላቅ ሥራ የሚሰሩበት ክስተት ይሆናል፡፡ በዚያም አስደናቂ የመገለጥ ክስተት ወቅት እኛም በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ እንዴትና ምን ዓይነት ድርሻና ተግባር እንደሚጠበቅብን በግልጽ እናለን፡፡ በአጭሩ ሲገለጽ መላእክት ለኛ ለሰው ልጆች መልካም የሆነውን ሁሉ ለማድረግ የእግዚአብሄር ሃሳብና ፈቃድ ብቻ የሚያድርጉ አገልጋዮች ብቻ ናቸው፡፡

የተደበቀ፤ ነገር ግን በጣም ወሳኝ ነገር

በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ስለማይታዩትና በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ስለሚገኙት ቁሳዊ ነገሮች እንመለከታለን፡፡ ይህም ማለት መንፈሳዊ ፍጥረታት በሌሎችም ዓለማት ውስጥ ይኖራሉ ማለት ነውና፡፡ ይሁን እንጂ ሥራቸውና ተግባራቸው በእግዚአብሄር ዓላማና እቅድ ውስጥ ትልቅ ጠቀሜታና ትርጉም ያለቸው እጅግ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄርን እንዲህ ካሉት ታላላቅ ሥራዎቹ አንጻር ለመረዳት ከፈለግን እንዲህ ያሉ ታላላቅ እና የተከበሩ ምሳሌዎችን ልንዘነጋ አይገባንም፡፡ ምንም እንዲህ ባሉ ሁኔታዎች ውስጥ የእግዚአብሄር መላእክት መገኘታቸውና ተግባራቸው በግልጽ የማይታይና ለመረዳትም አስቸጋሪ ቢሆንም እንኮን በሚታየው ዓለም ውስጥ የምናያቸው የሥራ ውጤቶቻቸው ግን  እርግጠኛና እጅግ ወሳኝ ናቸው ማለት እንችላለን፡፡ ከዚያ ሁሉ በላይ እንደምንመለከተው በጣም የሚያስደንቀውና የሚያስደስተው በመላእክቱ አገልግሎት አማካኝነት እግዚአብሄር ለህዝቡ እያደረገው ያለው ጥንቃቄና እንክብካቤ ነው፡፡ ስለዚህ እኛም በትክክል እንደምንረዳው በእግዚአብሄር ትእዛዝና በራሱ መንገድ መላእክቱ እንዲጫወቱ የሰጣቸው የአገልግሎት ሚና እጅግ አስደናቂ ነው፡፡

2. የተፈጥሮ ችሎታና አቅም

መጽሐፍ ቅዱሳዊው አገላለጾች

መልኣክ የሚለው ቃል መጽሃፍ ቅዱስ በተጻፈባቸው በሁለቱ ቋንቋዎች የሚለውን ለመረዳት መሞከር ይጠቅመናል፡፡ በእብራይስጥ ቋንቋ (mal’ak) ማልኣክ የሚል ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ደግሞ (angelos) አንጅሎስ ይላል፡፡ ይህም የሚያመለክተን የመላእክት ዋናው አገልግሎታቸው እና ተግባራቸው  ዜና ተሸካሚዎች እና አስተላላፊዎች፤ አዋጅ ነጋሪዎችና መልእክተኞች  እንደሆነ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አልፎ አልፎ ይህ መላእክት የሚለውን ቃል ለሰው ልጆች መልእክተኞችም መጠቀም ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ያህል በዮሃንስ ራእይ 2 እና 3 ላይ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲናት የተላኩ መልእክተኞችም በተመሳሳይ ስሜት መልእክተኞች ተብለው የተጠቀሱ ናቸው[1]፡፡

በሌላው አገላለጽ ደግሞ ይህ ዓይነቱ ሃሳብ በመጽሃፈ ኢዮብ 1፡6፤ የእግዚአብሄር ወይም የኃያሉ ልጆች በሚል እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት 29፡1 እና 89፡6 ላ ደግሞ የእግዚአብሄር/ሰማያዊ ነገሮች ተብለዋል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በ8፡5እና 97፡7 ቅዱሳን ተብለው ተገልጸዋል፡፡ በመዝሙር 89፡5፤ 7፤ ዳንኤል 4፡13 ላይ ቅዱስ ጠባቂ በሚል ቃል ተገልጾአል፡፡

በኢዮብ 38፡7 እና በራእይ 9፡1፤ በትንቢተ ኤርሚያ 33፡22፤ መዝሙር 104፡4፤ ህዝቅኤል 1፡13-14 ላይ ደግሞ በምሳሌኣዊ ንግግር ሲገለጽ በነፋስ፤ በእሳት ነበልባል፤ በሚቃጥል ከሰል፤ በችቦና በሚያበራ የመብረቅ ብርሃን እንደተገለጹ እንመለከታለን፡፡

[1] See D. Broughton Knox, ‘Translating “Angel” in the New Testament,’ Selected Works (Matthias Media, 2000), 1:363-373.

አገልጋዮችና መልእክተኞች

መላእክትን ከሰው ልጆች አገልግሎት ጋር ስናነጸጽር በእግዚአብሄር መገኛ ሥፍራ ውስጥ የሚኖሩ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ምክኒያቱም የስማቸው ትርጉም የሚያመለክተው አገልግሎታቸው ራሱ የአምባሳደሮችና የመልእክተኞች እንደሆነ ነው፡፡ መላእክት በምንም ዓይነት ሁኔታ የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው ሥልጣን ማደረግ አይችሉም፡፡ በራሳቸው ተነሳሽነትም ምንም ሊያደርጉና ሊወስኑም አይችሉም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የመደበላቸውንና ያዘዛቸውን ትእዛዝ ብቻ ተከትለው ይሄዳሉ፡፡ መጽሃፍ ቅዱስ ስለ እነርሱና ስለ መልእክተኝነት አገልግሎታቸው ከሚናገረው በላይ አልፈው መሄድ በፍጹም አይሄዱም፡፡

መላእክት የት ይገኛሉ? እንዴትስ ይገለጣሉ?

መላእክት በሆነ መልኩ መንፈሳዊ ዓይነት ባህሪይ እንዳለቸው መጽሃፍ ቅዱሳችን ይነግረናል (መዝ 104፡4፤ ሃዋ ሥራ 23፡8-9፤ እብራውን 1፡14)፡፡ በዚህ ዓይነቱ ስሜት ስንመለከተው መላእክት ቁሳዊ አካላትም ሲሆኑ፤ በሰውነት ቅርጽ ወይም በተክለ ሰውነት ግን ያልተገለጡ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ስለዚህ የመላእክት ከኛ ከሰው ልጆች ጋር ያላቸው ግንኙነት ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡ ነገር ግን መላእክት ቁሳዊ አካል አላቸው ከማለት ይልቅ በሚታይ መልኩ በቁሳዊ ማንነታቸውም የተዋቀሩ ናቸው ማለት ያስኬዳል፡፡ ምክኒያቱያም በጊዜና በቦታም የተወሰነና ከብዙ ነገሮቻችን ጋር ብዙ ዓይነት ግንኙነት አላቸውና፡፡ በርግጠኝነት የሊታወቅ የሚገባው ነገር ደግሞ መላእክት የሰው ልጆች ዓይነት ማንነትና ተግባርም ያላቸው ፍጥረታት ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡- በዘፍጥረት 19፡1-3 በሰው ልጆች መልክ ተገልጠው ወደ ሎጥ ቤት ተጋብዘው ከገቡ ጊዜ ምግብ ሲቀርብላቸው እንደበሉ ይናገራልና፡፡

መላእክት እንደሰው ልጆች የሚሞቱ፤ የሚዋለዱና የሚባዙ ፍጥረታት አይደሉም፡፡ ነገር ግን ከሌሎች ፍጥረታት የተለየ ማንነት ያላቸው ፍጥረታት ናቸው (ዳን. 8፡16፤ 9፡21፤ ሉቃ. 1፡19፣ ቁ 26)፡፡ እንዲሁም ደግሞ ሁሉም መላእክት ክንፍ ያላቸውና የሚበርሩ ባይሆኑም  አንዳንዶቹ ግን በክንፎቻቸው የሚበርሩ ናቸው (ዳን. 9፡21፤ ራእይ 14፡6)፡፡ ለምሳሌ፡- ሱራፌልና ክሩቤል ክንፍ ያላቸውና የሚበርሩ ናቸው (ዘጸኣት 25፡20፤ ኢሳይ. 6፡2፤ ህዝቅ. 1፡6 እና ራእይ 4፡8)፡፡ በሌላ አገላለጽ መላእክት ሁሉ ከክንፎቻቸው ጋር የሚታወቁ ብቻ ባይሆኑም አንዳንዶቹ ግን የግድ ክንፍ ያላቸው እንደሆኑ ደግሞ ሊታሰብ ይገባል ማለት ነው፡፡

መላእክት ከሰው ልጆች በምን ይለያሉ?

በሰው ልጆችና በመላእክት መሃል ያለው አንዱና ዋናው ልዩነት የሰው ልጆች በእግዚአብሄር አምሳል መፈጠራችን ነው፡፡ እንዲሁም መላእክት በኃይልና ሥልጠን በማንነታቸውም ጭምር ታላላቅና ኃያላን ሲሆኑ የሰው ልጆች ደግሞ በእርስ በርስ ግንኙነት የላቀ ማንነት አላቸው፡፡ ስለዚህ የሰው ልጆች ማንነት በእግዚአብሀር አምሳል ከመፈጠራቸው ጋር ተያይዞ እጅግ የበለጸገ ማንነት አላቸው ማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ከሰው ልጆች በተቃራኒው መላእክት አይጋቡም፤ ልጅ አይወልዱም፤ የቤተሰብም ጉዳይ አይመለከታቸውም፡፡ ከዚያም አልፎ የቀደሙ አያቶቻቸውንና የቅድመ አያቶቻቸውን  የዘር ሃረግ መቁጠርና ወደ ኃላ አይቆጥሩም፡፡

ከሌሎች ሁሉ የተለዩ፤ በግል ማንነታቸው የሚታወቁ እና ፍጥረታት ናቸው

ምንም እንደ ሰው ልጆች የሚዋለዱና የሚባዙ ባይሆንም እንኮን መላእክት ከሰው ልጆች ጋር የሚጋሩኣቸው የተለያዩ ባህሪያት አሉኣቸው፡፡ ለምሳሌ፡- እነርሱም እንደ ሰው ልጆች ስም አላቸው፡፡ ስለዚህ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ገብርኤል፤ ሚካኤል እየተባሉ በስም ያታወቃሉ፡፡ ይህም የሚያሳየን እኛ ብናውቅም ባናውቅም ሌሎችም ብዙ መላእክት የግል ስም ሊኖራቸው እንደሚችል ነው፡፡ እንዲሁም በሉቃስ ወንጌል 1፡19 እንደምናነበው ገብርኤል ራሱ ስለ ራሱ በመጀመሪያ ስሙ ሲተዋወቅ ነው፡፡ መላእክት በእግዚአብሄር የፍጥረት ሥራው እና በአሰራሩ ሁሉ ምን ያህል እንደሚደሰቱና እግዚአብሄርን እንደሚመልኩትም እንመለከታለን (ኢዮብ 38፡7)፡፡

በሉቃስ 12፡10 አንድ ኃጢኣተኛ ንስሃ ገብቶ ወደ እግዚአብሄር መንገድ ሲመለስ መላእክት ምን ያህላ እንደሚደሰቱና ሃሴት እንደሚያደርጉ ጌታችን ኢየሱስ ራሱ ተቅሶ ሲናገር እንመለከታለን፡፡ በሌላም ክፍል ደግሞ መላእክትም ምን ያህል ስሜታቸውንና ጉጉታቸውን እንደሚገልጹ እንመለከታለን ( 1ኛ ጴጥ 1፡12):: ይህም የሚያሳየን መላእክትም በግል ማንነታቸው የታወቁ ፍጥረታት እንደሆኑና ከእግዚአብሄርና ከሰው ልጆችም ሁሉ ጋር ግንኙነት ያላቸው ፍጥረታት እንደሆኑ ነው፡፡

ሰለዚህ ይህንን ጉዳይ ስናጠቃልለው፡-

መላእክት ትክክለኛና እውነተኛ ፍጥረታት ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ ቅዱስ ተብለው ይታወቃሉ (ማቴ 25፡31፤ ማር 8፡38፤ ሉቃ. 1፡26፤ ሃዋሪያት ሥራ 10፡22፤ ራእይ 14፡10፤ ዮሃ. ወ. 8፡44፤ 1ኛ ዮሃ. 3፡8)፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዶቹ የሚዋሹና ኃጢኣትን የሚሰሩም ተብለዋል፡፡ እንዲሁም ስለ ራሳቸው ጉዳይ በእግዚአብሄር ፊት እንደሚጠየቁም ሃዋሪያው ጳውሎስ በግልጽ ይናገራል (1 ቆሮ. 6፡3)፡፡ ምን ያህል በትክክል እንደሚያውቁ ግልጽ ባይሆንም መላእክት በአእምሮ እውቀትና ጥበብም ከሰው ልጆች ይልቅ በጣም አስደናቂ ፍጥረታት እንደሆኑ መረዳት ይቻላል (2 ሳሙኤል 14፡20፤ ራእይ 22፡9፤ ማቴ. 24፡36፤ 1 ጴጥ 1፡12)፡፡ የመላእክትንና የሰዎችን እውቀትና ባህሪይ ብናነጸጽር አንዳቸው በሌላቸው ላይ በተለያዩ መንገዶች ተጽእኖ ይኖራቸዋል (ሉቃ. 12፡8፤ 15፡10፤ 1ቆሮ. 4፡9፤ ኤፌ 3፡10)፡፡ መላእክት የራሳቸው ህሊና ያላቸውና የእግዚአብሄር መልእክተኞች እንደመሆናቸው ከሰዎች ጋር በቋንቋ ለመግባባት ይነጋገራሉ፡፡ ነገሩን እንደማጋነን ብንረዳምና ብንናገርም ሃዋሪያው ጳውሎስ መላእክት የራሳቸው ቋንቋ እንዳላቸው ደግሞ ይናገራል (1 ቆሮ. 13፡1)፡፡

እንዲሁም መላእክት ብርቱዎችና ኃያላን ፍጥረታን እንደሆኑም እናውቃለን (መዝ. 103፡20)፡፡ በብዙ ሁኔታዎችና መንገዶች የመላእክት ችሎታ ከሰው ልጆች አቅምና ችሎታ እጅግ ይልቃል (2ጴጥ 2፡11)፡፡ መላእክት በጣም አስደናቂና አስገራሚ የሥራ ድርሻና የአገልግሎት ሥልጣንም አላቸው (ዘፍ 19፡11፤ 2ዜና 32፡21፤ ደን 6፡22)፡፡ ዙፋናት፤ አገዛዝና ሥልጣናት ሁሉ የእነርሱ ናቸውና፡፡ ይህም ኃይልና ሥልጣን የሚመጣላቸው ከእግዚአብሄር ዘንድ ብቻ ሲሆን ሁሉም የሚወሰነውና የሚመራው በእግዚአብሄር በራሱ ፈቃድ ነው እንጂ በመላእክቱ አይደለም፡፡

ከዚህም የተነሳ ልክ እንደ ሰዎች ሁሉ መላእክትም መንፈሳዊ ፍጥረታት ናቸው፡፡ ብዙዎች ቢሆኑም በአንድ ላይ በመሆን ከሌሎች ጋር ህብረት ለመፍጠርም የተፈጠሩ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ምክኒያቱም መላእክትም ሰዎችም ለእውቀት፤ ለጽድቅ እና ለቅድስና የተፈጠሩ ነገሮች ናቸውና፡፡ እንዲሁም ሁለቱም ለመግዛትና ለማስተዳደር ሥልጣን የተሰጣቸውና ለበረከት የተፈጠሩ የእግዚአብሄር ልጆችም ተብለው ተጠርተዋልና (ኢዮብ 1፡6፤ ሉቃስ 3፡38)፡፡

ሱራፌልና ክሩቤል

ሱራፌል የሚለው የመላእክት ስም በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ የተጠቀሰ ሲሆን የስሙም ትርጉም የሚያቃጥል ማለት ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው ከሁሉ የበላይ የሆነውን የእግዚአብሄርን ቅድስና ነው (ኢሳ. 6፡2፣ 6)፡፡ ክሩቤል የሚለው ቃል ደግሞ ብዙ ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን ከሱራፌልም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው፡፡ ሁለቱም ከመንፈሳዊ ባህሪያቸውና ከልዩ ችሎታቸው የተነሳ ከሌሎች መላእክት ሁሉ የተለየ ዓይነት ደረጃና ባህሪይ አላቸው፡፡

በመጽሃፍ ቅዱሳችን በዘፍ. 3፡24 ስለ መንፈሳዊ ፍጥረታት እንደምናነበው በተለይ ክሩቤል ወደ ህይወት መንገድ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅ በኤድን ገነት በስተምሥራቅ እንደተቀመጠ እናነባለን፡፡ በሌላ አገላለጽ አዳምና ሄዋን ከኤድን ገነት  ከተባረሩ በኋላ ክሩቤል ግን በኤድን ገነት እንደተቀመጠ እናያለን፡፡ እንዲሁም የክሩቤል ጉዳይ ከቃል ኪዳኑ ታቦትም ጋር ተያይዞ ተነስቶ ተጠቅሷል (ዘጸ 25፡18-22፤ 37፡7-9፤ ዘኁ 7፡89፤ 1ዜና 28፡18)፡፡ እንዲሁም ከማደሪው ድንኮን መጋረጃዎችና ከቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍልና ከግድግዳውም ጋር የተያያዘ ታሪክ አለው (ዘጸ 26፡1፤ ቁ. 31፣ 36፡8 ቁ. ፤ 36፤ 1ነገ. 6፡23-35፤ 7፡20- 8፡7)፡፡ በዚህም ምክኒያት፤ በምሳሌዊ ንግግር ሲገለጽ ጌታ-አምላክ ከክሩቤል በላይ እንደተቀመጠ እናነባለን (1ሳሙ. 4፡4፤ 2ሳሙ. 6፡2፤ 2ነገ. 19፡15፤ መዝ. 18፡10፤ ኢሳ. 37፡16)፡፡

የመጀመሪያው የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ሲገነባ በነበረበት ወቅት ሁለቱ ክሩቤል የነበሩበትን ደረጃ አንዱ በቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል መሆኑን ሌላኛው ደግሞ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ከቃል ኪዳኑ ታቦት በላይኛው ሥፍራ እንደነበር በግልጽ ተጠቅሶአል (2 ዜና 3፡10-14፤ 5፡7-8)፡፡ በነቢዩ ህዝቅኤልም ራእይ የመጀመሪዎቹ ምእራፎች የምናነበው ስለ ክሩቤል የተጠቀሱትን እውነቶች ነው፡፡ ከክንፎቹም በተጨማሪ ክሩቤል በሰው መልክ የተፈጠሩና ህያው ፍጥረታት እንደሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ አራት ክንፍ እና ብዙ ዓይኖች ያሉኣቸው እንደሆኑ እናነባለን (ህዝቅ 1፡5-10፤ 9፡3፤ 10፡1-21፤ ራእይ 4፡6-9፤ 5፡6-7፡118፡9፤ 14፡3፤ 15፡7፤ 19፡4)፡፡ በአዲስ ኪዳናችንም የክብር ክሩቤል ከኪዳኑ ጽላት በላይ ማስተሰሪያውን የሚጋርዱ ሆነው እንደተገለጹ እናነባለን (እብ. 9፡5)፡፡ ከዚህም የምንረዳው ክሩቤል የእግዚአብሄርን ቅድስና የመጠበቅ ወይም የመጋረድ አገልግሎት የተሰጣቸው እንደሆነ ነው፡፡

3. በሰማያዊ ሥፍራ መደራጀታቸውና ልዩ ሚናቸው

እግዚአብሄርን ማምለክና ምስክርነታቸው

መላእክት የሚኖሩት በሰማይ ነው (ሉቃስ 2፡15)፡፡ በሰማያዊው ዙፋኑም ፊት ለፊት እግዚአብሄር የሚያዛቸውን ሁሉ ይታዘዙታል፡፡ ለእግዚአብሄር አገልግሎትና ፈቃዱንም ለማድረግ እንዲሁም እርሱን ለማመስገንና ለማምለክ ሁልጊዜ የተዘጋጁ ናቸው (መዝ. 103፡2021)፡፡ የእግዚአብሄርንም ፊት እያዩ ያመልኩታል (ማቴ 18፡10)፡፡ በአጭሩ ሲገለጽ የመላእክት ሥራቸው በሰማያት ሆነው እግዚአብሄርን መታዘዝ፤ ማምለክና ማመስገን ነው፡፡

የውትድርና ዓይነት የሥልጣን ተዋረድ አላቸው

በራእይ 10፡11፤ 18፡1 ስንለመከት አንዳንድ መላእክት ከሌሎቹ ይልቅ ኃይላን/ኃለኞች ይመስላሉ፡፡ ምክኒያቱም ሊቀ መልኣክ የሌሎቹ መላእክት ትእዛዝ ሰጪ ወይም አዛዥ ሆኖ ተገልጦአልና (1 ተሰ. 4፡16፤ ይሁዳ 9)፡፡ ሊቀ መላኣኩ ሚካኤልም ከዋናዎቹ አለቆች እንደ አንዱ ተቆጥሮ ተገልጾኣልና (ደን 10፡13)፡፡ እንዲሁም በዳን 12፡1 እና ራእይ 12፡7-9 ላይ መልኣኩ ሚካኤል ከእርሱ በታች ሌሎች እንዳሉት እንደ ታላቅ አለቃ ተገልጦአልና፡፡ ነገር ግን ግልጽ የሆነ የሥልጣ ተዋረዱ ሰንሰለት ምን ዓይነትና በምን ዓይነት ሁኔታ የተያያዘ እንደሆነ አልተገለጸም፡፡ ሊቀ መልኣኩ ሚካኤል የእግዚአብሄርን ህዝብ ከክፉ የመከላከ ሚናው ምን እንደሆነም በዳን 12፡1 ላይ ተጽፎኣል፡፡ መላእክት ሠራዊትም ተብለው ተገልጸዋል፡፡ ምክኒያቱም እነርሱ ራሳቸው አለቃ ያላቸው ስለሆኑ የበላይ አለቃቸው ጠባቂዎች ሆነው ተገልጸዋል፡፡ ከዚያ ሁሉ በላይ ግን እግዚአበሄር ራሱ የሠራዊት ወይም የአለቆች ሁሉ ጌታና ልዑል ተብሎ ተገልጾአል (ዳን 8፡11)፡፡

ይሁን እንጂ በመላእክቱ መሃል ያለውን የሥልጣን ተዋረድ ወይም የአወቃቀሩን  ሁኔታ በግልጽ እንዲህ ነው ማለት አንችልም፡፡ ነገር ግን እነርሱ በእግዚአብሄር ትእዘዝ እንደሚንቀሳቀሱና በተለያዩ ደረጃዎች ተደራጅተው በተለያዩ የሥልጣን እርከኖችም እንደሚሰሩ ወይም እንደሚያገለግሉ ማየት ይቻላል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር ብቻ የሰራዊቱ ሁሉ ጌታና አዛዥ እንደሆነ እናውቃለን፡፡

መለኮታዊ ጉባኤና ሰማያዊ  ሠራዊት ናቸው

እንደ ቡድን በአንድ ላይ ሲጠሩ የመላእክቱ ስብስብ ሰማያዊ ጉባኤ ተብሎ ሊጠራ ይችላል (መዝ. 89፡5)፡፡ መለኮታዊ ጉባኤም ናቸው ማለት ይቻላል (መዝ. 8፡21፤ 89፡7)፡፡ ሠራዊትም ይባላሉ ምክኒያቱም እግዚአብሄርም የሠራዊት ጌታና አለቃ ተብሎአልና (መዝ. 148፡2፤ 1ሳሙ. 1፡11፤ ሉቃ. 2፡13)፡፡ እንዲሁም ግዛት፤ ሥልጣናት፤ ዙፋናት እና ኃይላትም ተብለው ተጠርተዋል (ቆላ 1፡16፤ 1ጴጥ. 3፡22)፡፡ እነዚህ ቃላት በሃዋሪው ጳውሎስና ጴጥሮስ አማካኝነት  ሰማይና ምድርን ባጠቃለለ ሁኔታ መላእክት ያላቸውን ሥልጣን ለማሳየት የተገለጹ አባባሎች ናቸው፡፡ እነዚህና ሌሎችም የመላእክቱ ተግባራት የሚታቀዱትና የሚፈጸሙት  በሰማይ ነው፡፡ ምክኒያቱም ሰማይ የእግዚአብሄር ፈቃድ፤ እቅድ ዓላማና ግብ የሚወሰንበትና የሚተላለፍበት ሥፍራ ስለሆነ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እኛ አሁን በምድር ላይ ባለን እውቀትና ሥልጣን የሰማያዊውን ሠራዊት ግልጽ የሆነ ይዘትና አጀንዳ ሙሉ በሙሉ አናውቅም፡፡ እንዲሁም፤ መላእክቱ እንደ ቡድንም እንደ ግለሰብም አንዱ ከሌላቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነትም አናውቅም፡፡

ምክኒቱም ማንነታቸው ሁሌም ምስጢራዊ ነውና፡፡ መላእክት እንደ ሰማያዊ ፍጥረታት በግልም ሆነ በቡድን መኖራቸውን እናውቃለን፡፡ ይሁን እንጂ እንደ ግለሰብም ሆነ በቡድን እንደሚታወቁት ፍጥረታት መላእክቱ የሚኖሩት በማያቋርጥ ሁኔታ እግዚአብሄርን ለማምለክ ነው፡፡ እንዲሁም የመኖራቸውም ትልቁ ትርጉም የእግዚአብሄርን ፈቃድ ለማድረግና ለመታዘዝ ብቻ ነው፡፡

የማስተዳደርና የመግዛት ሥልጣናቸው

መጽሃፍ ቅዱሳችን እንደሚነግረን ከታላቁ የእግዚአብሄር ሥልጣንና አገዛዝ በታች መላእክት ወይም ብዙ ሰማዊ ሠራዊት ተብለው የሚታወቁ በብዙ የሚቆጠሩ ሰማያዊ  ሰራዊት ደግሞ አሉ (1ነገ. 22፡19-23፤ ኤር. 23፡18)፡፡ እነዚህ ሠራዊት እያንዳንዳቸው ለተለያየ ዓላማና ተግባር ሃላፊነትም ተሰጥቶኣቸው የተላኩ ናቸው፡፡

እግዚአብሄር ፍጥረቱን ሁሉ ለመግዛትና ለማስተዳደር ብሎም የሚያስፈልገውን ሁሉ አዘጋጅቶ ለመስጠት ሲወስን የመላእክቱ የተወካይነት ሚናቸው ጥቂት እንዳልሆነ ልናውቅ ይገባል፡፡ በተጠሩበትና በሚጠበቁበት በሁሉም ጉዳዮች ሲሳተፉ በእግዚአብሄር ሥልጣንና ኃይል እንደሆነ ደግሞ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ስለ ጉዳዩም ሲናገር ካልቪን እንዳለው፡- እግዚአብሄር አገልግሎታቸውን የሚጠቀምባቸው ሰማያዊ መናፍስት ሁሉንም ነገር ማድረግ ያለባቸው በእግዚአብሄር ፈቃድና እርሱ ባወጣው መርሃ ግብር አማካኝነት ብቻ ነው፡፡ በሌላ አባባል በተለይም ሥራውን ሁሉ ለመሥራትና ለሰው ልጆችም ጥቅም የሚውሉ ነገሮችን ሁሉ ለማድረግ እግዚአብሄር መላእክትን እንደ ትልቅና አስተማማኝ መሳሪያ ይጠቀምባቸዋል ማለት ነው፡፡ መላእክት የእግዚአብሄርን የጸጋ አገልግሎት እና ለኛ ለሰው ልጆች ደግሞ መልካም የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ውጤታማ በሆነ መንገድ የሚያስተዳድሩ እና የሚያገለግሉ አገልጋዮች ናቸው፡፡

ሌላው የምንመለከተው ነገር ቢኖር በእግዚአብሄር መንግስት ጉዳይ በመላእክቱ ጉባኤ አስደናቂ የሆነ በህብረት ተዋህዶ የመሥራቱ ነገር ነው፡፡ መላእክቱ ሁሉም ከሰማይ እስከ ምድር ለሚያደርጉት ነገር ሁሉ አቅጣጫ የሚያገኙት ከእግዚአብሄር ነው፡፡ ምንም እንኮን ከእግዚአብሄር የተለዩ ፍጥረታት ቢሆኑም ቅዱሳን መላእክቱ በእግዚአብሄር ፊት የሚመላለሱና እርሱንም በማምለክ ጭምር ያለ ምንም ዓይነት ርኩሰት በፊቱ የሚመላለሱ ፍጥረታት ናቸው (ራእይ 5፡11-14)፡፡ በዚህ ስሜት ስናስበው በሥራቸውም ሆነ በማንነታቸው ከሰው ልጆች የላቁ ፍጥረታት ናቸው፡፡

4. በአጠቃላይ የአቋማቸው ሁናቴ ምን ይመስላል?

ለመላእክት ሁሉ የሥራ አቅጣጫ የሚሰጣቸው እግዚአብሄር ራሱ ነው፡፡

መጽሃፍ ቅዱሳችን በግልጽ እና ያለምንም ማመንታት እንደሚነግረን መላእክት ከእግዚአብሄር በታች የሆኑ ፍጥረታትና በእርሱ እቅድና ፈቃድ ብቻ የሚመላለሱና የሚመሩ ናቸው፡፡ ስለዚህ በመላእክትና በእግዚእበሄር መሃል ያለው ልዩነት ግልጽ ነው፡ ምክኒያቱም እነርሱ የእርሱ ናቸውና (መዝ. 104-4)፡፡ እያንዳንዳቸውም በየግላቸውና በተለየ ሁኔታ በእግዚአብሄር በራሱ፤ ለእርሱም ክብር ለሚሆን አገልግሎት የተመረጡ ናቸውና (1 ጢሞ. 5፡21)፡፡ እንዲሁም እንደ እግዚአብሄር ያለ ማን ነው; የሚል ትርጉም ያለው የሚካኤል እና እግዚአብሄር ኃያል ነው የሚል ትርጉም ያለው የገብርኤል የስሞቻቸው ትርጉም በመላእክቱና በእግዚአብሄር መሃል ያለውን በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይቆረጠውን ግንኙነት ያሳያል፡፡

በሌላ አባባል በእግዚአብሄርና በቅዱሳን መላእክቱ መሃል ያለው ግንኙነት እጅግ ጠንካራና ትልቅ ትርጉም ያለው ነው፡፡

በእውቀትም ሆነ በልዩ ልዩ ተግባራት የመላእክቱ ችሎታ በርግጠኝነት ከሰው ልጆች እጅግ የላቀ ነው (ዳን. 9፡20-23)፡፡ እንደ ሰው ልጆች በቦታና በጊዜም የተወሰኑ ስለሆኑ መላእክት ከቦታ ወደ ቦታ የመሄድና የመምጣት ባህሪይ ይታይባቸዋል፡፡

ምንም በምድር ላይ ልዩ ልዩ የኃይል ሥራዎችን በመሥራት ቢታወቁም (ኢሳ. 37፡36)፤ እንደ እግዚአብሄር ግን ዘላለማዊ፤ ሁሉን ቻይ እና ሁሉን የሚያውቁ ፍጥረታት አይደሉም፡፡ በአጭሩ ሲገለጽ፤ መላእክት ከሚቃወማቸው ተቃራኒ ኃይሎች ጋር እንደሚገዳደሩና እንደሚቆቆሙ እንመለከታለን(ዳን 10፡13)፡፡ ይሁን እንጂ ከእግዚአብሄር በተቃራኒው ሁሉን ቻይና በሁሉ ሥፍራ የሚገኙ ፍጥረታት እንዳልሆኑ ልንገነዘብ ይገባል፡፡

ስለዚህ መላእክት እግዚአብሄር ብቻ ሊያደርግ የሚችለውን እነርሱ ሊያደርጉ የማይችሉ ፍጥረታት ናቸው ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል በምድር ላይ የሚገኘውን ፍጥረት ከምንም ዓይነት ህመምና ሥቃይ ሊያድኑ ወይም ነጻ ሊያወጡ አይችሉም፡፡ ለማንም የኃጢኣትን ይቅርታ ሊደርጉም አይችሉም፡፡ በጥቅሉ ስናየው፤ መላእክት በብዙ መንገድና ሁኔታ የተገደቡና የተወሰኑ ፍጥረታት ሲሆኑ ለእግዚአብሄር ልጅ ለኢየሱስ የበታች ሆነው ሊገዙና በእርሱም የሚያምኑትን ሊያገለግሉ የተገባቸው ፍጥረታት ናቸው (እብ. 1-2)፡፡

መላእክት ከክርስቶስ የበታች ናቸው

መለእክትን በሰውና በእግዚአብሄር መሃል እንደ አማላጆች ማሰብ/መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ የክርስቶስ አማላጅነት ግን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ የተጻፈ ነገር ነው (1 ጢሞ. 2፡5)፡፡ በሌላ አባባል መላእክት ከፈጣሪያቸው ከክርስቶስ የበታች ፍጥረታት ሲሆኑ እርሱ ግን ከሁሉም የበላይ የሆነ ፈጣሪ ነው (እብ. 1፡5-2፡9)፡፡ ስለዚህ መላእክት በሰውና በእግዚአብሄር መሃል ቆመው ማማለድ አይችሉም ማለት እንችላለን፡፡

የእግዚአብሄር የዘላለም ልጁ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ከሰማያት ወርዶ በቅድስት ማሪያም ማህጸን ውስጥ ሲጸነስ መላእክትም በዚያ ዙሪያ እንደነበሩና የእነርሱም ሚና ትልቅ እንደነበረ እንመለከታለን (ማቴ. 1፡18-25፤ ሉቃ. 1፡26-38፤ 2፡8-20)፡፡ እንዲሁም የመላእክት አገልግሎት ከሁሉም በላይና ልዩ ከሆነው ከእግዚአብሄር ማንነት እና ሥራው እጅግ በታች ነው፡፡ መላእክት የሚያበስሩትና የሚያውጁት የእግዚአብሄርን ታላላቅ ሥራዎች ነው እንጂ የራሳቸው የሆነውን ሥራ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ የእግዚአብሄርን ቃል በማወጁና በማብሰሩ ተግባር የቃሉ መሃከለኛ ሆነው የመልእክቱንም ጠቀሜታ በመግለጽ አያስተላልፉም ማለት አይደለም፡፡

ስለዚህ መላእክት በምንም ዓይነት ሁኔታ ሊመለኩ አይገባቸውም ማለት ነው (ቆላስ. 2፡18)፡፡ እንደ መለኮታውያን አማላጆችም ልዩ የሆነ የክብር ሥፍራ ሊሰጣቸው አይገባም፡፡ ምክኒያቱም በተፈጥሮ እንኮን እነርሱ ከእግዚአብሄር ፈጽሞ የተለዩ ናቸውና፡፡ እንዲሁም ደግሞ ከክርስቶስ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሲነጻጻሩ የተፈጥሮ ባህሪቸው ራሱ ተጨማሪና ሌላውን የሚያሟላ እንጂ በራሳቸው መለኮታውያን አይደሉም (እብ. 2፡5-9)፡፡

ስለ ክርስቶስ ይመሰክራሉ፤ ይታዘዙትማል

እግዚአብሄር ብቻ የሚያደርጋቸው እና መላእክት ግን የማያደርጉኣቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ፤ መላእክት አይፈጥሩም፤ የኃጢኣትን ይቅርታ አያደርጉም፤ አያድኑም፤ አይፈርዱም፤ ፍጹማንም አይደሉም፡፡ መላእክት የእግዚአብሄርን ፈቃድ በተሟላ ሁኔታ ያለ ምንም ስህተት ያደርጋሉ፡፡ እነርሱ ራሳቸው  የራሳቸውን ሳይሆን የእግዚአብሄርን ፈቃድ ብቻ በቀጥታ ይገልጣሉ፤ ያስተላልፋሉ፡፡ ምክኒያቱም የቃሉ ምንጭና ተናጋሪው እግዚአብሄር ራሱ ነውና፡፡ መላእክት ሊናገሩ ይችላሉ ነገር ግን እኛ ቃሉን የምንሰማው ከእግዚአብሄር ከራሱ ነው፡፡ ምክኒቱም መላእክቱ የእግዚአብሄር መላእክት ወይም መልእክተኞች ናቸውና፡፡ የመላእክት ዋናው ሥራቸውና ተግባራቸው የእግዚአብሄር መልእክተኞች ሆነው የእግዚአብሄርን ህዝብ ማገልገል ብቻ ነውና፡፡

መላእክት የሰውን ልጆች ያገለግላሉ

በመዝ. 8፡5 እና እብ. 2፡7 የሰው ልጅ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት እንደሚያንስ ይናገራል፡፡ ይህም ሰው ሆኖ በመገለጥ የሰውን መልክ ስለ ያዘው ስለ ኢየሱስ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ይሁን እንጂ በሰው መልክ ተገልጦ እንደ ሰው ከተቀበለው መከራ የተነሳ ይህ ኢየሱስ ራሱ የክብርና ምሥጋና ዘውድ ተጭኖለት በሁሉ ዘንድ እንደሚታይ ይነግረናለል (እብ. 2፡9)፡፡ ይህም የሚያመለክተን መላእክት ትልቅ ሥልጣን እንዳላቸውና የሰውን ልጆች በራሳቸው ሥልጣን እንደሚገዙና እንደሚቆጣጠሩ ሳይሆን እግዚአብሄር የሰጣቸውን ሥልጣን በጊዜያዊነት እንደሚፈጽሙት ብቻ ነው፡፡ በመጨረሻም ፍጹማን የሆኑ በክርስቶስ የሆኑ አማኞች ሁሉ ከክርስቶስ ጋር በሚገናኙበት ጊዜ ወሰን በሌለው ታላቅ ክብር ውስጥ እንደሚገቡና ከመላእክትም በላይ ክፍ እንደሚሉ እናነባለን (እብ. 2፡5-9)፡፡ ሌላ ደግሞ ከሰው ልጆች በተቃራኒ መላእክት አገልጋዮች እንጂ ነገሥታት አይደሉም፡፡

በሚመጣው ዓለም ከሚገለጥልን ታላቅ ስፍራ የተነሳ እኛ የሰው ልጆች በመላእክት ላይ እንኮን የመፍረድ እድል ሊኖረን እንደምችል ሃዋሪያው ጳውሎስ ይናገራል (1 ቆሮ. 6፡3፤ ኢዮ. 4፡18 እና 15፡15ን)፡፡ በዚህ ክፍል እንደምናነበው ሃዋሪያው ጳውሎስ የሰው ልጆች መጨረሻቸው ከመላእክትም ከሌሎች ፍጥረታትም ምን ያህል ከፍ ያለ እንደሆነ ነው፡፡

 የሰውን ልጆች በማገልገል የድነትን ጉዳይ ይከታተላሉ

በ1ኛ ጴጥ. 1፡12 ላይ እንደምንመለከተው መላእክት የሰው ልጆች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የሚያገለግሉትን ክቡር አገልግሎት ለማየት ምን ያህል እንደሚመኙ ነው፡፡ ይህም ማለት የእግዚአብሄር እውነት ለኃጢኣተኛው የሰው ልጆች በመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ጥበብ ሲታወጅ መላእክት እንዴት እንደሚደነቁ ያሳያል ማለት ነው (ኤፌ. 3፡10)፡፡ መላእክት የእግዚአብሄር ቃልና የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ ያንን ዓይነት አገልግሎት ለማገልገል እና ጉዳዩን በመከታተሉ ዙሪያም እጅግ በጣም ትጉህ አገልጋዮች ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ስለ እግዚአብሄር ህዝብ የድነት ጉዳይ ተግተው የሚያገለግሉ ቢሆንም ለራሳቸው ግን የድነት ጉዳይ ምንም ማድረግ የሚችሉ ፍጥረታት አይደሉም፡፡ መላእክት የእግዚአብሄርን የማዳን ጸጋውን፤ ምህረቱን፤ ርህራሄውን እና የኃጢኣት ይቅርታውን አያውቁም፡፡ ነገር ግን እነርሱ የሚያውቁት ቤክ የተባለ ሰው እንዳለው እግዚአብሄር በራሱ መንገድና ዘዴ ለሰው ልጆች የሚያደርገውን ታላላቅ ሥራዎች መመልከትና መከታተል ነው[1]፡፡ ወደ ኃላ አካባቢ እንደምንመለከተው በኃጢኣት የወደቁ መላእክት ንስሃ ገብተው የመመለስና እንደገና የመታደስ እድል የላቸውም፡፡ ይህ ተሃድሶና መመለስ የሚሆንላቸው ለሰው ልጆች ብቻ መሆኑ እኛን ከመላእክት የተለየን ያደርገናል፡፡

[1] Beeke, Reformed Systematic Theology, 1:1118.

5. መላእክት በምን ዓይነት መልክ ይገለጣሉ ወይም ይታያሉ?

ለማዳ ባይሆኑም በሚያስፈራ ሁኔታ ይገለጣሉ

በተለምዶ መላእክት ለሰው ልጆች በሥጋ ዓይን የሚታዩ ፍጥረታት አይደሉም፡፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ መላእክት በወንዶች መልክ የሚገለጡ ፍጥረታት ናቸው (ዘፍ. 18፡2፤ቁ. 16፤፤ 19፡1-22 መሳፍ. 13፡3-21፤ እብ 13፡2)፡፡ ከመለኮታዊ ሥልጣናቸው የተነሳ አንዳንዴ መላእክት የሚያስፈሩ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ባህሪያቸው መላእክት በሚታይ መልኩ ሲገለጡ የሚያስፈራ ሳይሆን በልዩ የእግዚአብሄር ክብርና ግርማ የተሞሉ እና በሚያስደንቅ ሁኔታም የሚገለጡ ናቸው (ዘኁ. 22፡31፤ 2 ነገስት 6፡17፤ ዳን. 10፡4-9፤ ማቴ. 28፡3፤ ሉቃ. 2፡9 እና ራእይ 10፡1-3)፡፡ በጥቂቱ ሊያስደንቀን የሚሞክረው ነገር ቢኖር ዮሃንስ ሁለት ጊዜ የእግዚአብሄርን መልእክት ወደርሱ ያመጣውን መልኣክ ሊያመልከው ወይም ሊሰግድለት ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን መልኣኩ ራሱ ይህንን ጉዳይ እንደተቃወመው እንመለከታለን (ራእይ 19፡10 እና 22፡8)[1]፡፡ ይህም ማለት መላእክት ለእግዚብአሄር የሚገባውን ክብር ለራሳቸው ለማድረግ እንደማይፈልጉ ነው፡፡

6. መላእክት በምድር ላይ ዋናው ተግባራቸው ምን ይመስላል?

 በምድር ላይ የመላእክት ዋናው ሥራቸው ወይም ተግባራቸው እግዚአብሄርን ማምለክና ማገልገል ነው፡፡ በሰማይ ያላቸው የተለምዶ ሥራቸውም እግዚአብሄርን ማመስገን ሲሆን በተለየና ባልተለመደ ሁኔታ ደግሞ ስናየው የእግዚአበሄርን ታሪካዊ የመዋጀትና የመታደግ ሥራውን ወደ ህዝቡ ዘንድ ማሳለጥ ነው፡፡ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ገና ከመጀመሪያው አካባቢ ጀምሮ የጌታ መላኣክ ወይም የእግዚአብሄር መልኣክ የሚሉ ሃሳቦች ከእግዚአብሄር ከራሱ ሥራና ተግባር ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ እዚህ ጋር እንደምንለመከተው መላእክትን ከፍጥረታት ጋር አንድ አድርጎ መመልከት አስቸጋሪ ይመስላል፡፡ ምክኒያቱም የመላእክቱ ሥራና ተግባር ከእግዚአብሀሄርና ከታላላቅ ሥራዎቹ ጋር በአንድ ላይ ተጠቅሶአልና፡፡ ለምሳሌ ያህል፤ የእግዚአብሄር መልኣክ ለአጋር እንደ ተገለጠላት እንመለከታለን (ዘፍ. 16፡7-12፤ 21፡17)፡፡ እንዲሁም ለሎጥ ለአብርሃምና ለያእቆብ እንደተገለጠላቸው እናነባለን (ዘፍ. 19፡1፣ ቁ. 15፤ 22፡11 ቁ. 15፤ 28፡12፤ 31፡11 ቁ. 13፤ 32፡1)፡፡ ምንም የመልኣኩ ሥራና ተግባር ከእግዚአብሄር ሥራና ተግባር የተለየ ቢሆንም (ዘጸ. 23፡20) የመልኣኩ ወደ ሰዎቹ የአመጣጡ እና የሚወስዳቸው እርምጃዎች የእግዚአብሄርን ሥራ የሚወክል ሆኖ እናገኛለን (ዘፍ. 24፡7፤ ቁ. 40 እና 32፡1፤ 48፡16)፡፡

መገለጦችን በማምጣት የእግዚአብሄርን ህዝብ ይታደጋሉ

 እንደ እግዚአብሄር አገልጋዮች የመላእክቱ ሚና የእግዚአብሄርን ህዝብ መታደግ፤ ከክፉም ሁሉ መከላከልና ወደ እግዚአብሄር ሃሳብና ፈቃድ መምራት ነው (ዘጸ. 3፡2፤ 14፡19፤ 23፡20፤ 23፡23፤ 32፡34፤ 32፡2)፡፡ እንዲሁም የመላእክቱ የአገናኝነትና የተወካነታቸው ተግባር ሁሉ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ በግልጽ የተቀመጠ ሲሆን እግዚአብሄር በንግግር ህዝቡን የሚገናኝበት መስመርም ሆነው ያገለግላሉ፡፡

በክርስቶስ መልእክተኝነት ያገለግላሉ

መላእክት ለክርስቶስ ለራሱ ሁለት ጊዜ እንደተገለጡለት እናነባለን፡፡ አንደኛው፡- ገና በአገልግሎቱ መጀመሪ አካባቢ ሲሆን ሌላ ጊዜ ደግሞ በአገልግሎቱ መጨረሻ አካባቢ ነው፡፡ ለምሳሌ ስለ ክርስቶስ አመጣጥ ካወጁበት እና ስሙን ካስተዋወቁበት ጊዜ አንስቶ እንዲሁም ስለ መወለዱና ስለልጅነት ህይወቱ እስከተተረከበት ድረስ በልዩ ልዩ ወንጌሎች ውስጥ እንመለከታለን (ማቴ 1፡2-23ሉቃ 1፡26-38፤ ማቴ 2፡13፤ ቁ. 19፤ ሉቃ 2፡9-15)፡፡ እንዲሁም ጌታ በምድረ በዳ በተፈተነበት ወቅት ደግሞ የመላእክቱን ሚና እንመለከታለን (ማቴ 4፡፤ ማር 1፡13)፡፡ በመከራውና በከባድ ሁኔታ ውስጥ በነበረበት የሥቃይ ህይወቱም ወቅት የመላእክቱን ሚና እንመለከታለን (ሉቃ 22፡43)፡፡ መላእክቱ የክርስቶስን ትንሳዔና እርገቱን ደግሞ ሲያውጁት እንመለከታለን (ማቴ 28፡2፤ ቁ. 5 እና ሃዋ. ሥራ 1፡10-11)፡፡

መላእክቱ ሰማይንና ምድርን በሚያገናኘው ሥፍራ ሆነው ወደ ላይ ሲወጡና ወደ ታች ሲወርዱ በቁሳዊና በመንፈሳዊ ዓለማት መሃል በሚታዩና በማይታዩ ዓለማት አገዛዞች ወይም መንግሥታት መሃል ሥራ ሲሰሩ እናስተውላለን (ዘፍ 28፡12)፡፡ ይሁን እንጂ መላእክቱ ያንን ሥራ እንዴት ይሰሩ እንደነበረ ከኛ እይታ ውጪ ነው፡፡ ነገር ግን ምንም እንኮን የሥራቸው አተገባባር በግልጽ ባይታየንም የመላእክቱ አሰራር ፈጽሞ የተደበቀ ሳይሆን ዋነው መልእክቱ ግልጽ ነው ማለት ይቻላል፡፡

[1] ‘Surely, since the splendour of the divine majesty shines in them, nothing is easier for us than to fall down, stupefied, in adoration of them, and then even to attribute to them everything that is owed to God alone’ (Calvin, Institutes, 1.14.10; 170).

የመላእክት መልእክተኛነታቸው

በመጀመሪያ ደረጃ፤- መላእክት መልእክተኞች ናቸው፡፡ አንድንም ሰው ወክለው ይናገራሉ፡፡ እግዚአብሄርም ለህዝቡ ሲገለጥ መላእክቱ በሰውና በእግዚአብሄር መሃል በመምጣት ለእግዚአብሄር ንግግር መሃከለኛ በመሆን መልእክቱን ያስተላልፋሉ፡፡ የእግዚአብሄርንም የማዳን ሥራውን በማከናወን የማስታረቅ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ የእግዚአብሄርን ቃል በመናገር ምልእክቱን ወደ ሰው ልጆች ያስተላልፋሉ፡፡

ገና ከመጀሚዎቹ የወንጌሎቻችን ክፍሎች እንደምናስተውለው የመላእክት ንግግርና አገልግሎታቸው ግልጽ ሆኖ ያታያል፡፡ ለምሳሌ መልኣኩ ገብርኤል ስለ መጥምቁ ዮሃንስ እና ስለ ኢየሱስ መወለድ የእግዚአብሄርን መልእክት ለዘካሪያስ እና ለማሪያም በግልጽ ያደረገውን እውነት ማየት ይቻላል (ሉቃ. 1፡11-20 ቁ. 26-38)፡፡ ሌላው ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ በተወለደበት ወቅት የብዙ መላእክት ቡድን የጌታችንን የኢየሱስን የመወለድ ታሪክ አጅበው እንደነበሩ ማስተዋል ይቻላል፡፡ በዚያም ወቅት ተሰብስበው ሲያደርጉት የነበረው እግዚአብሄርን የማመስገንና የማድነቅ ሥራ ሲሆን ሌሎችም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው አዲስ የተወለደውን  የእግዚአብሄርን ልጅ እንዲያመልኩት ማነሳሳት ነበር (ሉቃስ 2፡13-14)፡፡ መሪያም ኢየሱስን በማህጸንዋ ይዛ ከዮሴፍ ጋር በብዙ መከራ ውስጥ ሲሰደዱ በነበረበትም ወቅት ከእግዚአብሄር ዘንድ በማምጣት ዮሴፍንና ማሪያምን ሲመራቸው የነበረው መልኣኩ ነበር፡፡ ከዚያም በኃላ ዮሴፍን ወደ ግብጽ ሲሄድም ሆነ ሲመለስ ከክፉ ሁሉ የመከላከል ሥራ ሲሰራ የነበረውና ቤተሰቡን ሁሉ ከሄሮዲስ አደገኛ እቅድ የጋረደው መልኣኩ ነበር (ማቴ 1፡20-24፤ 2፡13 ቁ. 19-20)፡፡

በሃዋሪያት ሥራ 10-1-8 ስንመለከት የእግዚአብሄርን የድነት መልእከት ለብሄሮች ሁሉ መድረስ እንዳለባቸው የተረዳውን የቆርኔሌዎስን ታሪክ ያስተዋወቀውም መልኣኩ ነበረ፡፡ እንዲሁም ፍልጶስ እንዲነሳና በደቡባዊው መንገድ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ብሎም ወደ ጋዛ እንዲሄድ አቅጣጫ የሰጠው መልኣኩ እንደነበረ ማስተዋል ተገቢ ነው፡፡ ለምሳሌ በሃዋ. ሥ. 8፡26 እና ቁ. 29 እንደምናየው የመላእክቱ ምስክርነት ለእግዚአብሄር ታላቅ ዓላማው ትልቅ ማስረጃ ነው ማለት ነው፡፡ በዚህም ታላቅ የእግዚአብሄር እቅድ ውስጥ በጴጥሮስ አማካኝነት ወደ ቆርኔሌዎስ በመጣው መልእክት ውስጥ አስደናቂ የሆነውን የአህዛብን ወደ ታላቅ ድነት ውስጥ የመጠቃለላቸውን ምስጢር እንመለከታለን (ሃዋ. ሥ. 10፡3-7)፡፡

መላእክት በእግዚአብሔር አገልግሎት ውስጥ የተዋጊነት ሚና አላቸው

ለምሳሌ፡- በዘጸ. 14፡19 ላይ የእግዚአብሄር መልኣክ ከግብጻውያን ባርነት ነጻ የወጣውን የእግዚአብሄርን ህዝብ የመከላከልና የመርዳት ሥራ ሰርቶአል፡፡ በ2ኛ ነገስት 6፡11-17 ደግሞ ተራራውን ሞልቶ በነበረውን በእሳት ሰረገሎች ተከቦ የነበረውን ኤልሳን ከክፉ አደጋ እንደተከላከለ እናያለን፡፡ እንዲሁም ደግሞ ሰናክሬም የተባለው የአሶራውያን ንጉስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ሲያስጨንቅ በነበረበት ወቅት የጌታ መልኣክ ወጥቶ 185 000 የጠላትን ሠራዊት እንደ ደመሰሰ እንመለከታለን (2 ነገስት 19፡35)፡፡ ከተለመደው ዓይነት ውጪ በሆነ ሁኔታ ክሩቤል እንደ ተገለጠና በእግዚአብሄር ፊት ቆሞ ህዝቡን እንደተከላከል  እናያለን (ዘፍ. 3፡24)፡፡ እንዲሁም ሰፋ አድርገን ስናስብ የዲብሎስንና የክፋትን ኃይሎች ሁሉ ለመዋጋት በሚደረገው ትንቅንቅ የእግዚአብሄርን መልኣክ ታላቅ ሚና እንመለከታለን (ራእይ 12፡7፤ ይሁዳ ቁ. 9)፡፡ እንደ ከፍተኛ ደረጃ የውትድርና ማእረግ እና የእግዚአብሄርን መንግስት ወደ ፊት ለማስፋፋት መላእክት በብርጌድ ተደራጁ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ እንዲሁም በማቴ. 26፡53 እንደምናነበው ኢየሱስም ከእግዚአብሄር ዘንድ ስለሚላኩት ከአሥራ ሁለት ጭፍራዎች ስለሚበዙ 72 000 ሺህ መላእክት ይናገራል፡፡

በነጠላም ሆነ በቡድን አማካኝነት በመላእክት አገልግሎት የእግዚአብሄር ህዝብ ጠላቶች ሁሉ የሚደመሰሱበትና የሚቀጡበት የፍርድ ጊዜም እንዳለ ይናገራል (መዝ. 78፡49-51፤ ዘጸ. 12፡29፤ 2ነገስ. 19፡35፤ ኢሳ. 37፡36)፡፡ በአንድ ወሳኝ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ ህዝቡን በመቅሰፍት በመምታት በኢየሩሳሌምም ላይ ቅጣትን የሚያመጣው ራሱ መልኣክ እንደሆነ እናያለን (2 ሳሙ. 24፡16-17)፡፡ ጌታችን ኢየሱስም እርሱ እንደሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀን በብዙ ቅዱሳን መላእክት ታጅቦ እንደሚገለጥና በታላቁ የአባቱ ክብር እንደሚመለስ ለእያንዳንዱም እንደየሥራው እንደሚከፍል ይናገራል (ማቴ 16፡27)፡፡

 በራእይ መጽሃፍ 8፡6-9- 9፡21፤ 15፡1-1824 ደግሞ መላእክት በብዙ የሚቆጠሩና የእግዚአብሄርን ፈቃድ የሚደርጉ ሆነው ተገልጸዋለል፡፡ እነርሱም የባቢሎንን መውደቅ የሚውጁ ብቻ ሆነው አልተገለጹም፡፡ ነገር ግን መልኣኩ ሚካኤል ከሠራዊቱና ከበጉ ጋር በመሆን የእርሱን ፈቃድ ለመፈጸም ወደፊት ይጓዛል፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ከሰማያት በሚገለጥበት ወቅት ቅዱሳን መላእክቱን በሚንጸባርቅ የእሳት ነበልባል ከራሱ ጋር ከሰማያት ያመጣቸዋል፡፡ በዚያም ቀን በብዙ በቀልና የፍርድ ኃይል ተሞልቶ እግዚአብሄርን በማያውቁትና ለክርስቶስ ወንጌል በማታዘዙት ሁሉ ላይ ይገለጣል (2ተሰሎ. 1፡7-8)፡፡ ከዚያ ሁሉ በላይ ደግሞ ስሞቻቸው በህይወት መዝገብ ያልተጻፈውን ሁሉ ከዲብሎስ ጋር ለጥልቀቱ መጨረሻ ወደ ሌለው የእሳት ባህር ይጥላቸዋል (ራእይ 20፡1-4)፡፡

በጣም ብዙ የሚያስፈሩና የሚያስጨነረቁ ነገሮች አሉ፡፡ ይህንኑ ስናስብ መላእክት የእግዚአብሄርን ነጻ የማውታትና የበቀል ሥራዎቹን ይናገራሉ፤ ለሌሎችም ህዝቦች ሁሉ ያስተላልፋሉ፡፡ እንዲሁም ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ መቃብር ሥፍራ መግቢያ አካባቢ የነበረውን ድንጋይ እንዲንከባለል ዜና ለማስተላለፍ ከሰማይ የወረደውና ለመግደላዊት ማርያምና ለሌላዋም ማርያም ይህንኑ እውነት የገለጸው ይሀው የጌታ መልኣክ ነበር፡፡ ጌታ ከሙታን የመነሳቱንና ከጥቂት ጊዜ በኃላ በገሊላ ሊያገኛቸው እንደሚፈልግም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲስተላልፉ ታላቅና አስደናቂ ዜና የነገራቸውም የጌታ መልኣክ ነበር (ማቴ 28፡1-7)፡፡ በሁለት የተለያዩ ገጠመኞች ሃዋሪቱ ሁሉ ከወህኒ እንዲፈቱ (ሃዋ. ሥ. 5፡1-19) እና ሃዋሪያው ጴጥሮስ ደግሞ  በተዓምር ከእሥራት ነጻ እንዲወጣ መልእክት ያመጣውና ያስተላለፈው ይሀው የጌታ መልኣክ ነበረ (ሃዋ. ሥ. 12፡6-10)፡፡  

መላእክት የክርስቶስን አገልግሎት ይደግፋሉ

መላእክት ረዳቶች ናቸው እንጂ ዋናዎቹ አይደሉም፡፡ ከላይ ስለ መላእክት የተወያየነው ሁሉ መላእክት አገልጋዮች እና ረዳቶች ናቸው በሚል ሃሳብ ሊጠቃለል ይችላል፡፡ እንዲሁም በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ስናየው የመላእክት ሥራቸውና ተግባራቸው በጣም አስደናቂና አስገራሚ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሥራቸውና ተግባራቸው ዋናውን ስፍራ የሚይዝ ሳይሆን ዋናውና በእግዚአብሄር በሚከናወኑ ቁልፍ ሥራዎች  ላይ እንደ ተጨማሪ ብቻ ሆነው ሊወሰዱ የሚገባቸው ናቸው፡፡ በሌላ አባባል በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ አገልግሎት የሚለው ቃል የመላእክትን የአገልግሎት ሚና በሚገባ የሚገልጽ ሃሳብ ነው፡፡

መላእክት እግዚአብሄር ለህዝቡ በሚሰራቸውና በሚያደርግላቸው ታላላቅ ተግባራት ወቅት በጣም ጠቃሚና ወሳኝ ሆነው የመርዳት ወይም የመደገፍ ሥራዎችን በመሥራት ይታወቃሉ፡፡ በተለይም በኃጢኣታቸው መክኒያት በሚከሰቱ ከባባድ የጭንቀት፤ የአደጋና የእልቂት ጊዜያት መላእክት የእግዚአብሄር ሥራዎች ማስፈጸሚያ አገልግሎት ሰጪ መሳሪያዎች ሆነው ያገለግላሉ፡፡ የእግዚአብሄር የማዳን፤ የመከላከል፤ ህዝቡንም የመጠበቅና መልካም የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ለህዝቡ የማዘጋጀት ጉዳይ የሚከናወናው በመላእክት አማካኝነት ነው (መዝ. 34፡7፤ 91፡11፤ ማቴ. 18፡10)፡፡ መላእክት የእግዚአብሄርን ዓላማ ለመፈጸምና እቅዱን ለማከናወን የተፈጠሩ ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ ምክኒያቱም እነርሱ ሁሉን የሚያደርጉት ስለ እግዚአብሄር ህዝብ  የድነት እና የጽድቅ አገልጋዮች ሆነው ነው (እብ. 1፡14)፡፡ ይህም የሚያሳየን ስለ መላእክት አገልግሎት ስናስብ ባህሪቸው ሁሉ በአገልጋይ መናፍስትነት የሚታወቀውን ተግባራቸውን ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ስለ ሃብታሙ ሰውና ስለ አልዓዛር በምሳሌ እንደ ተናገረው የሞት አዋጅ እንኮን በታወጀበት ጊዜ የእግዚአብሄር መላእክት ህዝቡን እንዴት አድርገው ወደ ገነት እንደሚወስዱኣቸው ይናገራል (ሉቃ. 16፡22፤ 2 ነገስ. 2፡11)፡፡ በመጨረሻውም ቀን የሰው ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ በታላቅ ክብር በሚገለጥበት ቀን ክርስቶስ ራሱ እንዳለው ከአራቱም ነፋሳት ወይም ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ የሚገኙትን ምርጦች እንዲሰበስቡ መላእክትን እንደሚልክ ይናገራል (ማቴ. 24፡30-31፤ ማር. 8፡38)፡፡ ሃዋሪያው ጳውሎስም ይህንኑ ሃሳብ ሲያጠናክር ጌታ ራሱ ከሰማያት እንደሚወርድና በመላእክቱ አለቃ ድምጽ እንደሚገለጥ ይናገራል (1 ተሰ. 4፡16)፡፡

መላእክት ንስሃ በሚገቡት አማኞች ድነት ምክኒያት ታላቅ ደስታ እንደሚሰማቸው ይናገራል (ሉቃ. 15፡10)፡፡

በዮሃንስ ራእይ ደግሞ እንደምናነበው ጌታችን ኢየሱስ ስለ ሰባቱ አብያተ ክርስቲናት ሲናገር የአብያተ ክርስቲያናትን ጉባኤዎች እንዲጠብቁ መላእክትን እንደሚሰድላቸው ይናገራል፡፡

Copyright © 2022 by Benjamin T. F. Dean

ይመዝገቡ

ሙሉ ስም
Consent
I give permission for Great Truths to store my email address for the purposes of sending me regular updates. I understand that I can unsubscribe at any time using the link in any email.